29/05/2026
📢 ይፋዊ መግለጫ – ለድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
Dire Dawa Football Federation
ጉዳዩ፡ በተደጋጋሚ የሚፈጸም ግፍ፣ አድልዎ፣ የጎን ቃድ አሰራር እና ፍትሕ እጦት ምክንያት ከውድድሩን መሳተፍ ማቆም ስለማሳወቅ
በእግር ኳስ ስፖርት ውስጥ ፍትሕ፣ እኩልነት እና ግልጽነት ዋና መሠረቶች መሆናቸው እየታወቀ፣ ከሀፈተእሳ እግር ኳስ ክለብ አመራሮች፣ ተጫዋቾች፣ ደጋፊዎች እና አባላት በድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር በተደጋጋሚ በሚፈጸምብን ግፍ፣ አድልዎ፣ የጎን ቃድ አሰራር እና የፍትሕ እጦት እጅግ ተበሳጭተናል።
ይህ ችግር ዛሬ ብቻ የተፈጠረ ሳይሆን፣ ላለፉት ዓመታት በተከታታይ በክለባችን ላይ ሲደጋገም የቆየ ነው። በውድድሮች ውስጥ የፍትሃዊ ዳኝነት እጥረት፣ ህጎች በእኩልነት አለመተግበር፣ በሙሲና የታጥረ federation ለተወሰኑ ክለቦች የሚደረግ ግልጽ አድልዎ እና የክለባችን መብት ችላ መባል በተደጋጋሚ ተፈጽሟል።
በተጨማሪም በፌዴሬሽኑ ውስጥ የጎን ቃድ አሰራር መኖሩ እና ውሳኔዎች በፍትሕ ሳይሆን በወገንተኝነት መሰጠታቸው የስፖርቱን ክብር እጅግ እያበላሸ ነው። ይህም እኩል ውድድር እንዳይኖር እና ክለቦች በችሎታቸው ሳይሆን በወገንተኝነት እንዲመዘኑ እያደረገ ነው።
በዚህ ሁኔታ ላይ የተደጋጋሚ ቅሬታዎች ቢቀርቡም ፌዴሬሽኑ ተገቢ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ዝምታን መምረጡ በጣም አሳዛኝ ነው።
ስለዚህ፣ ፍትሃዊ፣ ግልጽ እና ተጠያቂነት ያለው አሰራር እስኪመጣ ድረስ ክለባችን በማንኛውም በሙሲና የታጥረው የድሬደዋ እግርከኳስ የሚያዘጋጀው ውድድሮች ላይ እንደማይሳተፍ በይፋ እናሳውቃለን።
Xafad_Ciisa ሀፈትኢሳ football clubs
📍 ድሬዳዋ
የድረዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ማህበር Dire Dawa City sport club Fan Association
ዋንጫ - Wancha
Mohamed Elmi
Followers on Facebook
dire