ወላይታ ዲቻ

ወላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ

15/03/2026
የወላይታ ሶዶ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ በይፋ ተጀመረ!   | ​"የወላይታን ባህልና ታሪክ የያዘ፣ ከ40 እስከ 45 ሺህ ተመልካች የሚይዝ ግዙፍ ስታዲየም" ​በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የወ...
27/01/2026

የወላይታ ሶዶ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ በይፋ ተጀመረ!

| ​"የወላይታን ባህልና ታሪክ የያዘ፣ ከ40 እስከ 45 ሺህ ተመልካች የሚይዝ ግዙፍ ስታዲየም" ​በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የወላይታ ሶዶ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ ዛሬ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ በባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ እና በወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ አማካኝነት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለታል።

​የስታዲየሙ ገፅታዎች:

✅ ደረጃ: የፊፋ (FIFA) እና የካፍ (CAF) ስታንዳርድን ያሟላ።

✅ አቅም: ከ40,000 እስከ 45,000 በላይ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም አለው።

✅ ዲዛይን: የወላይታን ህዝብ ታሪክ፣ ባህላዊ እሴቶች እና የአካባቢውን ገፅታ ያካተተ ነው።

✅ ይዞታ: በ51 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ይሆናል።

​ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፤ "ይህ ፕሮጀክት የህዝብ ነው፤ ከተባበርንና ካስተባበርን እውን ማድረግ ይቻላል" በማለት፤ የክልሉ መንግስት ለፕሮጀክቱ የሚሆን ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እንደሚያዘጋጅ ገልጸዋል።

​የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በበኩላቸው፤ "እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!" በማለት መላው ህዝብ አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ዎጌታ ኤፍ ኤም 96.6

የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ******************የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች የኢትዮጵያ ዋንጫ ለክለቡ እንዲመለስ መወሰኑን ተከትሎ ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡ክለ...
01/07/2025

የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ
******************

የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች የኢትዮጵያ ዋንጫ ለክለቡ እንዲመለስ መወሰኑን ተከትሎ ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

ክለቡን የሚገልጹ አርማዎችን ይዘው በመውጣት በወላይታ ሶዶ ከተማ ደስታቸውን በህብረት እየገለጹ ነው፡፡

ውሳኔውን አስመልክተው ለኢቢሲ አስተያየታቸውን የሰጡት የክለቡ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳንኤል ዳሌ፤ የእግር ኳስ ፌደሬሽን ቅሬታችንን ተቀብሎ ተገቢ ውሳኔ በማሳለፉ ተደስተናል ብለዋል፡፡

ይህንን ማድረግ የወላይታ ድቻን ቅሬታ መፍታት ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን እግር ኳስ የመታደግ እርምጃ ነው ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

ሲዳማ ቡና በአዲስ አበባ ስቴዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ድቻን 2 ለ 1 ቢያሸንፍም ዋንጫውን እንዲመልስ ተደርጓል፡፡

የኢትጵጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን እንዳስታወቀው ሲዳማ ቡና በፍጻሜው ጨዋታው ቅጣት የተጣለባቸው ተጫዋቾች መጠቀሙን ተከትሎ ነው ውጤቱ የተሰረዘበት፡፡

በተመስገን ተስፋዬ

01/07/2025

ለመላው የክለባችን ደጋፊ እንኮን ደስ አላቹ

83' ጎልብሩክ ማርቆስ (በራስ ላይ)(ወላይታ ድቻ 2-1 ሀዲያ ሆሳዕና)
16/06/2024

83' ጎል

ብሩክ ማርቆስ (በራስ ላይ)

(ወላይታ ድቻ 2-1 ሀዲያ ሆሳዕና)

75ወላይታ ድቻ 1-0 ሀምበርቾ45'+1 ቢኒያም ፍቅሩ
01/02/2024

75

ወላይታ ድቻ 1-0 ሀምበርቾ

45'+1 ቢኒያም ፍቅሩ

45'+1 ቢኒያም ፍቅሩ !(ወላይታ ድቻ 1-0 ሀምበርቾ)
01/02/2024

45'+1 ቢኒያም ፍቅሩ !

(ወላይታ ድቻ 1-0 ሀምበርቾ)

Address

Stadyme
Laftu
URL

Telephone

+251929567474

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወላይታ ዲቻ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ወላይታ ዲቻ:

Shortcuts

Share