Agare awateya

Agare awateya Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Agare awateya, Jimma.

የጨበራ ጩርጩራ ማራኪ ገጽታዎች ፣ ውብ መዳረሻ
10/08/2024

የጨበራ ጩርጩራ ማራኪ ገጽታዎች ፣ ውብ መዳረሻ

ትናንት በሪያል ማድሪድና ባየርን ሙኒክ መካከል በተካሄደው የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ላይ ለሙኒኮች ቅሬታ ምክንያት የሆነውና ቡዙዎችን ሲያነጋግር የነበረው ክስተት ምን ነበር?ባየርን ሙኒክ የማጥ...
09/05/2024

ትናንት በሪያል ማድሪድና ባየርን ሙኒክ መካከል በተካሄደው የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ላይ ለሙኒኮች ቅሬታ ምክንያት የሆነውና ቡዙዎችን ሲያነጋግር የነበረው ክስተት ምን ነበር?

ባየርን ሙኒክ የማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ እያለ የመሃል ዳኛው የመጀመሪያው ረዳት ዳኛን ባንዲራ ማንሳት አይቶ ጨዋታው እንዲቆም ፊሽካ ነፍቷል፤ ይኼም ማለት በመሀል ዳኛው ፊሽካ የቆመ የኳስ እንቅስቃሴ እንደገና ወደ እንቅስቃሴ የሚገባው በሌላ የመሀል ዳኛው ፊሽካ ነው!(በመሆኑም ከጨዋታ ማስቆሚያ ፊሽካ በኋላ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ በህጉ መሰረት ምንም አይነት ውጤት አይኖረውም)

ችግሩ የተፈጠረው የመጀመሪያው ረዳት ዳኛ እርግጠኛ ያልሆነበትን የOffside ጥሪ በተመለከተ ባንዲራ ሳያነሳ እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል ፈቅዶ ኳስ ከወጣ በኋላ ወይም ጎል ተቆጥሮም ከሆነ ከተቆጠረ በኋላ ባንዲራውን አንስቶ ቢሆን ኖሮ VAR ክፍል ያሉት ረዳት ዳኞች የSemi Automated Offside Technologyውን በመጠቀም የተቆጠረው ጎል ከጨዋታ ውጭ ስለመሆን አለመሆኑ እንዲወስኑ ማድረግ ይችል ነበር።

ከዚህ አንፃር ሪያል ማድሪድ ያስቆጠራት ሁለተኛ ጎል ከላይ በተባለው አግባብ ሁለተኛው የረዳት ዳኛ እንቅስቃሴው እንዲቀጥል ፈቅዶ ስለ እንቅስቃሴው አግባብነት በVAR እንዲወሰን መደረጉን ማስተዋል ያስፈልጋል። [4-3-3 sport]

ታሪካዊው የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በ26 አመት ከመንፈቅ የኦልድትራፎርድ ቆይታቸው የተለያዩ 38 ዋንጫዎችን ካሳኩ በኋላ ልክ በዛሬዋ እለት ከ11 አመት በፊት ነበ...
09/05/2024

ታሪካዊው የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በ26 አመት ከመንፈቅ የኦልድትራፎርድ ቆይታቸው የተለያዩ 38 ዋንጫዎችን ካሳኩ በኋላ ልክ በዛሬዋ እለት ከ11 አመት በፊት ነበር ቀያዮቹ ሰይጣኖችንና እግር ኳስን የተሰናበቱት።

09/05/2024
ኢትዮጵያ  የተወሰኑ ኤምባሲዎች በደቦ  የሚያወጧቸውን  መግለጫዎች  እንደማትቀበል ገለፀች --- ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተወሰኑ ኤምባሲዎች በደቦ  የሚያወጧቸውን  መግለጫዎች ...
09/05/2024

ኢትዮጵያ የተወሰኑ ኤምባሲዎች በደቦ የሚያወጧቸውን መግለጫዎች እንደማትቀበል ገለፀች
---
ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተወሰኑ ኤምባሲዎች በደቦ የሚያወጧቸውን መግለጫዎች ኢትዮጵያ እንደማትቀበል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ ዛሬ ግንቦት 01 ቀን 2016 ዓ.ም የሀገሪቱን አበይት የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎች አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን መደበኛ መግለጫ ሰጥተዋል ።

