29/08/2026
🔥 የሰሜን ለንደንን ቁስል የኮረኮረው የኢላንጋ “ሄነሪ-ስታይል” ደስታ አገላለጽ! 👑⚽
በቶተንሃም ሆትስፐር ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ የሜዳ ላይ ፍልሚያ ብቻ አልነበረም፤ የቶተንሃም ደጋፊዎችን እጅግ ያበሳጨና ማህበራዊ ሚዲያውን ያስወራ ታላቅ ድራማ የታየበት ምሽት ነበር!
ኢላንጋ የመጀመሪያውን ጎል ከመረብ ካሳረፈ በኋላ በቀጥታ ወደ ኮርነር ፍላጉ በመሮጥ በእግሮቹ መንሸራተት (Knee Slide) አድርጎ በቆራጥነት አንገቱን ደፍቶ ቆመ—ይህ ደግሞ የጠቅላላው አርሰናል እና የእግር ኳስ አፈ ታሪክ የሆነው የቴሪ ሄነሪ አይኮኒክ ደስታ አገላለጽ ትክክለኛ ግልባጭ ነበር! 👑⚡
ይህ ድርጊት ለቶተንሃም ደጋፊዎች ተራ የጎል ደስታ አልነበረም። ከዚህ ቀደም የፈረንሳይ ኤምፓየር ቴሪ ሄነሪ በስፐርስ ላይ ጎል ባስቆጠረ ቁጥር በሃይበሪና በሰሜን ለንደን ደርቢዎች የሚያደርገውን አይኮኒክ የደስታ አገላለጽ ቀጥታ የሚያስታውስ በመሆኑ የስፐርስን ደጋፊዎች በስታዲየምም ሆነ በማህበራዊ ሚዲያ እጅግ አበሳጭቷቸዋል! 😡💥
የኢላንጋ ይህ የድፍረት ደስታ አገላለጽ በአሁኑ ሰዓት በቲክቶክ፣ ፌስቡክ እና ኤክስ (ትዊተር) ላይ ዋነኛው ትሬንዲንግ ቶፒክ ሆኗል።