Bahir Dar kenema Sport club fans

Bahir Dar kenema Sport club fans Welcome to The Official Bahir Dar City Sport Club Page . www.bahirdarcitysc.com

ብሩክ ሙሉጌታ በይፋ የጣና ሞገዶቹን ተቀላቅሏል ...________________________ስም:- ብሩክ ሙሉጌታ የሚጫወትበት ቦታ:- የመስመር አጥቂ የነበረበት ክለብ :- ኢትዮጵያ መድን ኮል...
20/08/2026

ብሩክ ሙሉጌታ በይፋ የጣና ሞገዶቹን ተቀላቅሏል ...
________________________
ስም:- ብሩክ ሙሉጌታ
የሚጫወትበት ቦታ:- የመስመር አጥቂ
የነበረበት ክለብ :- ኢትዮጵያ መድን

ኮልፌ ቀራንዮ፣ በመቐለ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ መድን የተጫወተው የመስመር አጥቂው ብሩክ ሙሉጌታ በይፋ ዛሬ የጣና ሞገዶቹን ተጠናቋል ።

እንኳን ደህና መጣህ
መልካም የወድድር ዘመን ።

ቤልሔም ሽመልስ የግዮን ንግስቶችን ተቀላለቀለች ...._________________________ስም:- ቤተልሔም ሽመልስየምትጫወትቀት ቦታ:- አማካይ የነበረችበት ክለብ :- ሲዳማ አማካይ ተጫዋ...
17/08/2026

ቤልሔም ሽመልስ የግዮን ንግስቶችን ተቀላለቀለች ....
_________________________
ስም:- ቤተልሔም ሽመልስ
የምትጫወትቀት ቦታ:- አማካይ
የነበረችበት ክለብ :- ሲዳማ

አማካይ ተጫዋቿ የቀድሞዋ የፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና ተጫዋች ቤተልሔም ሽመልስ የግዮን ንግስቶችን ተቀላቅላለች።

እንኳን ደህና መጣሽ
መልካም የውድድር ጊዜ

የግዮን ንግስቶቹ በረኛ ወደ ባህር ዳር ተመልሳለች ...._________________________ስም:- ባንችአየሁ ደመላሽ የምትጫወትበት ቦታ :- ግብ ጠባቂ የነበረችበት ክለብ:- ሲዳማ ቡና...
17/08/2026

የግዮን ንግስቶቹ በረኛ ወደ ባህር ዳር ተመልሳለች ....
_________________________
ስም:- ባንችአየሁ ደመላሽ
የምትጫወትበት ቦታ :- ግብ ጠባቂ
የነበረችበት ክለብ:- ሲዳማ ቡና

ባለፈው የውድድር ዓመት በሲዳማ መለያ በተደጋጋሚ የጨዋታ ኮከብ ተብላ የተሸለመች እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂዋ ባንቹ ወደ ፕሪምየር ሊግ ወዳሳደገችው ባሕር ዳር ከነማ ተመልሳ ለመጫወት ተስማምታለች ።

ድል ለግዮን ንግስቶቹ
መልካም የውድድር ዘመን

#ባህርዳር

የኛ ባሕር ዳር ....የኛ ባሕር ዳር በመጨረሻም የብሔራዊ ቡድኑ ከስደት ነፃ አውጭ ሆና  ተገኝታለች ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሐገሩ ላይ ይጫወታል ።
16/08/2026

የኛ ባሕር ዳር ....

የኛ ባሕር ዳር በመጨረሻም የብሔራዊ ቡድኑ ከስደት ነፃ አውጭ ሆና ተገኝታለች ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሐገሩ ላይ ይጫወታል ።

የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የካፍ መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቀደለት። የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ)  መስ...
15/08/2026

የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የካፍ መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቀደለት።

የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቅዶለታል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ) የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም መስፈርቶችን ባለማሟላቱ ዓለምአቀፍ ጨዋታዎችን እንዳያደርግ አግዶት ቆይቷል።

በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሌሎች ሀገራት እንዲጫወት ተገድዶ ቆይቷል። ካፍ የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የዓለም አቀፍ ስታዲዬም ማሟላት የሚገባውን መስፈርት እንዲያሟላ አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።

ባለፉት ዓመታት ስታዲዬሙ የካፍ መስፈርቶችን ባሟላ መልኩ ግንባታ ሲካሄድለት ቆይቷል። አሁን ላይ መስፈርቶችን በማሟላት ማረጋገጫ ተሰጥቶታል።

