በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ማህበር/UoG Fasil Kenema F.C Supp Assoc

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ማህበር/UoG Fasil Kenema F.C Supp Assoc

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ማህበር/UoG Fasil Kenema F.C Supp Assoc Official page for the University of Gondar Fasil kenema football Club supporters associatio

🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹 #7ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ             ➖➖➖🌟➖➖➖  🗓 ቅዳሜ ታኅሳስ 13 ቀን 2011⌚️09:00   🆚     🔴               ...
21/12/2018

🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹
#7ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
➖➖➖🌟➖➖➖
🗓 ቅዳሜ ታኅሳስ 13 ቀን 2011
⌚️09:00
🆚 🔴
🏟 በሐረር ስታድየም🏟
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🔴🇦🇹 🇦🇹⚪️

🇦🇹  ⚽ ፋሲል ከነማ 🆚 መከላከያ ⚽📆 እሁድ ታኀሳስ 7/2011🕘 9:00⛳ በአጼ ፋሲለደስ ስታዲየም🏆 ድል ለአንጋፋውና ተወዳጁ ክለባችን🇦🇹   🇦🇹✧ በይፋዊ ገፃችን በቀጥታ👍 የጨዋታውን ውጤ...
14/12/2018

🇦🇹 ⚽ ፋሲል ከነማ 🆚 መከላከያ ⚽
📆 እሁድ ታኀሳስ 7/2011
🕘 9:00
⛳ በአጼ ፋሲለደስ ስታዲየም
🏆 ድል ለአንጋፋውና ተወዳጁ ክለባችን
🇦🇹 🇦🇹
✧ በይፋዊ ገፃችን በቀጥታ
👍 የጨዋታውን ውጤት ይገምቱ
💚💛❤"ድል ለአፄዎቹ"💚💛❤
🇦🇹 !!🇦🇹
ሊንኩን ተጭነው የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ
https://www.facebook.com/UoGFasilOfficial/?ref=bookmarks

ፋሲል ወልድያ ባህር ዳር ከነማ እንደ UA-07ለሶስት አስርት አመታት በቆየው በቀድሞው ፕሬዚደንት ሆስኒ ሞባረክ ዘመን ግብፃውያን በሀገሪቱ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ስነ ምህዳር የተ...
04/12/2018

