Tuba football club - TFC

Tuba football club - TFC ወደፊት

ወልቂጤ ከተማ ወደነበርኩበት ፕሪሚየር ሊግ ልመለስ ይገባኛል ሲል ጠየቀJuly 4, 2025 ቴዎድሮስ ታከለየ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት ላይ በደመወዝ ጥያቄ ...
04/07/2025

ወልቂጤ ከተማ ወደነበርኩበት ፕሪሚየር ሊግ ልመለስ ይገባኛል ሲል ጠየቀ

July 4, 2025

ቴዎድሮስ ታከለ

የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት ላይ በደመወዝ ጥያቄ ከሊጉ የተሰረዘው ወልቂጤ በቀጣዩ የ2018 የውድድር ዘመን ልመለስ ይገኛል ሲል በደብዳቤ ጠይቋል።



በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ለመሳተፍ ቅድመ ዝግጅቶችን ካደረገ በኋላ ለውድድር ወደ ድሬዳዋ ቢያመራም በክለቡ የተለያዩ ክሶች እና ውዝፍ የደመወዝ ክፍያዎች ስለነበሩበት በመጨረሻም ከተከታታይ የፎርፌ ውጤቶች በኋላ ከሀገሪቱ ከፍተኛው የሊግ ዕርከን ወርዶ በከፍተኛ ሊጉ ቆይታ ቢኖረውም የኋላ ኋላ ግን በመጨረሻም ወደ አንደኛ ሊግ መውረዱ ይታወሳል ፣ ይሁን እንጂ ከሰሞኑ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ እየታዩ ከሚገኙ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ክለቡ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ልመለስ ይገባኛል ሲል በተከታዩ ደብዳቤ ሀሳቡን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቁሟል።



ሙሉው የደብዳቤው ሀሳብ 👇

“በኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2017 ዓ.ም የውድድር ዘመን ክለቦችን የሚያስተዳድርበት ስርአት ከፍ ለማድረግ የክለብ ላይሰሲንግ መመሪያ በማውጣት ከምዝገባ ጀምሮ ክለቦች የዝውውርና የውድድር ፍቃድ የሚያገኙበት ስርአት ዘርግቶ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለሚካፈሉ ክለቦች በ5 መሰረታዊ መስፈርቶች ስር ዝርዝር መስፈርቶች ከቅጣት ማእቀፎች ጋር በማውጣት ምዝገባ ያከናወነ ሲሆን የወልቂጤ ከተማ እግር ካስ ክለብ ግን የደመወዝ ውዝፍ እዳ ስላለብን መስፈርቱን በወቅቱ ባለሟሟላታችን የውድድር ፍቃድ ባለማግኘታችን እንወዳደርበት ከነበረው ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ባስተዳደራዊ ውሳኔ ወደ ከፈተኛ ሊግ ወርደን እንድንሳተፍ ኢ ፍትሀዊ የሆነ ውሳኔ ተላልፎብናል፡፡

ሆኖም ክለባችን ውዝፍ ደመወዝና እዳ ባለሟሟለላቱ በክለብ ላይስሲንግ መስፈረት መሰረት ማለትም፡- ‘ክለብ ከደመወዝና ሌሎች ውዝፍ እዳዎች ነፃ መሆን ይኖርበታል እስከ ቀነ ገደቡ መስከረም 8/2017/ድረስ ተግባራዊ ካልተደረገ የውድድር አመቱን 3 ነጥብ ተቀነሶበት የሚጀምር ይሆናል በተጨማሪም ምንም አይነት የተጫዋች ውል ማጽደቅ አይቻልም።’

በሚለው መስፈርት መሰረት የውድድር አመቱን ስንጀምር 3 ነጥብ ተቀንሶብን መጀመር ሲገባን ከክለብ ላይሰንሲንግ ፍቃድ እንዳልተሰጠን እየታወቀ ፕሮግራም አውጥቶ ፎርፌ መስጠት በእኛ በኩል ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በወቅቱ ብንገልፅም ሰሚ ሳነገኝ ቀርተን የሚጠበቅብን 641,000 ዶላር እና 12,000(አስራ ሁለት ሺ CHF/የስዊዝ ፍራንክ ከፍለን ወደ ከፍተኛ ሊግ ወርደን እንድንወዳደር ተደርጓል፡፡

