06/02/2026
🔴 #ማስታወቂያ ለሁሉም እንዲደርስ #ሼር ይደረግ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የጨዋታ ታዛቢዎች/አሴሰሮች ስልጠና በመስጠት የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡትን በየሊጐች መድቦ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ዳኛ የነበራችሁ እና ከዚህ ጋር የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ብቻ በተቀመጠው ሊንክ እየገባችሁ እንድትመዘገቡ እናስታውቃለን፡፡
💥 #መስፈርት
➊- ፌደራል ዳኛ የነበረ
➋- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚያወዳድራቸውን ሊጎች በዳኝነት የሰራ
➌- እንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ያለው
➍- የሚሰጠውን የጤና ምርመራ የሚያልፍ
➎- ጥሩ ስነ ምግባር ያለው
➏- በማናቸውም የእግር ኳስ ክለብ እና የክልልና ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች አባል እና አመራር ያልሆነ
➐- የኮምፒውተር አጠቃቀም ክህሎት ያለው
➑- ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቀ እና ከዚያ በላይ
➒- ከደባል ሱስ የፀዳ
➓- በስነ ምግባር ጥሰት ተቀጥቶ ያልታገደ
እዚህ ይመዝገቡ 👇
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfmAWpJXe8xOKHB3xTIUXFMv6Z2SiyPiQC3vKbCm0txXgq80A/viewform?usp=publish-editor
የጤና ምርመራ፤ መግቢያ ፈተና የሚሰጥበት እና ስልጠናው የሚጀመርበት ጊዜ ወደፊት ይገለፃል፡፡
🌀