ጉራ ሚዲያ / Gura Media

ጉራ ሚዲያ / Gura Media ስፖርት ከፍቅር ጋር

የ2017 የ ቸሃ ወረዳ የጤና የውስጥ ለውስጥ ውድድር በተደረገው የምድብ ሁለት ጨዋታ ኬር ከ ትምርት በተደረገው ውድድር 2 እኩል በሆነ ውጤት ተጠናቁአል::
14/06/2025

የ2017 የ ቸሃ ወረዳ የጤና የውስጥ ለውስጥ ውድድር በተደረገው የምድብ ሁለት ጨዋታ ኬር ከ ትምርት በተደረገው ውድድር 2 እኩል በሆነ ውጤት ተጠናቁአል::

ወልቂጤ ከተማ ወደ ሊግ አንድ ወርዷል !በዘንድሮው የውድድር ዘመን ጅማሮ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በአስተዳደራዊ ጉዳዮች ወደ ከፍተኛ ሊጉ ለመውረድ ተገዶ የነበረው ወልቂጤ ከተማ አሁን ደግሞ ...
06/04/2025

ወልቂጤ ከተማ ወደ ሊግ አንድ ወርዷል !

በዘንድሮው የውድድር ዘመን ጅማሮ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በአስተዳደራዊ ጉዳዮች ወደ ከፍተኛ ሊጉ ለመውረድ ተገዶ የነበረው ወልቂጤ ከተማ አሁን ደግሞ ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ሊግ አንድ መውረዱ ዛሬ አመሻሽ ተረጋግጧል።

መጋቢት 21/2017 ዓ.ምበረመዷን ፆም ወቅት የነበረው እዝነት ሊቀጥል  እንደሚገባ ተገለፀ።1446ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በቸሀ ወረዳ  የጀመዓ ሶላት ስነ- ስረአት በድምቀት ተካሄደ። በ...
30/03/2025

መጋቢት 21/2017 ዓ.ም

በረመዷን ፆም ወቅት የነበረው እዝነት ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለፀ።

1446ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በቸሀ ወረዳ የጀመዓ ሶላት ስነ- ስረአት በድምቀት ተካሄደ።

በፌቅጠረቅ ከተማ ነስር መስጂድ በሶላቱ ስነስርአት አግኝተናቸዉ ያነጋገርናቸዉ ኡስታዝ ኢብራሂም ሚፍታ በሰጡት ሀሳብ ኢድ ለሙስሊሙ ኡማ ከአላህ የተቸረን የደስታና የክብረ በዓል እለት እንደሆነ ተናግረዉ በዚህ በደስታ ቀናችን አቅመደካሞች እና ምስኪኖች የደስታው ተቋዳሽ እንዲሆኑ ሁሉም ሰው መረዳዳትና መደጋገፍ እንዳለበት አሳስበዋል።

በረመዳን ፆም ወቅት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በፀሎትና በኢባዳ ወደ ፈጣሪው በመቅረብ ፈጣሪን የሚያስደስትበት በመሆኑ በሌሎች ጊዜያትም አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

አንድ ወር ሙሉ ሶላት በመስግድ እና በፆም እናሳልፋለን ምስኪኖችን በመርዳትና ወደ ፈጣሪ የሚያቀርበንም ደግ ስራ እየሰራን አሳልፈናል ብለዋል።

በዛሬው እለት የሚሰገደው የዒድ አልፈጥር ሶላት እጅግ ተወዳጅ እና ጠንካራ የነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ ሱናነት እንዳለውም ገልፀዋል።

ምእመናኑ ከዒዱ ማግስት ጀምሮ ለስድስት ተከታታይ ቀናት የሸዋል ሱና ፆም መፆም እንዳለበት አበክረው ያሳሰቡ ሲሆን ላቅ ያለ ምንዳ እንዳለውም አያይዘው ገልፀዋል።

