TANA SPORT

TANA SPORT Tana the best !

15/09/2021
ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ ዋሊያዎቹ ከጋና ጋር ይዞት የሚገባ አሰላለፍ 4 - 3 - 3 ነው። ድል ለዋሊያዎቹ !!
03/09/2021

ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ ዋሊያዎቹ ከጋና ጋር ይዞት የሚገባ አሰላለፍ 4 - 3 - 3 ነው።

ድል ለዋሊያዎቹ !!

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ..." ልጄን ለአንተ ምርጡ እግር ኳስ ተጫዋች ማን ነው ብየ ስጠይቀው አንተ አባቴ ይላል ብየ ጠብቄ ነበር፣ የልጄ መልስ ግን ሊወኔል ሜሲ ነበር "
23/08/2021

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ..." ልጄን ለአንተ ምርጡ እግር ኳስ ተጫዋች ማን ነው ብየ ስጠይቀው አንተ አባቴ ይላል ብየ ጠብቄ ነበር፣ የልጄ መልስ ግን ሊወኔል ሜሲ ነበር "

ሊወኔል መሲ ባርሴሎናን እያለቀሰ ሲሰናበት የተጠቀመበት ሶፍት በጨረታ 1ሚሊየን ዶላር ተሽጧል።
16/08/2021

ሊወኔል መሲ ባርሴሎናን እያለቀሰ ሲሰናበት የተጠቀመበት ሶፍት በጨረታ 1ሚሊየን ዶላር ተሽጧል።

በአንድ ወቅት ከሀይሌ ገብረስላሴ ጋር ፎቶ የመነሳት እድል የገጠማቸው ሰር አሌክስ ፈርጉሰን፣ ሪያን ጊግስ እና ሪዮ ፈርዲናንድ ።
11/08/2021

በአንድ ወቅት ከሀይሌ ገብረስላሴ ጋር ፎቶ የመነሳት እድል የገጠማቸው ሰር አሌክስ ፈርጉሰን፣ ሪያን ጊግስ እና ሪዮ ፈርዲናንድ ።

ሚሲ ድሮና ዘንድሮ
11/08/2021

ሚሲ ድሮና ዘንድሮ

06/09/2018

የሃሙስ ጳጉሜ 1/2010 ዓ/ም የጣና ስፖርት መረጃዎች
────────────────────────────────────────────
የሃገር ዉስጥ መረጃዎች

 ካፍ ወደ ኤሊት (ከፍተኛ) ደረጃ የሚያድጉ ዳኞችን ለመለየት የሚያከናውነው ፈተና ላይ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ ይካፈላል።
 የሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን በ2019ኙ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ላለበት ቀጣይ ጨዋታ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። 2 ወሳኝ ተጫዋቾች በጉዳት ምክኒያት ራሳቸውን ከቡድኑ ሲያገልሉ የአምበሉ ኡማሩ ባንጉራ መሰለፍም አጠራጣሪ ሆኗል።
────────────────────────────────────────────
────────────────────────────────────────────

