20/02/2026
“ ጥሩ ደሞዝ የሚገባው ለተጨዋቾች ሳይሆን ለሀኪሞች እና መምህራን ነው “ ጋርዲዮላ
ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ሀኪሞች እና መምህራን ለማህበረሰቡ በጣም አስፈላጊ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ፔፕ ጋርዲዮላ ሲናገሩም “ ዶክተሮች እና መምህራን በማህበረሰቡ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ሰዎች ናቸው “ ሲሉ ተደምጠዋል።
“ ሀኪሞች እና መምህራን በማህበረሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ተከፋይ ሊሆኑ ይገባል “ ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።
አክለውም “ ለተጨዋቾች እና እግርኳስ አሰልጣኞች ሳይሆን ለእነሱ ትልቅ ክፍያ ይገባቸዋል ፤ ማህበረሰቡን የተሻለ የሚያደርጉት እነሱ ናቸው “ ብለዋል።