አንዳንድ የበዓሉ ተሳታፊ የእምነቱ ተከታዮችም እንደተናገሩት በዓሉ በድምቀት እንደተከበረ ገልፀው በዓሉን በመረዳዳት እና ለሰላማችን ዱዓ በማድረግ ልናከብረው ይገባል ብለዉ በዛሬ ዕለት ሶላቱ በመላ ሀገሪቱና በዓለም ደረጃ እንደሚካሄድ ተናግረዋል ሲል የዘገበዉ የቸሀ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ነዉ።

ዋልያዎቹ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጅቡቲ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ 6ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። የዋልያዎቹን የማሸነ...
25/03/2025

ዋልያዎቹ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጅቡቲ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ 6ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የዋልያዎቹን የማሸነፊያ ግቦች አቡበከር ናስር 3x እና በረከት ደስታ 3x አስቆጥረዋል።

በጨዋታው አቡበከር ናስር እና በረከት ደስታ ሀትሪክ መስራት ችለዋል።

በማጣሪያው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን አሸንፏል።

ዋልያዎቹ በምድቡ ደረጃ ሰንጠረዥ ጊኒ ቢሳውን በግብ ክፍያ በመብለጥ ደረጃቸውን ወደ አራት ከፍ ማድረግ ችለዋል።

የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

4️⃣ ኢትዮጵያ :- 6 ነጥብ

6️⃣ ጅቡቲ :- 1 ነጥብ

የዋልያዎቹ ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ነሀሴ 28/2017 ዓ.ም - ግብፅ ከ ኢትዮጵያ

ጳጉሜ 1/2017 ዓ.ም - ሴራሊዮን ከ ኢትዮጵያ

ምሁር ኢየሱስ ገዳም የምሁራን መንደር ምሁር ኢየሱስ ገዳም የሚገኝው በጉራጌ ዞን በምሁር አክሊል ወረዳ ቆረር ቀበሌ ውስጥ ሲሆን ከአዲስ አበባ በ207 ኪ.ሜ፣ ከዞኑ ርዕሰ ከተማ ወልቂጤ በ52...
24/03/2025

ምሁር ኢየሱስ ገዳም
የምሁራን መንደር

ምሁር ኢየሱስ ገዳም የሚገኝው በጉራጌ ዞን በምሁር አክሊል ወረዳ ቆረር ቀበሌ ውስጥ ሲሆን ከአዲስ አበባ በ207 ኪ.ሜ፣ ከዞኑ ርዕሰ ከተማ ወልቂጤ በ52.ኪ.ሜ፣ ከወረዳው ርዕሰ ከተማ ሀዋርያት 3ኪ.ሜ ገባ ብሎ በስተሰሜን ምስራቅ በኩል ይገኛል፡፡

ገዳሙ ሀገራችን ኢትዮጵያ ካሏት በርካታ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳማት መካከል በዋናነት ተጠቃሽ ሲሆን በገዳሙ ውስጥ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ከዘመነ ዮዲት ጉዲት በፊት በ804 ዓ.ም እንደተተከለ ታሪክ ያስረዳል፡፡

በገዳምነት የተመሰረተው/ የተገደመው / ደግሞ በኢትዮጵያዊው ፃዲቅ በአቡነ ዜና ማርቆስ በ13ኛ ክ.ዘ /በ1250 ዓ.ም/ መሆኑን መዛግብት ይጠቁማሉ፡፡ አካባቢው ከባህር ወለል 2330 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡

የገዳሙን ዕድሜ ረጅምነት የሚያወሱ ብዛት ያላቸው ሀገር በቀል የዝግባ፣የወይራ፣የፅድ ወዘተ ተፈጥሮአዊ ይዘት ያላቸው ዛፎች እጅብ ብለውና ግርማ ሞገስ ተላብሰው ወደ ገዳሙ የሚመጣውን ሰው በመጀመሪያ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለው ይቀበሉታል፡፡