የዉጭ መረጃዎች

────────────────────────────────────────────

 የሊቨርፑል አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ እንዳሉት፣ ብድናቸው እስካሁን ምርጥ ብቃቱ ላይ እንዳልደረሰ ይልቅስ ቅድመ ውድድር ዘመን በሚመስል እንቅስቃሴ ላይ እንዳለ ተናግረዋል። የርገን ክሎፕ በአሁኑ ሰዓት ለቀድሞዉ የዶርትሞንድ ግብ ጠባቂ ሽኝት ፐሮገራም ወደ ጀርመን አቅንተዋል፡፡( ሚረር)
 የፒ ኤስ ጂዉ ፈረንሳዊዉ ወጣት ኮከብ ክልያን ምብፔ በሜዳ ዉስጥ ባሳየዉ ያልተገባ ባህሪ የ 3 ጨዋታ ቅጣት ተላልፎበታል፡፡(ዘ ሰን)
 የዌስት ሃም አሰልጣኝ ማኑዌል ፔሌግሪን የመጀመሪያ 4 ጨዋታዎችን መሸነፋቸዉን ተከትሎ ሊሰነበቱ እንደሚችሉ እየተነገረ ነዉ፡፡ አሰልጣኙ የሚያሰናብት ከሆነ በካሳ መልክ £15 ሚልዮን ይከፍላል።(ታይምስ)፡፡
 በዚህ ሲዝን ምርጥ ብቃቱን በማሳየት የነሃሴ ወር የክለቡ ኮከብ ተጫዋች መሆን የቻለዉ የማንችስተር ዩናይትዱ የቀኝ መስመር ፉልባክ ሉክ ሾው፤ ባጋጠመው የእግር ስብራት የተነሳ እግሩን እስከማጣት ሊያደርስ የሚችል አስቸጋሪ ጊዜ እንዳሳለፈ ገለፀ።(ዘ ሰን)
 በርካታ የአርሰናል አስተዳደር ሃላፊዎች ኡናይ ኤምሬን ጨምሮ ኢቫን ጋዚዲዝን በተመለከተ የመቆየት ወይም የመልቀቅን ውሳኔያቸውን ባለማወቃቸው ደስተኞች እንዳልሆኑ ታውቋል፤ ጋዚዲዝ ወደ ኤሲ ሚላን ሊዘዋወሩ ነው የሚል ዜና ሰናፈስ እንደቆየ የሚታወስ ሲሆን ጋዚዲዝ ግን እስካሁን ስለ ሁኔታዉ ያሉት ነገር እነደሌለ እየተነገረ ይገኛል።(ታይምስ)
 የማንችስተር ዩናይትዱ አማካኝ ፖል ፖግባ ከኦልትራፎርድ እንደሚለያይ አሁንም እየተወራበት ይገኛል፤ የባርሴሎናው አጥቂ ሊዊስ ስዋሬዝ ፣ ጀራርድ ፒኬ እና የተወሰኑ ባርሴሎና ተጫዋጮች ወደ ኑካምፕ ቢመጣ በደስታ እንደሚቀበሉት ተናግረዋል ። (ኢ.ኤስ.ፒ.ኤን)
 የጆሴ ሞሪንሆ የታክስ ማጭበርበር ወንጀል የአንድ አመት እግድ ወደ ገንዘብ እንደሚቀየር ተነግሯል ። (ኢ.ኤስ.ፒ.ኤን)

02/09/2018

የእሁድ 27/12/2010 የሃገር ውስጥ ስፖርታዊ መረጃዎች

፦ ረጅም ወራትን ከጨዋታ ርቆ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በ10:00 ላይ የቡሩንዲ አቻውን በወዳጅነት ጨዋታ ይገጥማል።

፦የዋሊያዎቹ ተጋጣሚ የሆነው በአሠልጣኝ ጆን ኪስተር የሚመራው የሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን ጳጉሜ 4 በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ የተመረጡ የመጨረሻ 23 ተጫዋቾችን
አሳውቋል። ቡድኑ 2 በሃገር ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ብቻ አካቷል።

02/09/2018

የእሁድ 27/12/2010 ስፖርታዊ መረጃዎች
ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማድረግዎን አይርሱ! ከተመቻቹ ደግሞ ሼር ያርጉት።
════════════════════════
በዜናወቻችን ላይ የተካተቱትን በጥቂቱ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣

የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ የሆኑት አወዛጋቢ ሰዉ ጆዜ ሞሪኖ በክረምቱ የዝዉዉር መስኮት ላይ የ5 ጊዜ የባላንዶር አሸናፊዉን ክርስቲያኖ ሮናልዶን ከሪያል ማድሪድ ወደ
ጁቬንትስ ሳይዘዋወር በፊት ወደ ክለባቸዉ ማንችስተር ዩናይትድ የማምጣት ፍላጎት እንዳልነበራቸዉ ተገልፆ።
ተያይዞም ጆዜ ከክለቡ ጋርም ባሳለፍነዉ ክረምቱ የዝዉዉር መስኮት ላይ በዉዝግብ ምክንያት አሳልፈዋል ተብሎል።(bbc)