በሌላ በኩል ሰሞኑን በተጫዋች ተግባቢነትና በፋይናንስ አጠቃቀም ዙሪያ በታዩ የአሰራር ግድፈቶች ምክንያት የፌዴሬሽን ዲሲፒሊን ኮሚቴ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ህጉን የጣሱ ክለቦች ከ2 ጨዋታ በላይ በፎርፌ ተሸናፊ ሆነው ሳለ ከሊጉ አይወርዱም ብሎ የፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መወሰኑን ከሰጡት መግለጫ መገንዘብ ችለናል፡፡ ታዲያ ይሄ ከሆነ የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ፎርፌ ተሰጥቶበታል ተብሎ ለምን እንዲወርድ ተደረገ? የሚለውን ጥያቄ አጭሮብናል። ስለዚህ ፌዴሬሽኑ ሁሉንም ክለቦች በአንድ አይን ተመልክቶ ክለባችን ወደ ነበረበት ፕሪሚየር ሊግ እንዲመለስ ተገቢውን ውሳኔ እንዲሰጠን እናመለክታለን፡፡”

5ተኛው የኬሮድ ሩጫ በወልቂጤ ዝ "🙏5ተኛው ኬሮድ የ15ኪሜ የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ሀምሌ 27 /2017 ለ5ኛ ጊዜ ይካሄዳል!!!
03/07/2025

5ተኛው የኬሮድ ሩጫ በወልቂጤ ዝ "🙏

5ተኛው ኬሮድ የ15ኪሜ የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ሀምሌ 27 /2017 ለ5ኛ ጊዜ ይካሄዳል!!!

Rip Diogo Jota
03/07/2025

Rip Diogo Jota

ማንም ማይወርድ ከሆነ ወልቂጤም ይመለስ።እነሱስ ፋይናንስ ህግ ጣሳቹ ተብለው አይደል የተቀጡት ነጥባቸዉ የተቀጡበት ጨወታ ላይ ቢቀነስ ወራጅ ናቸዉ  ? ስለዚ ወልቂጤም  የማቻቻል ውሳኔው ተጠቃ...
02/07/2025

ማንም ማይወርድ ከሆነ ወልቂጤም ይመለስ።እነሱስ ፋይናንስ ህግ ጣሳቹ ተብለው አይደል የተቀጡት ነጥባቸዉ የተቀጡበት ጨወታ ላይ ቢቀነስ ወራጅ ናቸዉ ? ስለዚ ወልቂጤም የማቻቻል ውሳኔው ተጠቃሚ መሆን አለበት።

?
ወልቂጤንም መልሱ ✊ በ20 ቡድን ብላቹ ወስናቹ የለ ስለዚ በ21 ይቀጥል ማለት ብዙም ኣይከብድም ። የእውነት ወልቂጤ በትክክለኛ ጠያቂ ደጋፊ ካለ ይህን እንጠይቅ ። እኛ ከማን እንለያለን ለምንድነዉ ምንወርደዉ ?? ህግ ሚሰራው እኛ ላይ ብቻ ነው ወይ ? እንጠይቃለን ። ማንም ኣይወርድም ከተባለ።እኛም ሊያጠቃልል ግዴታ ግዴታ ነዉ።

እንጠይቃለን????

04/05/2025
🧡
10/08/2023

🧡

 ኧረ ኡኡኡኡኡ እባካቹህ አመራሮቻችን ካርሎስ ዳምጠው አታስመልጡን ልጁ ያስፈልገናል ትልቅ አቅም አለው እባካቹ ይህ ውለታ እንኳን ዋሉልን እድሉ አሁንም በእጃችን ነው  ከሌላ ክለብ እየጨረሰ ...
09/08/2023



ኧረ ኡኡኡኡኡ እባካቹህ አመራሮቻችን ካርሎስ ዳምጠው አታስመልጡን ልጁ ያስፈልገናል ትልቅ አቅም አለው እባካቹ ይህ ውለታ እንኳን ዋሉልን እድሉ አሁንም በእጃችን ነው ከሌላ ክለብ እየጨረሰ ነው

Address

Jimma
Wolkite
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tuba football club - TFC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category