28/04/2026
ሁሉም አርት የራሱ የሆነ----
""""
ከ20 አመት በፊት አሁን MMA እየተባለ የሚጠራውን የሚመስል የፍልምያ ዜዴ በምረቃ ላይ በአራት ኪሎ ወወክማ በፈይሰልና ሙስጠፋ መሀል እንዲደረግ አድርጌ ነበር::
""""
በወቅቱ ከፍተኛ ደም ፈሰስ እና ያልተለመደ ጉዳት ሰለተፈጠረ በተመልካች ዘንድ ግርታ እና መደናገጥ ነበር::
"""""
ይህን ያነሳሁት በምክንያት ነው:-
ብዙ ሰዎች አንዱን የማርሻል አርት አይነት ከፍ ለማድረግ ሌላውን ማሳነስ እውቀት አድርገውት ስላየሁ ነው::
""""
በመሰረቱ ይህ ሚክስድ ማርሻል አርት የተባለው የውድድር አይነት አንዳች የተለየ የእግር ወይም የእጅ ቴክኒክ የለውም::
አብዛኛዎቹ ቴኒኮች በውሹ: በቴኳንዶ በጅዶ በካራቴም ያሉ ናቸው:: """"
በዋናነት ከሞይታይ: ከኪክ ቦግስ: ከጅጅትሱ የሚቀዱ ቴክኒኮች ይበዛሉ::
""""
Ground Fighting (Ne-waza ከጅጅትሱ ሌሎች የእግር እና የእጅ አጠቃቀሞች ደግሞ ከሞይታይና ኪክቦግስ ይወስዳል::
"""""
ቁምነገሩ ይህ ነው
ብዙዎቹ ማርሻል አርት ዜዴዎች ማለትም Traditional Martial Arts competitions (e.g., Karate, Judo, Taekwondo) often prioritize specific techniques, form, and safety, focusing on regulated scoring, ትኩረታቸው ውስን መወዳደርያ ቴክኒኮችን በመጠቀም: ጥብቅ የውድድር ህግ በመተግበር ያወዳድራሉ: እንደ ክርን ጉልበት የመሳሰሉ ማጥቂያ ዜዴዎችን የወደቀን ተጋጣሚ ማጥቃትን ሆን ብሎ ለመጉዳት ከፍተኛ ሀይል መጠቀምን በተለይ በITF ይከለክላሉ::
""""
ዋነኛ ምክንያታቸው safety ወይም የተጋጣሚዎችን ደህንነት መጠበቅ ነው::
""""
whereas MMA focuses on complete domination through multiple phases of fighting በአንፃሩ ሚክስድ ማርሻል አርት ማንኛውም ቴክኒክ ተጠቅመው ተጋጣሚን ማውደም ላይ ያተኩራሉ::
"""""
ስለሆነም ምንም እንኳን የሁሉም አርቶች ቴክኒኮች ተመሳሳይ ቢሆኑም የልምምድ መርሀ ግብራቸውና የውድድር ስርአታቸው በዚህ አኳሀን ይለያያሉ::
"""""
ሌላው ቀርቶ ውሹ ከካራቴ: ቴኳንዶ ከሌሎቹ በውድድር ህግ ይለያያሉ::
"""""
ስለሆነም አንድን ሰው ባልተለማመደው የውድድር ህግ ቢገባ ውጤቱ አያምርም:
አንዱ ከሌላ ስለሚሻል ግን አይደለም ::
"""""
አንድ የሚክስድ ማርሻል አርት ተለማማጅ በውሹ በካራቴ ወይም በቴኳንዶ ውድድር ህግ ቢወዳደር ውጤቱ ከዚህ እውነታ አይውጣም::
"""""
ሁሉም አርቶች የራሳቸው የሆነ ጠንካራ ጎን አላቸው: ማበላለጥ ግን ትክክል ላይ ሆን ይችላል::
እሺ ለእራስ መከላከልስ የትኛው ይሻላል?
ብዙ የማርሻል አርት ሰዎች ስልጠናቸው ትክክል ነው ወይ?
ለነዚህ ሁለት ጥያቄዎች በሌላ ፓስት እመጣለሁ::