ፈረንሳዮ አማካኝ ፖል ፖግባ በጥር ወር የዝዉዉር መስኮት ላይ ወደ ቀድሞዉ ክለቡ ጁቬንትስ የመመለስ ፈላጎት አንዳለዉ ቢነገርም ግን ፖግባ ከአሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኖ ጋር ጥሩ
ግንኙነት እንዳለዉ ተናግሮል። (sun)
:
የ26 አመቱ ብራዚላዊዉ ቄንጠኛ ተጫዋች ኔይማር ጁኔር ወደ እንግሊዞቹ ክለቦች ወደ ሆኑት አርሰናል እና ቼልሲ የመሄድ ፈላጎት አለዉ ተብሎል። ኔይማርም ለንደን ከተማ የመሄድ
ፍላጎት መኖሩን ተከትሎ ለወደፊቱ ከሁለቱ ክለቦች አንዳቸዉን ሊቀላቀል ይችላል ሲል፣ (Sunday express) ዘግቧል።
:
የቶተንሃሙ አማካኝ ቤልጀማዊዉ ሙሳ ዴንቤሌ በጥር ወደ ቻይና ሱፐር ሊግ ክለብ ወደ ሆነዉ ቤጅንግ ሲኖቦ ጁአን በ3 አመት የዉል ስምምነት፣ ሳምንታዊ ደሞዙ £192,000
በማድረግ ያመራል ተብሎል። (marca)
:
የማንችስተር ሲቲ ክለብ በለሀብት የሆኑት ሸክ መንሱር የክለባቸዉን ስታዲየም የሆነዉን ኢትሃድን ደጋፊወችን የመያዝ አቅሙን ከፍ ለማድረግ አስበዋል።(sky sport)
:
ቶተንሃሞች አይናቸዉን ከአያክሱ አማካኝ ፍራንክ ዲጆንግ ላይ አሳርፈዋል። በጥር ወደ ክለባቸዉ ለማዘዋወር ሲሉ።(mail)
:
ኮሎቢያዊዉ ተከላካይ ዮሪ ሚና በክረምቱ የዝዉዉር መስኮት ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ሊዘዋወር ነዉ ተብሎ ሲጠበቅ ወደ የመርሳይዱ ክለብ ኤቨርተንን ተቀላቀለ። የዚህ ምክንያት
ደግሞ የኤቨርተኑ አሰልጣኝ ማርኮ ሲሊቫ ናቸዉ፣ ነገሩም ማርኮ ሲሊቫ ለዪሪ ሚና በስልክ ደዉለዉ ከማን ዩናይትድ ጋር ያለዉን የዝዉዉር ንግግር አቁሞ ወደ ክከባቸዉ ኤቨርተን
እንዲቀላቀል አነጋገሩት በዚህም ወጣቱ ተከላካይ ዩሪ ሚና አሳቡን ቀይሮ ወደ ኤቨርተን ሊቀላቀል ችሎል።(daily mirror)
:
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ዩና ኤምሪ በፕሪሜየር ሊጉ የእረጅም እግር ኳስ አጨዋወትን ከመከተል ይልቅ አጭር የእግር አጨዋወት ፍልስፍናን ቢከተሉ የተሻለ እንደሆነ የተለያዩ
የእግር ኳስ ባለሞያወች ተናግረዋል።(star)
:
የቀድሞዉ የአርሰናል የአሁኑ የዌስታሃም ተጫዋች ጃክ ዊሊሸር በእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ግሬጅ ሳዉዚጌት እንዲመረጥ ወደ ቀድሞዉ ብቃቱ መመለስ እንዳለበት ተነግሮል።(sport)

06/03/2018

ጣና ሰፖርት ትኩስ ወቅታዊ የሃገር ዉስጥና የዉጭ ስፖርታዊ መረጃዎች ምንጭ
 በሬድዮ መከታተል ለምትፈልጉ ዘወትር ሰኞ፣ህሮብና አርብ ከረፋዱ 5 – 6 ሰዓት
• በ FM ባህር ዳር 96.9
• በ ደሴ FM
• በ ደ/ማርቆስ FM
• በ ደ/ብርሃን FM
• በ አማራ ሬዲዮ
• በ በናይል ሳት አማራ ሬዲዮ