ፋሲል ወልድያ ባህር ዳር ከነማ እንደ UA-07

ለሶስት አስርት አመታት በቆየው በቀድሞው ፕሬዚደንት ሆስኒ ሞባረክ ዘመን ግብፃውያን በሀገሪቱ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ስነ ምህዳር የተረገጠ ተሳትፎ ነበራቸው::ምድሪቱም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የምትተዳደር በሙስና የተዘፈቀ የመንግስት አሰራር ስራ ማግኘት ለወጣቱ የሚያስጨንቅበት ድህነት የተንሰራፋበት የህዝቡን ችግሮች የሚያሰሙና መንግስትን የሚቃወሙ የነፃነት ድምፆች የሚታፈኑበት የሚሰደዱበት ብሎም የሚገደሉባት ምድር ነበረች እንደግብፃውያን ሮሮ::
ህዝቡ ይህንን ጭቆና በነፃነት የሚያሰማበት ተቋም አልነበረውም::ይህ የመንግስት ግፍ እጅግ ሲበዛ ቀጥተኛ ያልሆነ ድምፁን የሚተነፍስበት እንደሃይማኖት ተቋማት ያሉ መንገዶችን ወለደ::ከዚያ ይልቅ ግን እግር ኳስ የአንበሳውን ድርሻ ወሰደ::
እ.ኤ.አ 2007 የመጀመሪያዎቹ የአንጋፋው አል አህሊ የእግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች የኮሌጅ ምሩቃን ሰራተኞች ከተለያየ ማህበራዊ እርከን እና ኃላፊነት የወጡ ወጣቶችን በማስተባበር Ultras Ahlawy UA-07 የተሰኘውን ራሱን በራሱ የሚያስተደድር የደጋፊዎች ህብረት አቋቋሙ::ጠንካራ ህብረት እና አደረጃጀት ያለው የAl Ahly sport club ደጋፊዎች ህብረት::
ከዚህ ማህበር መመስረት ማግስት የግብፅ እግር ኳስ በታሪኩ አይቶት የማያውቀውን ክስተት ማስተናገድ ጀመረ::የAl Ahly sport club ስታዲየም የህዝቡ ጥይቄ የሚዘመርበት የነፃነት ዜማዎች የሚዜሙበት እና የግብፅ አንድነት የሚሰበክበት መድረክ ሆነ::
የUA-07 አባላት በረዣዥም ህዝባዊ መዝሙሮች እና የነፃነት መፈክሮችን በማንገብ የተጨቆነው የግብፅ ህዝብ ድምፅ ሆነ::ከታዋቂ ሙፈክሮቹ መካከል:
እኛ አንድ ነን...በአንድነት ለዘላለም...ትከሻህን አስፋ አትፍራ አልትራ ነህና ...ህልውናችንን ተቀበል ካልሆነ ተቃውሞን ጠብቅ Respect Existence or Expect Resistance እኛ ግብፅ ነን!!! የሚሉት ይጠቀሱበታል::በሚያሳትሟቸውም የነፃነት ዜማ ሲዲዎችም በእያንዳንዱ ግብፃዊ ቤት እና ልብ ውስጥ መግባት ቻሉ::
ግብፅ አይኗን ወደ አዲሱ ትውልድ የነፃነት ድምፅ UA-07 አዞረች!የህዝቧ ፖለቲካዊ ማህበረሰባዊ እና ኢኮኖሚያዊ መንፈስ መነቃቃት ጀመረ!የህዝቡም ስነ ልቦና አንድ ወደ መሆን ገሰገሰ::
ከአረብ ሀገራት አብዮት በኃላ በፍርሃትና ፈተና ውስጥ ገብቶ የነበረው የሙባረክ መንግስት ይህንን ህብረት አሸባሪ አመፅኛ ዘራፊ የሚል ስያሜ በማውጣትና ማህበሩን ከመኖር ወደ አለመኖር መቀየር የሚችሉ ህግ እና ድንጋጌዎችን በማውጣት ማሳደድ ጀመር::
የአል አህሊ ደጋፊዎች ለእስር ስደት እና ሞት ተላልፈው መሰጠት ጀመሩ::ይሁን እንጂ የሙባረክ መንግሥት የደጋፊዎችን ህብረት ከመኖር ውደ አለመኖር መቀየር አልቻለም::
በመጨረሻም Feb -02 -2011 የግመል ትግል በተሰኘው በካይሮ አደባባይ በተደረገው ህዝባዊ አመፅ የአንበሰውን ድርሻ በመውስድ 3 ደጋፊዎችን ሰውቶ ብዙዎች ለአካል ጉዳት ተዳርገው ካይሮን ነፃ አወጣ::ከሙባረክ መውደቅ በኃላ የቀድሞው ስርዓት በነበረባቸው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አብዮታዊ ሰልፎችን በማስተባበርና በመምራት የግብፅ መሉ በሙሉ ነፃ መውጣት እሙን አደረገ::
ብዙዎች UA-07 ግብፅን መልሶ መገንባት የሚችለው የፖለቲካ ንቃተ ህሊና ያለው የአዲሱ ትውልድ ተምሳሌት እንደሄነ ይስማማሉ::
ዛሬም ድረስ የነፃነት መፈክሮቹ በታስዲየም ግድግዳዎች እና በካይሮ ጉዳናዎች ይነበባሉ::
እንደብረት ግብፅን ቀጥቅጦ የገዛው የሙባረክን ፈርዖናዊ አገዛዝ በድፍረት የተቃወመ ህብረት!!

ፋሲል ወልድያ ባህር ዳር ከነማ እንደ UA-07

ከሙባረክ የሚበልጥ እዚህ በኢትዮጽያ ምድር አለ::ዘርን መርጦ የሚገድል ዘርን መርጦ የሚያሳድድ ዘርን መርጦ የሚጨቁን ህዝብን መርጦ በድህነት የገደለ ህዝብን መርጦ ለማጥፋት ስልጣን የያዘ እና 27 አመት የታተረ!! TPLF!

