Wolkite City Sport Club

Wolkite City Sport Club Official page of wolkite city football club ወልቂጤ

Congratulations 🎉🎊🎈🍾 Halaba FC @ #@@
15/04/2026

Congratulations 🎉🎊🎈🍾 Halaba FC @ #@@

01/07/2025

ተናግረን ነበር ሰሚ ያጣ ጩኸት

የሀዘን ዜና ! ኢትዮጵያ ኮከብ ተጨዋቿን አጣች!አዲሱ ሙሽራ ማረፉ ተሰምቷል !በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ተጨዋች አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷ...
27/03/2024

የሀዘን ዜና ! ኢትዮጵያ ኮከብ ተጨዋቿን አጣች!

አዲሱ ሙሽራ ማረፉ ተሰምቷል !

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ተጨዋች አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

በቅርቡ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በቤተክርስቲያን የፈፀመው አዲሱ ሙሽራ ድንገት ዛሬ ለሊት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል ።

ለአርባምንጭ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው፤ ለሀዋሳ ከተማና አሁን ለባህርዳር ከተማ በሊጉ የሚጫወተው አለልኝ አዘነ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ተደርጎለት አገልግሎት ሰጥቷል።

አመለ ሸጋው ተጨዋች አለልኝ አዘነ ላለፉት ሁለት አመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት ክለቡንና ሀገሩን እያገለገለ የሚገኝ ወጣት ተጨዋች ነበር።

ወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በአለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።

የወንድማችን ወንድሙ ቱርጋ የገቢ ማሰባሰቢያ ጎፈንድሚ ተከፍቷል። የምትችሉትን ድጋፋችሁ እንድታደርጉለት እንጠይቃለን።
09/03/2024

የወንድማችን ወንድሙ ቱርጋ የገቢ ማሰባሰቢያ ጎፈንድሚ ተከፍቷል። የምትችሉትን ድጋፋችሁ እንድታደርጉለት እንጠይቃለን።

ወጣቱ ወንድማችንን እንታደግ ወጣት ስፖርተኛ ወንድማችን ወንድሙ ቱርጋ ከልጅነቱ እስከ ዕውቀቱ በወልቂጤ ከተማ ቅርጫት ኳስ ቡድን ውስጥ ሲ… Hunlachew Sebgaze needs your support for ለወጣት ስፓስተኛ .....

ባለዉለታዉ ወጣት ወንድሙ ቱርጋ ሁሉም ይድረሰለት!! ወጣት ስፖርተኛ  ወንድማችን ወንድሙ ቱርጋ ከልጅነቱ እስከ ዕውቀቱ በወልቂጤ ከተማ ቅርጫት ኳስ ቡድን ውስጥ ሲጫወት የነበረ ሲሆን በነበረው...
08/03/2024

ባለዉለታዉ ወጣት ወንድሙ ቱርጋ ሁሉም ይድረሰለት!!

ወጣት ስፖርተኛ ወንድማችን ወንድሙ ቱርጋ ከልጅነቱ እስከ ዕውቀቱ በወልቂጤ ከተማ ቅርጫት ኳስ ቡድን ውስጥ ሲጫወት የነበረ ሲሆን በነበረው ከፍተኛ አቅም ጉራጌ ዞንን፣ የቀድሞው ደቡብ ክልልን እና የኢትዮጲያ ብሄራዊ ቡድን ቅርጫት ኳስ በመወከል ህዝብንና ሀገሩን ሲያገለግል ቆይቷል፡፡

በተጨማሪም ታዳጊ ልጆችን ተተኪ ለማፍራት ሲያሰለጥን ነበር፡፡
ነገር ግን በልምምድ በነበረበት ወቅት በደረሰበት ጉዳት ምክንያት የቀኝ እጁ ታሞ ላለፉት አራት አመታት ሲንገላታና ያለውን አሟጦ 300 000 ብር በቤተሰቡ ወጪ በማድረግ ህክምናውን እየተከታተለ ቢቆይም የእጁ ጉዳት ከባድ ደረጃ ላይ በመድረሱ ነርቩ የተጎዳ በመሆኑ አሁን ላይ ከባድ የነርቭ ህክምና እየተደረገለት ይገኛል፡፡

