Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት

Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት welcome to the OFFICIAL Mesrak Sport Media

16/09/2026

በዴንማርክ ኮፐንሀገን ሴፕቴምበር 19 እና 20/2026 (መስከረም 9 እና 10/2019) በሚካሄደው የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና ላይ በመጀመሪያው ቀን ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩት አትሌቶች እና የውድድር ፕሮግራማቸው፡-

16/09/2026
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የታዳጊዎች እግር ኳስ ልማት ስትራቴጂን ይፋ አደረገፌዴሬሽኑ ላለፉት ሁለት ዓመታት በፓይለት ፕሮጀክት እና በክልል እንዲሁም ሀገር አቀፍ የምልመላ እና የመረጣ ...
16/09/2026

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የታዳጊዎች እግር ኳስ ልማት ስትራቴጂን ይፋ አደረገ

ፌዴሬሽኑ ላለፉት ሁለት ዓመታት በፓይለት ፕሮጀክት እና በክልል እንዲሁም ሀገር አቀፍ የምልመላ እና የመረጣ ሂደትን በማጠናቀቅ፣ የታዳጊዎች እግር ኳስን በተሻለ መዋቅራዊ ለውጥ ማስቀጠል የሚያስችለውን ስትራቴጂ ማዘጋጀቱ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ወጣቶች እግር ኳስ ልማት ስትራቴጂ በቀላል ሆኖም በጠንካራ መነሻ ሃሳብ ላይ የተገነባ ሀገር አቀፍ የተጫዋቾቸ ማሳደጊያ እንደሆነም ተነግሯል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ፌዴሬሽኑ የታዳጊዎች ልማት ላይ ለክልሎች እና ለከተማ አስተዳደሮች ኃላፊነት ቢሰጥም ሁለት ክልሎች ብቻ የሙከራውን አካሄድ መተገበራቸው ተነስቷል። ይህም ባለፈው ዓመት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በታዳጊዎች ልማት ላይ ለመስራት ከስምምነት ቢደርሱም በተግባር ማዋል ላይ ግን ድክመት መታየቱም ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እንደ ሀገር እየተማረ የሚጫወት ታዳጊ ለማፍራት በሙከራ ላይ የነበረውን ሂደት ወደ ዘላቂ አካሄድ ለመቀየር መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል።

የፌዴሬሽኑ የህክምና ክፍል ሃላፊ እና የስትራቴጂክ እቅድ አማካሪው ዶ/ር ሳሙኤል የሺዋስ፣ ስትራቴጂው በተመረጡ 21 ከተሞች በሚተገበር ከ17 ዓመት በታች ሊግ እንደሚካሄድ ገልፀዋል። በየከተሞቹ ከ16 እስከ 20 የሚደርሱ ክለቦች በደርሶ መልስ እንዲወዳደሩ እንደሚደረግም ይፋ ተደርጓል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የድሬዳዋ ወጣቶች እና ስፖርት ኮሚሽን እንዲሁም የድሬዳዋ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር የሶስትዮሽ ስምምነት መፈራረማቸው ታውቋል። ይህ ስምምነት በከተማዋ ከ17 ዓመት በታች የሊግ ውድድር እንዲኖር የሚያስችል ሲሆን፣ ውድድሩም በሀገር አቀፍ ደረጃ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እጅግ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገልጿል።

ፌዴሬሽኑ በየከተሞቹ የተሰጥኦ ልየታ ባለሙያዎችን የሚመድብ ሲሆን፣ የከተማ የማዕከል እና የሀገር አቀፍ ምልመላ (ካምፕ) እንዲሁም ብቁ አሰልጣኞችን ማፍራት ላይም በትልቁ እንደሚሠራ ገልፀዋል።

በታዳጊዎች እግር ኳስ ልማት ስትራቴጂው መሠረት የውድድር መዋቅሩ በአካባቢው መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ መሠረት ያደረገ እንደሚሆን እና በአንድ ዓመት 105 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚደረግበትም ይፋ ሆኗል።

መስከረም 6 ፥ 2019 ዓ.ም |

በአሰልጣኝ አንዶኒ ኢራዮላ የተሞካሸው ዶሚኒክ ሶቦዝላይአሰልጣኝ አንዶኒ ኢራዮላ ቡድናቸው በእንግሊዝ ካራባኦ ዋንጫ ቶተንሃምን 3 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ ዶሚኒክ ሶቦዝላይ ባስቆጠራት ሦስተኛ ግ...
16/09/2026

በአሰልጣኝ አንዶኒ ኢራዮላ የተሞካሸው ዶሚኒክ ሶቦዝላይ

አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራዮላ ቡድናቸው በእንግሊዝ ካራባኦ ዋንጫ ቶተንሃምን 3 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ ዶሚኒክ ሶቦዝላይ ባስቆጠራት ሦስተኛ ግብ እጅግ መደነቃቸውን ተናግረዋል፡፡