ለረዥም ጊዜ በአስከፊ ድህነት መገፋት የጅምላ እልቂት መሰደድ መናቅ እና መረገጥ ውስጥ የነበረው የአማራ ህዝብ የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ከዕለታት አንድ ቀን ፍሬ ማፍራት ጀመረ:: የከተማዎቹ ክለቦች ወጣቱን መሰብሰብ ጀመሩ::ክለቦቹን ለመደገፍ የተሰበሰበው የጭቁን ህዝብ ልጆችም ለረጅም ጊዜ ታፍኖ የነበረውን ድምፃቸውን በየጨዋታው ማሰማት ጀመሩ::ህዝባዊ የነፃነት ጥያቄዎች ይዘመሩ ጀመር::
አማራ አይኑን ወደ ልጆቹ አደረገ::ጠላት ስልታዊ በሆነ መንገድ ከከተተው ድባቴ መውጣትና መንቃት እና መነቃቃት ጀመር::ከረጅም ጊዜ በኃላ በፕሪሚየር ሊግ ተሳትፏቸው ለተጨቆነው እና ሞት ለተደገሰበት የአማራው ህዝብ የነፃነት ድምፅ ሆኑት!!
ገደልኩት ቀበርኩት ያለው አማራ ሞት እንዳልያዘው ጠላት ተመለከተ::በታትኘዋለው ያለው አማራ አንድ ሆኖ መዘመር ጀመር::እግር ኳሱን ተዋሃደበት አማራዊ ስነ ልቦናን ደግም ገነባበት:: ይህ ለጠላት ራስ ምታት ነበር በተለያየ መንገድ ክለቦቹን እና ደጋፊዎቹን ለማዳከም እና ለመቆጣጠር ዘመተ:: እጅ የሚሰጥ አልተገኘም የክለቡ መለያዎች የሚያስደብድቡ የሚያሳስሩ በጠላትነትየሚያስፈርጁ ነበሩ አሁንም ድረስ መለዮውን ለብሰህ በነፃነት የማትሄድበት ክልሎች አሉ::
አማራው እንደህዝብ የደረሰበትን የሚጮህበት የሚናገርበት ሚዲያ ሳይኖረው የህዝብ ማዲያ ሆኑለት!!
ስቴዲየሞቹ አማራ አማራ አማራ!!!! የሚል የመኖር ዜማ
የሉም ጠፍተዋል ላሉት የሚሰሙበት የትግል ስፍራዎች ሆኑ!!
አማራን ነፃ በማውጣት እና መልሶ በመገንባት ታላቅ ሚናን ተጫዎቱ!!!
አማራ ባለበት አሁን እነርሱም አሉ!!
የአማራ ህዝብ የነፃነት ልሳኖች !!
ፋሲል ወልዲያ ባህር ዳር ከነማ!!
በአንድነት ለዘላለም!!!

ማሳሰቢያ

1.የክለቦች አመራሮች አማራዊ ስነ ልቦና ባላቸው ሰወች መያዝ አለበት
2. ክለቦቹ በውስጣቸው ያሉትንየአማራን ትንሳኤ ከማይሹ አማራነታቸው በሆድ የሸጡ ባንዳ ሰዎችን ማፅዳት አለባቸዉ
3.ሌሎች ፕሪሚየር ሊግ ያተቀላቀሉ የአማራ ከተማ
ክለቦች ሙያዊ የገንዘብ ድጋፍ እና ሌሎች
ማድረግ ይኖርባቸዋል
4.የክለቦቹ ደጋፊዎች ህብረት ህዝቡን የማንቃት
ስራውን መቀጠል ይኖርበታል

የአማራ ወጣቶች ማህበር በጎንደር /ዘሚካኤል/

 _____________________________________የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በ25 አገር አቋራጭ አውቶብሶች እና በአውሮፕላን ወደ ጎንደር ይጓዛሉ፡፡በሳምንቱ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረ...
30/11/2018


_____________________________________
የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በ25 አገር አቋራጭ አውቶብሶች እና በአውሮፕላን ወደ ጎንደር ይጓዛሉ፡፡
በሳምንቱ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ከሚስቡ አጀንዳዎች መሀከል የፋሲል ከነማና የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ፍቅር በጥንታዊ የኢትዮጵያ መናገሻ ከተማ እማማ ጎንደር ላይ የሚደምቁበት ትልቁ የኳስ ድግስ ነው፡፡
የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ማህበር የኢትዮጵያ ቡናን ደጋፊዎች ቅዳሜ አመሻሽ ጎንደር ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ሙሽራዋ ጎንደር ልጆቿን (እንግዶቿን ) የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች እንኳን በደህና መጣችሁ ቤት ለቦሳ ብላ ለመቀበል ዝግጅቷን አጠናቃለች፡፡

🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹  አስኪያጂ ቀጠረ👉ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ከቀድሞ ስራ አስኪያጁ አቶ ጌታሁን ስዩም ጋር ከተለያየ በኋላ ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር...
07/11/2018

🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹
አስኪያጂ ቀጠረ
👉ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ከቀድሞ ስራ አስኪያጁ አቶ ጌታሁን ስዩም ጋር ከተለያየ በኋላ ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ኢንስትራክተር ፍሰሃ አገኘሁን ለፋሲል ከነማ በዋና ስራ አስኪያጅነት እንዲያገለግሉ ሹሟል።
-
ኢንስትራክተር ፋሰሃ አገኘው በጎንደር ዩኒቨርስቲ በስፖርት ትምህርት ክፍል በመምህርነት ያገለገሉ ሲሆን ፒ.ኤች.ዲ ስኮላር፣ ኤም.ኤስ.ሲ በእግር ኳስ አሰልጣኝነት አ/አ ዩኒቨርስቲ፣ ኤም.ኤ በካውንሲሊን ሳይኮሎጅ አ/አ ዩኒቨርስቲ፣ በእግር ኳስ 'A' ላይሰንስ፣ የካፍ የሀገር ውስጥ ኢንስትራክተር፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ እና ልማት ኮሚቴ አባል ናቸው።
-
ኢንስትራክተር ፍሰሃ አገኘሁ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፈዴሬሽን የትምህርትና ስልጠና የብሔራዊ ቡድኖች፣ የፕሮጀክቶች ኃላፊ፣ የወጣቶችና ስፖርት ከፍተኛ ኤክስፐርት፣ የጎንደረር ዩኒቨርስቲ አስተማሪ፣ ዳሽን ቢራ እግር ኳስ ክለብ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ሲቀላቀል ቴክኒክ ዳይሬክተር፣ የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ የቀድሞ ተጨዋቾች፣ ከ1990 ዓ/ም ጀምረው የነፃ አገልግሎት በመስጠት በሱፐር ሊግ ቴክኒክ ዳይሬክተር፣ የመቀሌ እግር ኳስ ክለብ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ሲቀላቀል የቴክኒክ ዳይሬክተር፣ የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የአማራ ክልል ሻምፒዮን ሲሆን አማካሪ፣ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን በበርካታ ክለቦችና ተቋማት አመርቂ ስራ በመስራት አገልግለዋል።
-
ኢንስትራክተር ፍሰሃ አገኘሁ የኢትዮጵያ ስፖርት ናሽናል አካዳሚ ፕሮጀክት፣ የመላው ኢትዮጵያ ስፖርት ጨዋታዎች የጥናት ሰነድ፣ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ታዳጊዎች ልማት ጥናት፣ የኢትዮጵያ ስፖርት ፖሊሲ መተርጎሚያ ሰነድ፣ የብሔራዊ ሊግ የውድድር ፎርማት ሰነድ፣ የኢትዮጵያ ስፖርት ውድድሮች የጥናት ሰነዶችን አዘጋጅተዋል።
-
ኢንስትራክተር ፍሰሃ አገኘሁ በክለባችንና በደጋፊዎቻችን ስም ወደ ተወዳጁ ክለባችን እንኳን በደህና መጡ እያልን መልካም የስራ ጊዜ እንመኛለን።
- # እንኳን_ደህና_መጡ🇦🇹 # ፋሲል_ከነማ_ከክለብም በላይ ነው #
# ለደጋፊዎች_መረጃ_እንዲደርስ_ላይክ_Like_ኮመን
ት_Comment_ሼር_Share_ያድርጉ🇦🇹🇦🇹🇦🇹

    ⚽ ፋሲል ከነማ 🆚 ሀዋሳ ከነማ ⚽ 📆 ነገ እሁድ ጥቅምት 25/2011🕘 9:00⛳ በአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን አራት የመግቢያ በሮች ይኖሩታል1.ክቡር ትሪቡን በር ቁጥር 1 ...
03/11/2018


