Icon of Kality

Icon of Kality Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Icon of Kality, Sports, US Newyork, Rochester, NY.

09/01/2026
09/01/2026
08/28/2026

የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባና እድሳት ሊጠናቀቅ 8 ቀናት ብቻ ቀሩት

ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የተከራይና የአከራይን ግንኙነት በህግ ማዕቀፍ ለመምራትና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ (ከወረዳ 10 በስተቀር) በክፍለ ከተማው በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባና እድሳት እያከናወነ ይገኛል።

ይህ በክፍለ ከተማው እየተከናወነ የሚገኘው የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባና እድሳት ሊጠናቀቅ 8 ቀናት ብቻ የቀረው በመሆኑ በክፍለ ከተማው የምትገኙ አከራዮችም ሆናችሁ ተከራዮች በሚኖሩበት ወረዳ አስፈላጊውን መረጃ በማሟላት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በሁሉም የሥራ ቀናት እስከ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም ብቻ በአካል ተገኝታችሁ የውል ምዝገባና እድሳት በማካሄድ ራስን ከቅጣት ማዳን እንደሚገባ ተገልጿል።

08/27/2026

ቃል ሐሳብን ይቀርጻል፤ ሐሳብ ደግሞ ዓለምን ይለውጣል። ንግግሮች የጊዜን ወሰን ሰብረው፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገሩ የሕዝቦች የማንነት ማኅተምና የዘመን ምስክር ናቸው። በመሪዎች መነጽር ሲታይ ቃል ቀላል ድምፅ ሳይሆን፣ ታሪክን የሚወስን፣ ማኅበረሰብን የሚቀይር እና ሀገርን የሚገነባ የኃይል ምንጭ ነው። በመሪዎች ቃል ውስጥ ህዝብ የሀገርን ተስፋና የመሪዎቹን ርዕይ እንዲቃኝ ያስችላል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዘጋጅነት የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ከ2017 እስከ 2018 ዓ.ም ያደረጓቸውን ንግግሮች እና ያስተላለፏቸውን መልዕክቶች ዳግም «ከመስከረም እስከ መስከረም» በተሰኘው መጽሐፍ 8ተኛ ቅጽ በይፋ ለአንባቢያን ቀርቧል።
እርስዎም በመጽሐፉ ዘልቀው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያየ አቅጣጫ ሀገር ለማቅናት የተጓዟቸውን የዓመት ጉዞ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጓቸው ቁልፍ ንግግሮች እና ያስተላለፏቸውን አቅጣጫ ጠቋሚ መልዕክቶች ይቃኙ።

ሙሉ መጽሐፉን ለማግኘት ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ:-https://share.google/uTjPqcMG1OFDWj7Xq

Words shape thought, and thought transforms the world. Speeches transcend the boundaries of time, serving as an enduring seal of a people's identity and a testament to an era, passed down from generation to generation. Viewed through the lens of leadership, a word is never merely a fleeting sound, it is a source of power that defines history, reshapes society, and builds a nation, allowing the public to discern a nation's hope and its leaders' vision through their executive rhetoric.

Prepared by the Office of the Prime Minister of Ethiopia, the speeches and messages delivered by His Excellency Prime Minister Abiy Ahmed (PhD) from 2017 to 2018 E.C. have been officially released to readers in the 8th volume of the book entitled “Meskerem to Meskerem.” Delve into this volume to explore His Excellency the Prime Minister’s year long journey and multifaceted efforts to reconstruct and uplift the nation through his key speeches and strategic directives delivered over time.

↓ Discover the full journey, access the book here ↓

Link: https://share.google/uTjPqcMG1OFDWj7Xq

08/27/2026
08/27/2026

#ማስታወቂያ

በክፍለ ከተማው ለምትገኙ ኢንተርፕራይዞች በሙሉ!

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት በሥራ ቦታዎች ላይ ተደራጅተው ለሚሰሩ ኢንተርፕራይዞች የ2019 በጀት ዓመት የውል ማደሻ ጊዜ ከሐምሌ 1/2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም ድረስ መሆኑን በመግለጽ ውላቸውን ያላደሱ አካላት በአስቸኳይ ቀርበው እንዲያድሱ ጥሪ አቀረበ።

ጽ/ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 84/2016 በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት የውል ማደስ ሂደቱ የሚመለከተው የአምስት ዓመት የጊዜ ገደብ ያልሞላቸውን ኢንተርፕራይዞች እንደሆነ ያሳወቀ ሲሆን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ውላቸውን በማያድሱት ላይ መመሪያውን ተከተሎ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድም አሳስቧል።

-ውል ለማደስ የሚያስፈልጉ ሰነዶች፦

-የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የነዋሪነት መታወቂያ

-ነባር የኪራይ ውል እና የታደሰ የደረጃ ዕድገት ማስረጃ

-የኪራይ ክፍያ ደረሰኝ

-የግቢ ኮሚቴ ግዴታዎችን በአግባቡ መወጣታቸውን የሚያረጋግጥ የኮሚቴ ማረጋገጫ

ኢንተርፕራይዞች እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ በማደስ ኃላፊነታችንን እንወጣ!!!

Address

US Newyork
Rochester, NY

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Icon of Kality posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category