ስለሆነም አሁን ላይ በሀገር ውስጥ ህክምና የመጨረሻው ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን በሳምንት 40,000 ብር የህክምና ወጪ እያወጣ ሲሆን ህክምናውም በፍጥነት ማገኝት ስለሚኖርበት ለህክምናው ከ 3,000,000 ብር ( ሶስት ሚሊዮን ብር) በላይ ስለሚያስፈልገን ይህ ወጪ ደግሞ በቤተሰቡ አቅም ሊሸፈን የማይችል በመሆኑ በፍጥነት ማግኝት አለበት፡፡

ህክምና ማግኝት ካልቻለ ህይወቱ ላይ አደጋ ሊያስከትልበት እንደሚችል ሀኪሞች ያሳወቁን ሲሆን ህይወቱን ለመታደግ የእርሶን እርዳታ ስለ ሚያስፈልገን ድጋፍ እንዲያደርጉልን ስንል በፈጣሪ ስም እንለምኖታለን።

መርዳት የምትፈልጉ በኮሚቴዎች በተከፈቱ አካዉንቶች ድጋፍ አድርጉ።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000612297677
ወይም
አቢሲንያ ባንክ 179112 345

( በአስተባባሪ ኮሚቴ አካዉንት የተከፈተ ነዉና ሁሉም ይደግፈዉ ይህ ብርቱ ወጣት ትልቀ ባለዉለታችን ነዉ።

ስልክ
0920960849 ( ሌክሲ ቱርጋ )
+251911398020 ( ባሀሩ ተካ)
+251920967710 (ዘመዴ በቀሉ)

ሰጪ እጆች በፈጣሪ ዘንድ ትልቅ ቦታ አላቸዉ።

ኑሬ ረጋሳ

ክለቡ ከውጤት ደረጃ እና ከደጋፊው ልብ ውስጥ እየሸሸ እና እየወረደ እንዳይሄድ ልንታደገው ይገባል።ከዚህ በፊት ባሳለፍናቸው የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ታሪክ  ውስጥ በፌክ ፌስቡክ  አካ...
07/03/2024

ክለቡ ከውጤት ደረጃ እና ከደጋፊው ልብ ውስጥ እየሸሸ እና እየወረደ እንዳይሄድ ልንታደገው ይገባል።

ከዚህ በፊት ባሳለፍናቸው የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ታሪክ ውስጥ በፌክ ፌስቡክ አካውንት ጋጋታ ፤ ስድብ ፤ ወከባ ፤ ጠርዝ በሌለው ወቀሳ...ይወከብ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።ነገር ግን ያ ሁሉ ልክ ያልሆኑ ኢ ሥነ ምግባራዊ ነገሮች ዛሬ ላይ አንዳቸውም የሉም።።ምክንያቱ ደግሞ ግልፅ ነው.......ይህ ማለት ክለቡን ለሚመሩት አካሎች ተረጋግተው እንዲመሩ ዕድል የሰጠ ነው።

አሁን ላይ ክለቡ በሁለት መንገዶች ችግር ውስጥ ነው ።አንደኛ በውድድሩ ውስጥ ካለው ደረጃ መውረድ ሁለተኛ ደግሞ በደጋፊው ልብ ውስጥ ካለው ደረጃ መውረድ ነው።
በሁለቱ መንገዶች ችግር ውስጥ ነው ሊባል ይችላል።

ክለቡ ከሌላው ጊዜ በተሻለ ከክልል እስከ ዞን ባሉ የመንግስት አካላት እየታገዘ እና እየተደገፈ ቢገኝም ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት የውጤት ቀውስ ውስጥ እንዲገባ ሆኗል።

መታወቅ ያለበት ዘንድሮ ከብዙ ክለቦች በተሻለ ወልቂጤ ለተጫዋቾች ደሞዝ ይከፍላል። ነገር ግን ከውጤት ቀውስ መውጣት አልቻለም።

ታድያ ችግሩ ምኑ ጋር ነው ??መፍትሔውስ ምንድነው??? ማንን ነው የምንጠይቀው ??ማንንስ ነው የምንወቅስው?? ከማን ጋር እንነጋገር?????????? የሚሉ ጥያቄዎች እየበዙ በመምጣታቸው ክለቡን የሚመሩት አካላት ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ መስጠት እና ለክለቡም መፍትሔ ሊሰጡት ይገባል።

