03/02/2019
�� በዛሬው እለት በታላላቅ የአውሮፓ ጋዜጦች ላይ የወጡ በርካታ እግርኴሳዊ ዜናዎች።
═════════════════════════
⚽️ቸልሲም ማንችስተር ዩናይትድን ለመቀላቀል ተዘጋጅቱዋል የቶተንሀሙን አሰልጣኝ ሞሪሲዮ ፖቸቲኖን አሳምነው በክረምት ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ለመውሰድ።(Sunday Express)
:
⚽️የማንችስተር ዩናይትዱ ግዜያዊ አሰልጣኝ ኦሊገነር ሶሻየር ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴህያ ፈረንሳያዊውን የቡድን አጋሩን አንቶኒዮ ማርሻልን በመከተል አዲስ ኮንትራት እንዲፈርም ይፈልጋል።(Evening Standard)
፡
⚽️ቶተንሀም የክረምቱ የዝውውር መስኮት እንደተከፈተ ከበርንስማውዝ ጋር አስደናቂ ግዜን እያሳለፈ የሚገኘውን ዌልሳዊ አማካይ ዴቪድ ብሮክስን ለማስፈረም £50 million አዘጋጅተዋል ማንችስተር ዩናይትድም የተጫዋቹ ፈላጊ ክለብ ነው።(Sunday Mirror)
፡
⚽️ቶተንሀም ቤልጄማዊውን የቸልሲ የ 25 አመት አጥቂ ሚቺ ባቱሺያን በውሰት ለማስፈረም ለሰማያዊዎቹ £8million ቢያቀርቡም ቸልሲዎች ግን በቀጥታ ተፎካካሪ ቡድን ማጠናከር ነው በማለት ለክሪስታል ፓላስ ሰተውታል።(DH, via Sun on Sunday)
፡
⚽️የኒውካስሉ ባለቤት ማይክ አሽሊ በክረምት ኮንትራታቸው የሚጠናቀቀው አሰልጣኝ ራፋኤል ቤንቴዝን የሚፈልጉት ፓራጉዋዊ ኩዋስ አቀጣጣይ ማጉዌል አልሜሮን ስለፈረመላቸው በጀምስ ፓርክ አዲስ ኮንትራት እንደሚፈርም ተማምነዋል። (Sunday Mirror)
፡
⚽️ጉዳት ላይ የሚገኘው ጣልያናዊው አማካይ ማርኮ ቬራቲ ለመጀመሪያው ዙር ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ለሚደረገው የቻምፕዮን ሊግ ጫወታ ሊደርስ ይችላል።(Mail on Sunday)
፡
⚽️በውሰት ለአርቢ ላይፕዚክ የፈረመው የአርሰናል አማካይ ኤሚሊ እስሚዝ ሮው ወደ ጀርመን ካቀና ቡኃላ ልምምድ አልጀመረም ምክንያቱ ደግሞ በደረሰበት የብሽሽት ጉዳት ለሶስት ሳምንታት ከሜዳ ይርቃል።(Independent on Sunday)
፡
⚽️የሊቨርፑሉ አለቃ ጀርገን ክሎፕ ጊኒያዊው አማካይ ናቢ ኬታ ባለፈው ክረምት ከአርቢ ላይፕዚክ በ£53million ከተዘዋወረ ቡኃላ አሁን ጥሩ መሻሻል እያሳየነው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።(Independent on Sunday)
:
⚽️አያክስ የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች የሆነውን እና የክለቡ ቴክኒካል ዳይሬክተር ማርክ ኦቨርማስን ከክለባቸው በመልቀቅ የመድፈኞቹ ቴክኒካል ዳይሬክተር እንዳይሇን ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው።(mirror)
:
⚽️አርሰናል በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከኮንትራት ነፃ የሚሆነውን የፓሪሴንጀርመኑን አማካይ አንድሪያን ራቢዮትን ለማስፈረም ከወዲሁ ክትትል እያደረገ ነው።(mirror)
፡
⚽️የማንችስተር ሲቲው አለቃ ፔፕ ጋርዲዮላ ዘንድሮ በክሪስታል ፓላስ አስደናቂ ግዜ እያሳለፈ የሚገኘውን የመስመር ተከላካይ ዋን ቢሳካን እና የሌስተር ሲቲውን የመስመር ተከላካይ ቤን ቻልዌልን በክረምት ሁለቱንም።(sun)
፡
⚽️የቸልሲው አማካይ ቲም ባካዮኮ በውሰት ከሄደበት የጣልያኖ ክለብ ኤስሚላን በድጋሚ ወደ እንግሊዝ መመለስ እናት ክለቡን መቀላቀል አይፈልግም ዝውውሩ ቇሚ እንዲሆን ይፈልጋል።(star)
፡
⚽️የሬያል ማድሪዱ በረኛ ቲቦ ኮርቱዋ ከፓሪሴንጀርመኑ ብራዚላዊ አጥቂ ኔይማር ይልቅ የቤልጄም ብሔራዊ ቡድን አጋሩ የሆነው ኤደን ሀዛርድ ቢመጣ ምርጫው እንደሆነ ተናግሯል። (Het Nieuwsblad, via Sun on Sunday)