አቶ ነብዩ ተድላ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዲስ አበባ የሚገኙ የተወሰኑ ኤምባሲዎች በደቦ የሚያወጧቸው የጋራ መግለጫዎች ከተለመደው የዲፕሎማሲ አሰራር ያፈነገጡ መሆናቸውን ገልፀው ባለፈው ሳምንት የዓለም የፕሬስ ቀንን ምክንያት በማድረግ አንዳንድ ኤምባሲዎች በጋራ የሰጡት መግለጫም የዚሁ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል ። ኢትዮጵያ የደቦ መግለጫዎችን እንደማትቀበልም ገልጸዋል ።

የኢትዮጵያ መንግስት የፕሬስ ነጻነት እንዲከበር ጽኑ አቋም እንዳለውና ከአሁን በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የነባር እና አዳዲስ የዲጂታል ሚዲያዎች ቁጥር መስፋፋት የፕሬስ ነጻነት እያደገ መምጣቱን ያሳያል ብለዋል። ይህ መብት ሊከበር እና ሊጠበቅ የሚገባው በሕግ የበላይነት ማዕቀፍ ውስጥ እንደሆነም ተናግረዋል ።

3ኛው ክልል ዓቀፍ የ21ኛው ባህል ስፖርቶችና 17ኛው ባህል ፌስቲቫል ውድድር በዛሬው ዕለት ፍፃሜውን አግኝቷልበደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሸካ ዞን ማሻ ከተማ ''ባህልን በማወቅ ...
11/04/2024

3ኛው ክልል ዓቀፍ የ21ኛው ባህል ስፖርቶችና 17ኛው ባህል ፌስቲቫል ውድድር በዛሬው ዕለት ፍፃሜውን አግኝቷል

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሸካ ዞን ማሻ ከተማ ''ባህልን በማወቅ በብዙሃነት መኖር" በሚል መሪ ቃል ለተከታታይ ስድስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው 21ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድርና 17ኛው ባህል ፌስቲቫል በሸካ ዞን አሸናፊነት ተጠናቋል።

በማጠቃለያው ፕሮግራም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አህመድን አወል የባህል ስፖርቶች ውድድርና ባህል ፌስቲቫል የአሸናፊነትና ተሸናፊነት ሳይሆን የእህትማማችነት እና የወንድማማችነት እሴት ማንፀባረቂያ ነው ብለዋል።

ቢሮው በክልሉ ባህላዊ ስፖርቶች እንዲጎልብቱ እየሰራ ያለውን እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሁሉም ርብርብ ያሻል ሲሉም ገልጸዋል።

እንደ አቶ አህመድን ገለፃ እስካሁን በነበረው ቆይታ ስፖርታዊ ጨዋነትን ተላብሳችሁ በመጫወት ውድድሩ በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት ሆኖ እንዲጠናቀቅ ያደረጉ ስፖርተኞችን እንዲሁም ውድድሩ ከጅምሩ እስከፍፃሜው በሰላም እንዲጠናቀቅ ያደረጉ ፀጥታ አካላትንና የከተማው ህዝብ በቢሮ ስም አመስግነዋል።

ዘንድሮ በሸካ ዞን ማሻ ከተማ የተካሄደው ውድድር የክልሉ መንግስት እኩል ፍትሃዊነትና የጋራ ተጠቃሚነትን በትግባር ያሳየበት በመሆኑ ቀጣይ በሁሉም አከባቢዎች ተፈፃሚ ይሆናል ተብሏል።

ውድድሩ በክልሉ ያሉት ስፖርተኞች ባህላቸውን እና ታሪካቸውን ከማስተዋወቅ ባሻገርም ክልላዊ አንድነታቸውን ያጠናክሩበት አጋጣሚም ጭምር መሆኑን የክልሉ ባህል ስፖርቶች ፌደሬሽን ምክትል ፕረዝዳንት አቶ አፈወርቅ ዳና ተናግረዋል።

ከዚህ ውድድር ተመርጣችሁ ቀጣይ በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄደው ሀገር ዓቀፍ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሚትሆኑ ስፖርተኞች እንደከዚህ ቀደም አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ውድድሩን በማሸነፍ ክልላችንን እንዲታኮሩ ከባድ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል ብለዋል ።