ኢትዮጵያ በመሠረተችው የአፍሪካ እግር ኳስ መሪነት ክብሯ ለመመለስ መልካሙ እርምጃ ኢትዮጵያ የአፍሪካ እግር ኳስ መስራች ሆና ወደ ፊት የመጣች ቀዳሚት ሐገር ብትሆንም ላለፉት አስርት አመታት ...
14/02/2024

ኢትዮጵያ በመሠረተችው የአፍሪካ እግር ኳስ መሪነት ክብሯ ለመመለስ መልካሙ እርምጃ

ኢትዮጵያ የአፍሪካ እግር ኳስ መስራች ሆና ወደ ፊት የመጣች ቀዳሚት ሐገር ብትሆንም ላለፉት አስርት አመታት ከሜዳ ውስጥ ሆነ ከሜዳ ውጭ ይህንን መሪነቷን ማስቀጠል አልቻለችም ።

በቅርብ ዓመታት ውስጥ በእግር ኳሱ በኢንተርናሽናል አልቢተሮቿ ባሞላክ ተሰማ እና ሊዲያ ታፈሰ እንዲሁም በኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በኳሱ በተሻለ ሁኔታ ለመጠራት በቅታለች።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን እንደ ተቋም መልካም የሚባል እድገትን ማሳየት የቻሉት አቶ ኢሳያስ ጅራ የካፍ የስራአስፈፃሚ አባል መሆን በቅርብ በእግር ኳሱ መሪነት እንደሐገር ከተገኙ የመሪነት ቦታወች መልካሙ ዜና ሆኗል ።

በእግር ኳሱ የእርስ በእርስ ግንኙነት ስራወች ላይ መልካም ተሞክሮን ማሳካት የቻሉት የፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት የስራአስፈፃሚ አባል መሆናቸው ለሐገራችን እግር ኳስ ጥሩ ተሞክሮ እና ከሌሎች ጋር አብሮ የመስራት እድልን እንደሚያጎናፅፍ ተስፋ እናደርጋለን ።

እንኳን ደስ አልዎት አቶ ኢሳያስ ጅራ

07/02/2024
ጥር 22/2016 ዓ.ምየወልቂጤ እግር ኳስ ስፖርት ክለብ ህዝባዊ መሰረት በማስያዝ ክለቡ በሀገርና በአለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን በሚደረገው ጥረት ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ተ...
31/01/2024

ጥር 22/2016 ዓ.ም
የወልቂጤ እግር ኳስ ስፖርት ክለብ ህዝባዊ መሰረት በማስያዝ ክለቡ በሀገርና በአለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን በሚደረገው ጥረት ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ተጠየቀ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው የወልቂጤ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ህዝባዊ መሰረት ለማስያዝ ብሎም ያለበትን የፋይናንስ እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

አቶ እንዳለ ስጦታው በመግለጫቸውም የወልቂጤ እግር ኳስ ስፖርት ክለብ በ2012 ዓ.ም ወደ ፕሪምየር ሊግ ከተቀላቀለ ጊዜ ጀምሮ በተለያየ ምክንያት ህዝባዊ መሰረት ሳይዝ ቆይቷል።

ከዚህ በፊት ስፖርት ክለቡ በመንግስት ሀብት የሚመራ እንደነበር ጠቅሰው ህብረተሰቡ የሚጠይቃቸው በርካታ የመሰረተ ልማት ጥያቄ መኖሩን ተከትሎ ስፖርት ክለቡ ህዝባዊ መሰረት በማስያዝ ስፖርቱና ልማቱ ጎን ለጎን ማሳለጥ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

ለዚህም ክለቡ ህዝባዊ መሰረት ለማስያዝ የፊታችን ሰኞ በቀን 27/2016 ዓ.ም ተወላጅ ባለሀብቶች፣ በሀገርና በአለም አቀፍ የሚኖሩ ባለሀብቶችን በማስተባበር የሀብት አሰባሰብ ስራ በስካላይት ሆቴል በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የሚመራ መድረክ ተዘጋጅቷል።