“የመጀመሪያዎቹ ሁለት ግቦች የተገኙበት መንገድ ለእኛ በጣም አስፈላጊ ቢሆንም፣ ሦስተኛዋ ግብ ግን እጅግ አስደናቂ እና ከፍ ያለ ደረጃ ያላት ናት” ብለዋል።

“ዶሚኒክ ሶቦዝላይ ኳሱን ከመምታቱ በፊት እንኳን ግብ እንደሚያስቆጥር እምነት ያሳድርብሃል። ለሌላ ተጫዋች ቢሆን ኖሮ ቦታው ሩቅ ነው ብለህ ልታስብ ትችላለህ” ሲሉ ለተጫዋቹ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

በአሰላለፍ ላይ ስላደረጓቸው በርካታ ለውጦች ሲናገሩም በቡድኑ ላይ በርካታ ለውጦችን ማድረጋቸውን ገልጸው፤ ይህን የማድረጋቸውን ተገቢነትም አብራርተዋል።

“ምክንያቱም ባለፈው ጨዋታ ጉድለት እንደነበረብን አይተናል፤ አዲስ ጉልበትም ያስፈልገን ነበር” ሲሉ ሀሳባቸውን ተናግረዋል።

አያይዘውም ሁሉም ተጫዋቾች ከፍተኛ ጉልበትና ጠንካራ ፍልሚያ ሜዳ ላይ በማሳየታቸው ደስተኛ መሆናቸውን፣ በአብዛኛው የጨዋታው ክፍል ጥሩ እንደነበሩ ብሎም ማሸነፍ እና ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ የሚገባቸው እንደነበር ገልጸዋል። ( etv )

ባርሴሎና የሀምዛ አብደልከሪምን ባርሴሎና ለቀድሞ የአል አህሊ ተጫዋች አዲስ ውል መስጠቱ ታውቋል። ይህም ተጫዋቹ በካምፕ ኑ እስከ 2030 እንዲቆይ ያስችለዋል።በቅድመ ውድድር ዘመን ለባርሴሎና...
16/09/2026

ባርሴሎና የሀምዛ አብደልከሪምን

ባርሴሎና ለቀድሞ የአል አህሊ ተጫዋች አዲስ ውል መስጠቱ ታውቋል። ይህም ተጫዋቹ በካምፕ ኑ እስከ 2030 እንዲቆይ ያስችለዋል።

በቅድመ ውድድር ዘመን ለባርሴሎና ተሰልፎ በተጫወተባቸው ጨዋታዎች አራት ግቦችን ያስቆጠረው የፊት መስመር ተጫዋቹ ሀምዛ አብደልከሪም፣ በአዲሱ የባርሴሎና ትውልድ ቁልፍ ሚና ይኖራቸዋል ተብለው ከሚጠበቁ ተጫዋቾች አንዱ ነው።

ባለፈው የውድድር ዘመን አጋማሽ ክለቡን የተቀላቀለው ሀምዛ አብደልከሪም፣ ዓመቱን ያሳለፈው ለባርሴሎና ከ19 ዓመት በታች ቡድን በመጫወት ነበር።

የሁለተኛ ደረጃ ብሔራዊ የብስክሌት ዳኞች ሥልጠና ተጠናቆ ለሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ተሰጠየኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ለአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ዳኞች ያዘጋጀው የሁለተኛ ደረጃ ብሔራ...
15/09/2026

የሁለተኛ ደረጃ ብሔራዊ የብስክሌት ዳኞች ሥልጠና ተጠናቆ ለሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ተሰጠ

የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ለአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ዳኞች ያዘጋጀው የሁለተኛ ደረጃ ብሔራዊ የብስክሌት ዳኞች ሥልጠና በስኬት ተጠናቋል።

ከነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለ20 ዳኞች ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና፣ የውድድር ደንቦችን፣ የዳኝነት መርሆዎችን፣ የውሳኔ አሰጣጥን፣ ገለልተኛነትን፣ የውድድር ደኅንነትንና ሌሎች ተያያዥ ሙያዊ ጉዳዮችን ያካተተ ነበር።

የክፍል ውስጥ ትምህርቱን ከመስክ ልምምድ ጋር ለማጣመር፣ ሰልጣኞቹ ወደ አዳማ ከተማ ተጉዘው ተግባራዊ ሥልጠና አካሂደዋል። ይህም የተማሩትን ዕውቀት አዳማ ላይ በተካሄደ የብስክሌት ውድድር ላይ እንዲተገብሩና የመስክ ልምዳቸውን እንዲያሳድጉ አስችሏቸዋል።

በሥልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የምረቃና የምስክር ወረቀት መስጫ መርሐ ግብር ተካሂዶ፣ ሥልጠናውን ላጠናቀቁ ተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