የዘንድሮ ባህል ስፖርቶች ውድድርና ባህል ፌስቲቫል ውድድር ብሔር ብሔረሰቦች አንዱን የሌለውን ባህል እንድያውቅ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጠናከር ከማድረግም አልፎ በአከባቢው ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ፀጋ እንዲታወቅ ዕድል የፈጠረ መሆኑን የገለፁት የሸካ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተግባሩ እንዳሻው ናቸው።

በውድድሩ አጠቃላይ አሸናፍ ሸካ ዞን ሲሆን የጸባይ ዋንጫ ተሸላሚ ምዕራብ ኦሞ ሲሆን በባህል ትርኢት 1ኛ ካፋና ዳውሮ 2ኛ ሸካ ዞን 3ኛ ኮንታ ዞን በመሆን የዋንጫ ተሸልመዋል።

የተለያዩ ስፖርት ውድድርና ተሳትፎ የሜዳሊያ ሽልማት የበረከተ ሲሆን በዋንጫ ብዛት 1ኛ ሸካ 2ኛ ዳውሮ 3ኛ ካፋ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል።

በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ለውድድሩ ተሳታፊዎች፣በየደረጃው ለውድድሩ መሳካት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና አካላት የዋንጫና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

በስተመጨረሻም በአዲስ አበባ ከተማ ለሚካሄደው ሀገር ዓቀፍ 21ኛው ባህል ስፖርቶች ውድድርና ባህል ፌስቲቫል ላይ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎችን በመመልመልና የቀጣይ ዓመት የውድድሩ አዘጋጅ ለሆነው ኮንታ ዞን ስንደቅ ዓላማ ርክክብ በመደረግ መረሃ ግብሩ ተጠናቋል።

west communicatjon #

The eclipse of Arsenal
08/04/2024

The eclipse of Arsenal

1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ይከበራል።በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የጨረቃ ክትትል ኮሚቴ የረመዳን ወር 29ኛው ቀን ጀንበር ከጠለቀች በኋላ የጨረቃ ምልከታ አድርጓል።በዚህም ምሽት ላይ...
08/04/2024

1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ይከበራል።

በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የጨረቃ ክትትል ኮሚቴ የረመዳን ወር 29ኛው ቀን ጀንበር ከጠለቀች በኋላ የጨረቃ ምልከታ አድርጓል።

በዚህም ምሽት ላይ አዲስ ጨረቃ ባለመታየቷ ኢድ ከነገ በስቲያ ረቡዕ ሚያዚያ 2 2016 ይሆናል ብሏል።

የኢድ አልፈጥር የመጀመሪያ ቀን የሚወሰነው በሂጅራ አቆጣጠር 10ኛው ወር ወይም ሸዋል ወር መጀመሩን የሚያመላክት ጨረቃ መታየቷን ተከትሎ ነው።

Ain Amharic #

በነገው እለት ከፊል ወይም ሙሉ  የጸሀይ ግርዶሽ ወይም ሶላር ኢክሊፕስ በበርካታ የአለም ሀገራት እንደሚከስት ይጠበቃል።ሙሉ የጸሀይ ግርዶሹ የሚከሰተው በአሜሪካ ውስጥ በጠባብ ኮሪደር ሲሆን የ...
08/04/2024

በነገው እለት ከፊል ወይም ሙሉ የጸሀይ ግርዶሽ ወይም ሶላር ኢክሊፕስ በበርካታ የአለም ሀገራት እንደሚከስት ይጠበቃል።

ሙሉ የጸሀይ ግርዶሹ የሚከሰተው በአሜሪካ ውስጥ በጠባብ ኮሪደር ሲሆን የተወሰኑ የአውሮፓ ሀገራትም ከፊል ግርዶች እንደሚታይባቸው ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።

ጸሀይ በጨረቃ ሙሉ በሙሉ ስትጋረድ የተወሰነው የሰሜን አሜሪካ ክፍል ሙሉ በሙሉ በጨለማ ይዋጣል። ጨረቃ በጸሀይ ስትሸፈን የሚያሳየውን ድንቅ ክስተት በሜክሲኮ ፖስፊክ ጠረፍ ያሉ በአስር ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይመለከቱታል ተብሏል።
Ain Amharic #

VAR checking possible offsides
07/04/2024

VAR checking possible offsides

Address

Jimma

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Agare awateya posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share