06/03/2018

መጋቢት 27/2010 የዉጭ ሃገራት ስፖርት መረጃዎች
 ሆዜ ሞሪንሆ በመጪው ክረምት በሚዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ለሩሲያው የመገናኛ ብዙኃን ማሰራጫ ለሆነው አርቲ ቲቪ የጨዋታ ትንታኔ ባለሙያ ሆነው የሚሰሩ ይሆናል።
የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ” በሃገሪቱ መንግስት የገንዘብ ምንጭ ለሚተዳደረው የቴሌቭዥን ጣቢያ “ሙያዊ ትንተና እና የውጤት ግምታቸውን” እንደሚያቀርቡ አርቲ ገልፅዋል።
“የአርቲን ቡድን በመቀላቀሌ በጣም ደስተኛ ነኝ። በመጪው ክረምት በሩሲያው ዓለም ዋንጫ ላይ ለመታደም እና በጨዋታዎቹ ላይ ያለኝን ምልከታ ለማቅረብ እቅድ አለኝ።” ሲሉም ሞሪንሆ በአርቲ ድረገፅ በኩል ገልፀዋል።
የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ፒተር ሽሜይክልም በሩሲያ በሚዘጋጀው ውድድር ላይ ለአርቲ ቲቪ በተንታኝነት የሚሰራ ሌላኛው ሰው ነው።
“የአርቲን ሃሳባዊ ምርጥ ቡድን በጋራ መስራታችንን እንቀጥላለን። እናም አሁን አሰልጣኛችንን አግኝተናል።” ሲሉ የሩሲያ ቱደይ ጋዜጣ ዋና ኤዲተር የሆኑት ማርጋሪታ ሲሞንያን ተናግረዋል።
አርቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋ የዜና አገልግሎት መሰረቱን በዌስትሚንስቴር ያደረገ እና ከዚህ ቀደም በቭላድሚትር ፑቲን እና በሩሲያ መንግስት ቃልአቀባይ እንደሆነ ወቀሳ ሲደርስበት የቆየ የቴሌፅቭዥን ጣቢያ ነው።
 መድፈኞቹ የመስመር ተጫዋች ሄነሪክ ማኪቴሪያን ከማንችስተር ዩናይትድ ለመለቀቁ ትልቁ ምክንያት የአሰልጣኝ ጆዜ ሞውሪንሆ የአጨዋወት ፍልስፍና መሆኑን ገልጿል።
በጥር ወር የአሌክሲ ሳንቼዝን ከአርሴናል መልቀቅ እና ማንችስተር ዩናይትድን መቀላቀል ተከትሎ የ 29 አመቱ አማካኝ በተቃራኒው ከማንችስተር ወደ አርሰናል መዘዋወሩ ይታወሳል።
በማንችስተር ዩናይትድ የአንድ አመት ከግማሽ ቆይታው 11 ጎሎችን ማስቆጠር የቻለው ማኪቴሪያን በዘንድሮው የውድድር ዘመን በተደጋጋሚ ከቋሚ አሰላለፍ ውጭ መሆኑን ተከትሎ የመጫወት እድልን ለማግኘት ምርጫውን አርሰናል አድርጓል።
አርመናዊው ኮከብ አርሰናልን ከተቀላቀለ በኋላ ከኤቨርተን ጋር ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ ሶስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ማመቻቸት ቢችልም ባለፉት ሳምንታት ለመድፈኞቹ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ላይ ይህንን ምርጥ አቋሙ መድገም ተስኖት ታይቷል።
ማኪቴሪያን ወደሰሜን ለንደኑ አርሰናል ስላደረገው ዝውውር ከስካይ ስፖርት ጋር ባደረገው ቆይታም “አርሴናል ማጥቃት ላይ ያመዘነ ኳስ እንደሚጫወት ሁሉም ሰው ያውቃል። እኔም ማጥቃት ላይ የተመሰረተ ኳስ መጫወት እወዳለሁ።
“በማንችስተርም ቤት ማጥቃት ላይ ያመዘነ ጨዋታን እንጫወት ነበር፤ ነገር ግን ሁሉም ጨዋታዎች ላይ አይደለም። ስለዚህ በጣም ይለያያል።”
“አጥቂ፣ አማካኝ ወይም የክንፍ ተጫዋች ብትሆን ሁሉም ተጫዋች መከላከል አለበት። በአራት እና በአምስት ተጨዋች አትከላከልም፤ በሙሉ ቡድኑ መከላከል ግድ ነው።
“ቡድኑ በመከላከል ለማገዝ የተቻለኝን ጥረት አደርጋለው፤ ነገር ግን አንድ አንዴ ይሳካል ሌላ ጊዜ አይሳካም። እኔ ሁሌም ከሁሉም በፊት ቡድኔን ለመርዳት እሞክራለሁ። ከዛም ስለራሴ አስባለሁ። እራሴን ለማስቀደም የምሞክር እራስ ወዳድ ተጨዋች አይደለሁም።” ብሏል።
ማኪቴሪያን በጆሴ ሞውሪንሆ ስር ያለው በአካል ብቃት ላይ ያመዘነ አጨዋወት ከደቃቃ ሰውነቱና ከሚወደው የአንድ ሁለት ቅብብል አጨዋወት አንፃር ከብዶት እንደቆየ አይረሳም።