በዚህም መድረክ ጥሪ የተደረገላቸው ሚኒስቴሮች፣ ባለሀብቶች፣ ተወላጅ ባለሀብቶች እና መላው የስፖርቱ ደጋፊ ማህበረሰብ የሚችሉትን አስተዋጽኦ በማድረግ ክለቡ ከገጠመው የፋይናንሺያል እጥረት ችግር ለማላቀቅ እንዲቻል ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነም አቶ እንዳለ አንስተዋል።

በሀብት ማሰባሰብ ስራውም ከ250 በላይ ባለሀብቶች እንደሚገኙ የጠቀሱት ከንቲባው በዚህም ከ60 እስከ 80 ሚሊዮን ብር ይሰበሰባል ተብሎ እንደታቀደም በመግለጽ።

የማህበረሰቡ አርማ የሆነው የወልቂጤ እግር ኳስ ስፖርት ክለብ አሁን ላይ ያለበትን ፋይናንሺያል እጥረት በዘላቂነት በመፍታት ዘላቂ የሆነ የገቢ አማራጮችን በመጠቀም ክለቡ ህዝባዊ ቅቡልነት እንዲኖረው በማድረግ በሀገርና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማስቻል ነው።

መንግስት ያለውን ውስን ሀብት በመጠቀም ስፖርቱና ልማት ጎን ለጎን ለማሳለጥ ክለቡ ህዝባዊ መሰረት ለማስያዝ በሚደረገው ጥረት ባለሀብቱ፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ ነዋሪውና ሲቪል ሰርቫንቱ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

ከዚህም ባለፈ የወልቂጤ እግር ኳስ ስፖርት ክለብ ብቻ ሳይሆን የዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ፣ ቅርጫት ኳስ እና በተለያየ መልኩ የተደራጁ ታዳጊ ስፖርት ቡድኖች ሁሉ ከመንግስት ሀብት የሚፈልጉ በመሆናቸው እነዚህን በስፖርት ጽህፈት ቤት ተደራጅተው ህዝባዊ መሰረት እንዲኖራቸው በማድረግ መንግስት ከሚመድበው ውስን በጀት ባለፈ ዘላቂ በሆነ መልኩ ስፖርቱ መምራት እንዲቻል በተለያዩ አማራጮች ገቢ የማሰባሰብ ስራ ለመስራት ታቅዷል።

በመሆኑም ይህ እንዲሳካ ሁሉም የንግዱ ማህበረሰብ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የክለቡ ደጋፊና ወዳጆች ተሳትፎ እንዲያደርጉም አቶ እንዳለ አሳስበዋል።

28/12/2023

መቶ ብር ለአምባሳደሬ" #
የወልቂጤ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ሰራተኞቹ የገጠመወን የፋይናንስ ችግር ለመቅረፍ በዞኑ ውስጥ እና በሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ የስፖርቱን ቤተሰብ በየወሩ የመንግስት ሰራተኛው፤ ወጣቱ እና የስፖርት ቤተሰቡ በሙሉ ይህን # በመቀላቀል አባሳደራችንን እንታደግ
አዲስ አበባ፤ ሃዋሳ ድሬዳዋ፤ በወልቂጤ፤ በእዣ፤ በቸሀ፤ በጉመር፤ በጌቶ፤ በእነሞር፤ በኤነር፤ በእነደጋኝ ፤በሙህር፤ በኮኪር ገደባኖ የምትገኙ የመንግስት ሰራተኛው፤ ወጣቱ እና የስፖርት ቤተሰቡ በየወረዳው በሚቋቋሙ ተወካዮች አማካኝነት ይህን ታሪካዊ # በመቀላቀል ሰራተኞቹን እንታደግ !!!!!!!!
1000026889271
Welkite eger kwase club

14/12/2023

የሙሉ ሰአት ውጤት
ወልቂጤ 0 ___ 2 መቻል

Address

WOLKITE
Wolkite

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolkite City Sport Club posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share