ሌላው የገዳሙን ጥንታዊነት እና ታሪካዊነትን የሚያመላክቱ ተዳሳሽና የማይዳሰሱ ቅርሶች ሲገኙ ተዳሳሽ የሆኑ ቅርሶች በዘመናዊ ሙዚየም ተሰድረው ይገኛሉ። ጥቂት ቅርሶች ለመጥቀስ ያህል የብር መስቀል፣ የብራና መፃህፍት፣ መቁራሪት፣ ጽዋ፣ ደወል፣ የቀደምት የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ካባ፣ መለከት/ጡርንባ/፣ ውዥግራና ራስማር ጠመንጃዎች፣ ከአንድ ወጥ እንጨት ተፈልፍሎ የተሰራ የመጾር መስቀል፤የቅዱስ ዳዊትን ታሪክ የያዘ በስዕላዊ መልክ የተዘጋጀ መፅሐፍ ከነማህደሩ፤የነገስታት ደብዳቤዎች … ወዘተ ይገኛሉ፡፡

እንዲሁም በአቡነ መልከ ፃዲቅ ጵጵስና ዘመን ከተለያዩ ሀገሮች በገጸ በረከትነት የተበረከቱ በርካታ ንዋያተ ቅድሳትና ቅርሶች የሚገኙ ሲሆን ለአብነት በ1990 ዓ.ም ከሊባኖስ ለገዳሙ የተበረከተ የእጅ መቁጠሪያ ፣ከግሪክ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሱራፌል የተበረከተ የግሪክ ስዕል፣ የተለያዩ ጌጣጌጦች፣ የሰጎን እንቁላል እና መብራት ያላቸው መስቀሎች፣ ከግብፅ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኢንቶኒዮስ የተበረከቱ የቤተ መቅደስ መገልገያ ጽዋ የስነ-ስቅለት ምስል ያለበት መስቀል ይገኛሉ፡፡

እንዲሁም በ18ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጲያ ሰዓሊያን በእንጨት ላይ የሳሏቸው ስዕሎች፣ ኢትዮጲያ ፓትሪያርክ መሾም ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የነበሩና አሁን ያሉ ፓትሪያርኮች ፎቶግራፍ በሙዝየሙ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ገዳሙ በአጠቃላይ ከሚሰጣቸው ኃይማኖታዊ፣ባህላዊና ማህበራዊ አገልግሎቶች በተጨማሪ በማህበራዊ ዘርፍ ረገድ በሃዋርያት ከተማ ውስጥ የመዋዕለ-ህጻናት ትምህርት ቤት፣ የእንግዳ መቀበያና ማረፍያ ቤት፣ በገዳሙ ግቢ ውስጥ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ት/ቤት፣ የተለያዩ የዕደ ጥበብ ውጤቶች ማምረትና መሸጥ፣ የእንግዳ ማረፍያ ቤቶች፣ በወልቂጤ ከተማ ደግሞ ከመዋዕለ-ህጻናት እስከ 10ኛ ክፍል ባለሶስት ፎቅ ህንጻ ት/ቤት አስገንብቶ በማስተማር የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ እያደረገ ነው፡፡

ገዳሙ ዓመቱን ሙሉ የተለያዩ መንፈሳዊ ጎብኚዎች የሚጎበኙት ሲሆን በዋናነት ሶስት አበይት ክብረ በዓላት አሉት፡፡ እነሱም፡-
ታህሳስ ሶስት የአቡነ ዜናማርቆስ የእረፍት ቀን መታሰቢያ፣ ለረጅም አብይ ፆም አጋማሽ(ደብረዘይት) ልዩ የበገና ምሽት፣
በግንቦት ወር ውስጥ አብይ ፆም በተፈታ አርባኛው ቀን(የእርገት በዓል) ሲሆኑ በእነዚህ በዓላት ወቅት ቁጥሩ በዛ ያለ ከተለያዩ የአካባቢው፣ የሃገሪቱ ክፍሎች እና ከሃገር ውጪ በሚመጡ ቱሪስቶች በድምቀት ይከበራል፡፡