 ኤደን ዜኮ ከአለማችን አምስቱ ታላላቅ ሊጎች በሶስቱ ላይ አምሳ እና ከዚያ በላይ ጎል ማስቆጠር የቻለ የመጀመሪያው ተጫዋች የሚያደርገውን ታሪክ ሰርቷል፡፡
ትናንት ምሽት የሴሪ አውን መሪ ናፖሊ 4-2 በሆነ ውጤት ያሸነፉት ሮማዎች ከአራቱ ጎሎች መካከል ሁለቱን በቀድሞው የማንችስተር ሲቲ አጥቂ ዜኮ አማካኝነት ያስመዘገቡ ሲሆን እነዚህ ሁለት ጎሎችም ዜኮ በሴሪያው ያስቆጠራቸው 49 እና 59ኛ ጎሎች ሆነው ተመዝግበውለታል፡፡
አምስቱ የአለማችን ታላላቅ ሊጎች የሚባሉት(እንግሊዝ ፣ ስፔን ፣ ጣልያን ፣ ጀርመንና ፈረንሳይ) ውስጥ በሶስቱ ቆይታ የነበረው ዜኮ በየሄደበት የተረጋገጠለት ጎል አስቆጣሪ መሆኑን ማሳየቱን የቀጠለ ሲሆን ይህም ለአዲስ ክብር አብቅቶታል፡፡
ዜኮ በጀርመን ቆይታው ለዎልፍስበርግ 66 ጎሎችን ማስቆጠርና ክለቡንም ለቡንደስሊጋ ክብር ማብቃት ከቻለ በኋላ ወደእንግሊዝ በመምጣት ማንችስተር ሲቲን ተቀላቅሎ 130 ጨዋታዎችን ማድረግ የቻለ ሲሆን 50 ጎሎችንም በውሃ ሰማያዊው መለያ አስቆጥሯል፡፡
በበርካታ ረብጣ ሚልዮኖች ታላላቅ ከዋክብትን ሰብስቦ በነበረው ሲቲ ቤት በአጉዌሮና ካርሎስ ቴቬዝን በመሳሰሉ አጥቂዎች እምብዛም የመጫወት ዕድልን ያላገኘው ቦስኒያዊ ወደጣልያን አምርቶ የተለመደ ጎል አስቆጣሪነቱን የቀጠለ ሲሆን በዚህም ቆይታው የመጀመሪያ እግር ኳሰኛ የሆነበትን አጋጣሚ አሳክቷል፡፡
 መድፈኞቹ ከ2002 በሆላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተከታታይ ለ4ተኛ ጊዜ ሽንፈትን አስተናግደዋል፡፡ አርሰን ዌንገር ከሽንፈቱ በኋላ አስተያታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ብራይተንን ከሜዳቸው ውጭ የገጠሙት መድፈኞቹ ፤ በባለሜዳዋቹ ብራይተኖች የ 2 ለ 1 የሽንፈት ፅዋን ተጎናፅፈው ለመመለስ ተገደዋል፤ የብራይተኑ የሽንፈት ውጤት ለአርሰናሎች ለተከታታይ 4ተኛ ጊዜ ሽንፈት ሁኖ ተመዝግቧል ይሄም ከ2002 በሆላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆኗል፡፡
የአርሴናል ቤት የአሰልጣኝነት ስራቸውን ለማስጠበቅ እየከበዳቸው ያሉት እና ጫናው የበዛባቸው አርሴን ቬንገር ስለቀጣዬ አመት የሻምፒዬንስ ሊግ ተሳትፎ እና ስለ ሽንፈቱ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። “ተመልከቱ ተስፋ መቁረጡ ይገባኛል ፤ ከባለፈው ሳምንት ከደረሰብን ነገር ቶሎ ለማገገም በጣም ከባድ ነው፤ በጣም በከባድ ጊዜ ውስጥ እየተጓዝ ነው ያለነው.” .
” ከእውነት ያልራቀ ልንሆን ይገባል፤ በሻምፒዬንስ ሊጉ ለመሳተፍ የሁለት ቡድኖችን መውደቅ ያስፈልገናል ፤ ነገር ግን ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ በሆላ ብዙ ነጥቦችን ይጥላሉ ብሎ ማሰብ ከባድ ነው ፤ ነገር ግን የተቻለንን ሁሉ በማድረግ ሩቅ መጓዝ ይኖርብንል ለዚህ ደግሞ የአውሮፖ ሊጉ ውድድር ተመራጩ መንገድ ነው.
” . አርሴናል ከብራይተኑ ሽንፈት በሆላ በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 6ተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል ፤ የቀጣይ አመት የሻምፒዬንስ ሊግ ተሳትፏቸውም ጥያቄ ውስጥ ገብቷል ወይስ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር ያለፈው አመት የጆዜ ሞሪንሆን የሻምፒዬንስ ሊግ የመሳተፊያ መንገድ በኢሮፖ ሊግ በማድረግ ይሳካላቸው ይሆን?

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when TANA SPORT posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category