⚽ ፋሲል ከነማ 🆚 ሀዋሳ ከነማ ⚽
📆 ነገ እሁድ ጥቅምት 25/2011🕘 9:00
⛳ በአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን አራት የመግቢያ በሮች ይኖሩታል
1.ክቡር ትሪቡን በር ቁጥር 1 ሲሆን የመግቢያ ዋጋውም #50ብር ሁኗል የመግቢያ በሩም በተለመደው ዋና በር ብቻ ይሆናል፡፡
2. ዞብል በር ቁጥር 2 ሲሆን የመግቢያ ዋጋውም #20ብር ሁኗል የመግቢያ በሩም ካሁን በፊት በነበረው በር ብቻ ይሆናል፡፡
3. ቋራ በር ቁጥር 3 ሲሆን የመግቢያ ዋጋውም #20ብር ሁኗል የመግቢያ በሩም ከቋራ ጀርባ ባለው በዞብልና በቋራ መካከል ባለው በር ብቻ ይሆናል፡፡
4. ምንትዋብ በር ቁጥር 4 ሲሆን የመግቢያ ዋጋውም #5ብር ሁኗል የመግቢያ በሩም በቋራና በምንትዋብ መሀል በሚገኘውካሁን በር ብቻ ይሆናል፡፡
ስለዚህ ሁሉም የክለባችን ደጋፊዎች በተጠቀሱት በሮች በቻ የምትስተናገዱ መሆኑን እናሳወሸቃለን፡፡
🏆 ድል ለአንጋፋውና ተወዳጁ ክለባችን
🇦🇹 🇦🇹
✧ ማሳሰቢያ በቋራና በክቡር ትሪቡን የምትገቡ ደጋፊዎች ለሜዳችን ድምቀት ግዴታ የክለቡን ማሊያ በመልበስ የሜዳው ድምቀት እንድንሆን እና ሙሉ ጨዋታው እስኪጠናቀቅ በማያቋርጥ ድጋፍ ክለባችን እንደግፋለን፡፡
💚💛❤"ድል ለአፄዎቹ"💚💛❤
🇦🇹 !!🇦🇹

የኢትዮጵያ_ፕሪሚየር_ሊግ_የ2ኛ_ሳምንት_ጨዋታ 🇨🇬🇦🇹🇨🇬🇦🇹🇨🇬🇦🇹🇨🇬🇦🇹🇨🇬🇦🇹🇨🇬🇦🇹🇨🇬🇦🇹🇨🇬🇦🇹 ⚽ ፋሲል ከነማ 🆚 ሀዋሳ ከነማ ⚽📆 እሁድ ጥቅምት 25/2011🕘 9:00⛳ በአፄ ፋሲለደስ ስ...
31/10/2018

የኢትዮጵያ_ፕሪሚየር_ሊግ_የ2ኛ_ሳምንት_ጨዋታ 🇨🇬🇦🇹🇨🇬🇦🇹🇨🇬🇦🇹🇨🇬🇦🇹🇨🇬🇦🇹🇨🇬🇦🇹🇨🇬🇦🇹🇨🇬🇦🇹 ⚽ ፋሲል ከነማ 🆚 ሀዋሳ ከነማ ⚽
📆 እሁድ ጥቅምት 25/2011
🕘 9:00
⛳ በአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም
🏆 ድል ለአንጋፋውና ተወዳጁ ክለባችን
🇦🇹 🇦🇹
💚💛❤"ድል ለአፄዎቹ"💚💛❤
🇦🇹 !!🇦🇹

27/10/2018


ጨዋታው በሲዳማ ቡና አሸናፊነት ተጠናቀቀ
ሲዳማ ቡና 2 : 1 ፋሲል ከነማ
24′ ፀጋዬ ባልቻ
59′ አዲስ ግደይ
90' አዙካ ኢዙ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2011 አ.ም የመጀመሪያ ጨዋታ ወደ ሀዋሳ ያቀናው ተወዳጁ ክለባችን ፋሲል ከነማ የመጀመሪያ ጨዋታውን በሲዳማ ቡና የተሸነፈ ሲሆን በ2009 አም የሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ በተመሳሳይ በመክፈቻው ሲገናኙ ሲዳማ ቡና ማሸነፉ ይታወሳል በአጠቃላይ ለ5 ጊዜ ሲገናኙ ሲዳማ ቡና 4 ጊዜ ሲያሸንፍ ፋሲል ከነማ 1 ጊዜ ብቻ ማሸነፉ ይታወሳል፡፡ ሲዳማ ቡና አሁንም በፋሲል ከነማ ላይ የበላይነቱን ወስዷል፡፡

!!

 ሲዳማ ቡና ከ ፋሲል ከነማቅዳሜ ጥቅምት 17/2011 9:00በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳድል ለአንጋፋውና ተወዳጁ ክለባችን   !!!
22/10/2018


ሲዳማ ቡና ከ ፋሲል ከነማ
ቅዳሜ ጥቅምት 17/2011 9:00
በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ
ድል ለአንጋፋውና ተወዳጁ ክለባችን

!!!

🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹👉 ። #በክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ዛሬ ረፋድ 4:00 ላይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የአቋም መለኪያ የወዳጅነት ጨዋታ አድርጎ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል። #አ...
21/10/2018

🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹
👉 ።

#በክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ዛሬ ረፋድ 4:00 ላይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የአቋም መለኪያ የወዳጅነት ጨዋታ አድርጎ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

#አፄዎቹ ከብሄራዊ ቡድኑ የተመለሱትን 3 ተጫዋቾች ጨምሮ ያሬድ ፣ ሙጂብ ፣ ሳኛ እና ሰይድ በአማካኝ ክፍሉ ላይ ኤፍሬም ፣ ኩሊባሊና ሱራፌል እንዲሁም በአጥቂ ቦታ ግሪዳው ፣ ሽመክትና ኢዴን በመጠቀም በ4.3.3 አሰላለፍ ወደ ሜዳ ገብተዋል።

#በዚህ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ኳስን መስርቶ በመጫወት በታጋጣሚ ላይ የኳስ ቁጥጥር ብልጫን በመውሰድ እና ኳስ በታቃራኒ ቡድን ውስጥ ሲገባ በፍጥነት በመንጠቅ ምርጥ እንቅስቃሴ የነበረው ቢሆንም ወደ ጎል የሚሻሙና የሚሞከሩ ኳሶች ግን ውጤታማ ሲሆኑ አልተመለከትንም።

#ከእረፍት መልስ የመሃል ተከላካይ ክፍሉን ከያሬድ ጋር በመምራት ምርጥ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ሙጂብ ቃሲም በጉዳት በመጣባቸው ተቀይሮ ሲወጣ ኩሊባሊ ወደ ተካላካይ ቦታ ተመልሶ ከያሬድ ጋር መጣመር ችሏል።ከዚህ በተጨማሪ ያሳር ፣ ናትናኤል ፣ ለአለምብርሃን ፣ ፋሲል ፣ ኢዙ እና ፣ፍፁም በኤፍሬም ፣ ኢዴ ፣ ሱራፌል፣ ሰይድ ፣ ሽመክትና ግሪዳው ተቀይረው ወደ ሜዳ መግባት የቻሉ ሲሆን ተመጣጣኝ የሆነ እንቅስቃሴ መመልከት ችለናል።

#ጨዋታው ሊጠናቀቅ የተወሰኑ ደቂቃዎች ሲቀሩት ያሬድ ባዬህ ለሳማኪ ያቀበለውን ኳስ በአግባቡ ማውጣት ባለመቻሉ ጊዮርጊሶች ያገኙትን ኳስ በአዲሱ አጥቂ አማካኝነት አስቆጥረው ተሸንፈናል።

#ይህ ጨዋታ የወዳጅነት ጨዋታ በመሆኑ በቀጣይ ፕሪሚየር ሊጉ ላይ ስህተቶች ታርመው ፣ ክፍተቶች ተሞልተው ምርጡን እና በውጤት የታጀበው ፋሲል ከነማን እንደምንመለከት ሙሉ እምነት አለን።
🇦🇹ፋሲል ከነማ ከክለብም በላይ ነው።

 ተጠናቀቀ| ፋሲል ከነማ 0-1 ቅዱስ ጊዮርጊስ 90''ዛሬ እሁድ ጥቅምት 11/20114:00 ሰዓትበክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚድል ለአንጋፋውና ተወዳጁ ክለባችን # ፋሲል_ከነማ"ድል ለ...
21/10/2018


ተጠናቀቀ| ፋሲል ከነማ 0-1 ቅዱስ ጊዮርጊስ 90''
ዛሬ እሁድ ጥቅምት 11/2011
4:00 ሰዓት
በክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ
ድል ለአንጋፋውና ተወዳጁ ክለባችን
# ፋሲል_ከነማ
"ድል ለአፄዎቹ"
# ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው !!

 ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስተጫዋቾቻችን በሟሟቅ ላይ።በክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ  #ቢሾፍቱ
21/10/2018



ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ተጫዋቾቻችን በሟሟቅ ላይ።
በክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ #ቢሾፍቱ

Address

Gondar

Telephone

+251918736590

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ማህበር/UoG Fasil Kenema F.C Supp Assoc posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ማህበር/UoG Fasil Kenema F.C Supp Assoc:

Shortcuts

Share