ገዳሙን ሊጎበኙ ሲሄዱ በተጓዳኝ

የሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ቦታ  ላይ የሊዝ ጨረታ ወጣ- ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ለሆቴል ግንባታ ተረክቦበት በነበረ ቦታ ላይ የሊዝ ጨረታ ወጣበት በጉራጌ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ቀደም ሲል ...
19/03/2025

የሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ቦታ ላይ የሊዝ ጨረታ ወጣ

- ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ለሆቴል ግንባታ ተረክቦበት በነበረ ቦታ ላይ የሊዝ ጨረታ ወጣበት

በጉራጌ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ቀደም ሲል ተፈራ ሆቴል ተብሎ ይጠራ የነበረውን ሆቴል በማፍረስ ለሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ለሆቴል ግንባታ ካለጨረታ ያስረከበ ቢሆንም ሻለቃ ይሌ ገብረስላሴ ወደ ግንባታ ሊገባ አልቻለም ፡፡

ቅዳሜ ገበያ ከከተማ አስተዳደሩ ማህበራዊ ድረ ገጽ እንደተረዳችው ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ከከተማ አስተዳደሩ ተረክቦ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የመሰረት ድንጋይ ያኖረበት ቦታ ላይ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ ወጥቶበታል።

በጨረታ ማስታወቂያው ላይ እንደተገለጸው በማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ቀደም ሲል ተፈራ ሆቴል ተብሎ ይጠራ የነበረው በከተማው መሀል ላይ የሚገኝ 5333.05 (አምስት ሺ ሶስት መቶ ሰላሳ ሶስት ) ካሬ ሜትር ስፋት እንዳለው ተገልጿል ፡፡

960 ተማሪዎችን የሚያስተናግደው አዳሪ ት/ቤት በ243 ሚሊየን ብር ግንባታው እየተከናወነ ነውአዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ...
19/03/2025

960 ተማሪዎችን የሚያስተናግደው አዳሪ ት/ቤት በ243 ሚሊየን ብር ግንባታው እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የአዳሪ ትምህርት ቤት ጎበኙ፡፡

ከ243 ሚሊየን ብር በሚልቅ ወጪ እየተገነባ ያለው ትምህርት ቤቱ፤ የመማሪያና የተማሪዎች ማደሪያ ክፍሎች፣ መመገቢያ አዳራሽ፣ ቤተ-መኩራ፣ ቤተ-መጻሕፍት፣ አይሲቲ ክፍልና ሌሎች መሠረታዊ ግንባታዎችን ማካተቱ ተገልጿል፡፡

ግንባታው ተጠናቅቆ በሙሉ ዐቅሙ አገልግሎት መስጠት ሲጀምርም ከ960 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይችላል መባሉን የጉራጌ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ አመላክቷል፡፡

በ2018 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሥራ እንደሚጀምርም ይጠበቃል ተብሏል፡፡

08/03/2025

Big shout-out to my newest top fans! Wende Gebre

የካቲት 29/2017በቸሀ ወረዳ 2017 ዓ/ም በወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት  አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየዉ የበጋ የዉስጥ ለዉስጥ እግር ኳስ  ዉድድር በያዶት  አሸናፊነት ተጠናቀቀ!~በቸሀ ወረዳ ወ...
08/03/2025

የካቲት 29/2017

በቸሀ ወረዳ 2017 ዓ/ም በወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየዉ የበጋ የዉስጥ ለዉስጥ እግር ኳስ ዉድድር በያዶት አሸናፊነት ተጠናቀቀ!
~
በቸሀ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት ላለፉት ሶስት ወራቶች ሲካሄድ የቆየው የ2017 የቀበሌዎች የዉስጥ ለዉስጥ የእግር ኳስ ዉድድር በዛሬዉ ዕለት ፍፄሜዉን አግኝቷል።