ብቁና በቂ ቁጥር ያላቸው ዳኞችን ማፍራት ፍትሐዊ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ተዓማኒና ደረጃውን የጠበቀ ውድድር ለማካሄድ መሠረታዊ ነው። ዳኞች የውድድር ሕጎች ለሁሉም በእኩልነት መተግበራቸውን፣ ውድድሩ በትክክለኛው የቴክኒክ ሥርዓት መመራቱንና የአትሌቶች ደኅንነት ቅድሚያ ማግኘቱን የሚያረጋግጡ ቁልፍ ባለሙያዎች ናቸው።

በፌዴሬሽኑ ውስጥ የብቁ ዳኞች ቁጥር፣ የሙያ ደረጃና ሀገር አቀፍ ስርጭት ከሚፈለገው ደረጃ በታች ሆኖ ቆይቷል። በመሆኑም ይህ ሥልጠና ክፍተቱን ለመቀነስና የሀገራችንን የውድድር አመራር ሥርዓት ለማጠናከር የተወሰደ ጠንካራ እርምጃ ነው።

ፌዴሬሽኑ ሥልጠናውን በመስጠት ብቻ የማይቆም ሲሆን፣ የሠለጠኑ ዳኞች በውድድሮች ላይ ተግባራዊ ዕድል እንዲያገኙ፣ ብቃታቸው እንዲገመገምና ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና እንዲያገኙ ይሠራል። ይህ የአቅም ግንባታ ሥራም በተያዘው እቅድ መሠረት በሌሎች ከተሞችና ክልሎች ይቀጥላል።

ሥልጠናውን ላጠናቀቁ ዳኞች እንኳን ደስ አላችሁ!

ሥልጠናው እንዲሳካ ለተባበረው የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን፣ ለአሰልጣኞችና ለድጋፍ ሰጪ አካላት የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል።

ኢትዮጵያን በብስክሌት ወደ ከፍታ እናድርስ!




ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ፤በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 18ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ከፕሬዚዳንቱ በተጨማሪ በቀጣይ አራት ዓመታት ፌዴሬሽ...
15/09/2026

ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ፤

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 18ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ከፕሬዚዳንቱ በተጨማሪ በቀጣይ አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን የሚመሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትም ተመርጠዋል።

እነርሱም፦

1. ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ (ምክትል ፕሬዝዳንት)
2. ዶ/ር ዳኛቸው ንግሩ
3. ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ
4. ወ/ሮ ሰርካለም ሳሙኤል
5. ዶ/ር ወገኔ ዋልተንጉሥ
6. አቶ አበባው ሰሎሞን
7. አቶ አንበሴ አበበ
8. አቶ ደመላሽ ይትባረክ

ለኮሚሽነር አለሙ መግራ እና ለተመረጡት የስራ አስፈፃሚ አባላት መልካም የስራ ዘመን እንመኛለን!

በእግር ኳስ ጥበብ ከፍ ባለ ዙፋን የተቀመጠውን ፣ በዘመኑ ያዩት ሁሉ ታላቅነቱን በአንድ ድምፅ የተስማሙበትን ፡ በአንድ ወቅት ጥበበኛው ኢታሎ ቫሳሎ የሊቻኖ ቫሳሎ ታናሽ ወንድም ( ከ3ኛ እስ...
14/09/2026

በእግር ኳስ ጥበብ ከፍ ባለ ዙፋን የተቀመጠውን ፣
በዘመኑ ያዩት ሁሉ ታላቅነቱን በአንድ ድምፅ የተስማሙበትን ፡ በአንድ ወቅት ጥበበኛው ኢታሎ ቫሳሎ የሊቻኖ ቫሳሎ ታናሽ ወንድም ( ከ3ኛ እስከ 8ኛ አፍሪካ ዋንጫ የተጫወተ ፣
የ3ኛ አፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ፣ የኮተን ተጫዋች) ስለራሱ ጥበበኛነት ሲጠየቅ " የሙቅቢልን ያህል ተጫዋች ከሆንኩኝ በእርግጥም ጥበበኛ ነኝ " ሲል የመሰከረለትን ፣
በጥበቡ ያኔ ያዩት ሁሉ እስካሁንም አይተኬ እንደሆነ ሳይሰለቹ የሚናገሩለትን ሙቅቢል አህመድን ይዤው መጥቻለሁ ። 'ሲ ሲ ሲቱ ቲያ አስ ጎሪ ጎሪ ገመ ኪያ ' የተባለ ድንቅ የኦሮምኛ ዘፈን እንደነበረውና ሜዳ ውስጥ ሳይቀር እየተጫወተ ሁሉ ዘፈኗን ያንጎራጉር እንደነበረ ይነገርለታል ።
ኑሮህንም በየመን አድርገህ በአሰልጣኝነት እንደቆየህም ሰምቼያለሁ ፥ ጋሽ ሙቅቢል ባለህበት ረጅም እድሜንና ጤናን ተመኝቼልሃለሁ ።

Via፦ አለማየሁ ኡርጌሳ

Address

Dire Dawa

Telephone

+251915750424

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት:

Shortcuts

Share