በካራቻ ሳሌዥያ እግር ኳስ ክለብ እና ያዶት የእግር ኳስ ክለብ 90 ደቂቃ አንድ አቻ በሆነ ዉጤት ተጠናቆ በመለያ ምት ለ6በ5 በመርታት የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የቸሀ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ሽምንሳ እንደተናገሩት የስፖርት ውድድሮች የህዝብ ለህዝብ ትስስርና ለአካባቢ ሰላም የሚሰጡት ጥቅም የጎላ በመሆኑ መሰል ውድድሮች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዉ ስፖርታዊ ስነምግባር ለአንድ ሀገር ስፖርት ትልቅ ደረጃ መድረስ ወሳኝ ነው፡፡ ስለሆነም በስነ ምግባር የታነፀና ስፖርታዊ ጨዋነትን መለያው ያደረገ ስፖርተኛ ልትሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡

የቸሀ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ደሳለኝ ፈታ እንደገለፁት በስፖርት ዘርፍ ላይ ያሉ አካላት ብቃታቸው ለማሳደግ መሰል አይነት ውድድሮች ወሳኝነት አላቸው ብለዉ

ዉድድሩም ላለፉት ተከታታይ ወራቶች ሲካሄድ መቆየቱን ገልጸዉ እንደ ሀገር ተተኪ ስፖርተኞች ለማፍራት ዉድድሩ ፋይዳዉ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

የዉድድሩ ዓላማ ተተኪ ስፖርተኞች የሚፈሩበት መሆኑን በመግለጽ በየዕድሜ እርከኑ ዉድድሮችን በማከናወን ዉጤታማ ትዉልድ መፍጠር እንደሚገባ አብራርተዋል።

ውድድሩ በሰላም ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸው አቅርበዋል።

በመጨረሻም ለኮከብ ተጫዋቾችና ዳኞች፣አሰልጣኞች፣ ኮከብ ግብ አግቢዎች እና ለሌሎችም ዉድድሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የተለያዩ ዕዉቅናና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል አንዲሁም የፀባይ ዋንጫ ለካራቻ ሳሌዥያ እግር ኳስ ቡድን ተበርክቶለታል ሲል የዘገበዉ የቸሀ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ነዉ።

በቸሀ ወረዳ 2017 ዓ/ም በወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት  አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየዉ  የዉስጥ ለዉስጥ እግር ኳስ  ዉድድር በካራቻ ሳሌዢያን እግር ኳስ ክለብ እና  ያዶት የእግርኳስ ከለብ ለዋን...
08/03/2025

በቸሀ ወረዳ 2017 ዓ/ም በወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየዉ የዉስጥ ለዉስጥ እግር ኳስ ዉድድር በካራቻ ሳሌዢያን እግር ኳስ ክለብ እና ያዶት የእግርኳስ ከለብ ለዋንጫ ፍልሚያ ደርሰዋል ።

መልካም እድል ለሁለቱም ክለቦች

አንድ ዓመት ከመንፈቅ በወልቂጤ ከተማ ማረሚያ ታስረው የነበሩት የምክር ቤት አባሉን የተከበሩ ታረቀኝ ደግፌን ጨምሮ የቀረበባቸውን የሐሰት ክስ በመቋረጡ የተነሳ በዛሬው ዕለት ከእስር ተፈተዋል...
03/03/2025

አንድ ዓመት ከመንፈቅ በወልቂጤ ከተማ ማረሚያ ታስረው የነበሩት የምክር ቤት አባሉን የተከበሩ ታረቀኝ ደግፌን ጨምሮ የቀረበባቸውን የሐሰት ክስ በመቋረጡ የተነሳ በዛሬው ዕለት ከእስር ተፈተዋል‼️

Address

Emdber
Wolkite

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጉራ ሚዲያ / Gura Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category