የአማራ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ መልካሙ ጸጋዬ ለአሚኮ እንደገለጹት ለበርካታ ዓመታት የዓለም አቀፍ ውድድሮች እገዳ ተጥሎበት የቆየው የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገለት ሰፊና ዘመናዊ የሁለተኛ ምዕራፍ የማሻሻያ እና የግንባታ ሥራ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) መስፈርቶችን በማሟላት ለዓለም አቀፍ ውድድሮች ዝግጁ መኾኑ ተረጋግጧል ብለዋል።

ይህ ትልቅ የስፖርት ስኬት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) እና ክለቦች አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ውድድሮችን በሜዳቸው እና በደጋፊያቸው ፊት እንዲያደርጉ ያስችላል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ ወደፊት አበይት የአህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል ብለዋል። ይህ ስኬት በመገኘቱ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን እንዲያደርግ ፈቃድ ማግኘቱ የአማራ ክልል እና የመላው ኢትዮጵያ የስፖርት ቱሪዝም እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በታሪካዊ ፣ በተፈጥሯዊ እና በባሕላዊ የቱሪዝም ሃብቶች ለታደለው የአማራ ክልል ተጨማሪ ሃብት ነው።የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የካፍ መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቀደለት።

የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቅዶለታል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ) የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም መስፈርቶችን ባለማሟላቱ ዓለምአቀፍ ጨዋታዎችን እንዳያደርግ አግዶት ቆይቷል።

በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሌሎች ሀገራት እንዲጫወት ተገድዶ ቆይቷል። ካፍ የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የዓለም አቀፍ ስታዲዬም ማሟላት የሚገባውን መስፈርት እንዲያሟላ አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።

ባለፉት ዓመታት ስታዲዬሙ የካፍ መስፈርቶችን ባሟላ መልኩ ግንባታ ሲካሄድለት ቆይቷል። አሁን ላይ መስፈርቶችን በማሟላት ማረጋገጫ ተሰጥቶታል።

የአማራ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ መልካሙ ጸጋዬ ለአሚኮ እንደገለጹት ለበርካታ ዓመታት የዓለም አቀፍ ውድድሮች እገዳ ተጥሎበት የቆየው የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገለት ሰፊና ዘመናዊ የሁለተኛ ምዕራፍ የማሻሻያ እና የግንባታ ሥራ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) መስፈርቶችን በማሟላት ለዓለም አቀፍ ውድድሮች ዝግጁ መኾኑ ተረጋግጧል ብለዋል።

ይህ ትልቅ የስፖርት ስኬት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) እና ክለቦች አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ውድድሮችን በሜዳቸው እና በደጋፊያቸው ፊት እንዲያደርጉ ያስችላል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ ወደፊት አበይት የአህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል ብለዋል። ይህ ስኬት በመገኘቱ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን እንዲያደርግ ፈቃድ ማግኘቱ የአማራ ክልል እና የመላው ኢትዮጵያ የስፖርት ቱሪዝም እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በታሪካዊ ፣ በተፈጥሯዊ እና በባሕላዊ የቱሪዝም ሃብቶች ለታደለው የአማራ ክልል ተጨማሪ ሃብት ነው።

መረጃው :- የባሕር ዳር ከተማ ኮምንኪኬሽን

ማንያዘዋል ካሳ በጣና ሞገዶቹ ቤት ውሉን አራዝሟል ...._________________________ስም :- ማንያዘዋል ካሳ የሚጫወትበት ቦታ :- ተከላካይ ከከፍተኛ ሊግ ተገኝቶ ያሳለፍነው ዓመ...
15/08/2026

ማንያዘዋል ካሳ በጣና ሞገዶቹ ቤት ውሉን አራዝሟል ....
_________________________
ስም :- ማንያዘዋል ካሳ
የሚጫወትበት ቦታ :- ተከላካይ

ከከፍተኛ ሊግ ተገኝቶ ያሳለፍነው ዓመት በጣናሞገዶቹ መለያ ድንቅ የውድድር ዓመት ማሳለፍ የቻለው ወጣቱ ተከላካይ ማንያዘዋል በባህር ዳር ከነማ ቤት ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ለመቆየት ውሉን አራዝሟል ።

መልካም የውድድር ጊዜ

14/08/2026

😯 ታላቁ ብራንድ ጎፈሬ ቤተሰቡ ለሆኑ የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች የሚጠቀማቸው የማሊያ ላይ የስም እና ቁጥር የፅሁፍ ፎንት ስታይል ይፋ ሆነ! 😯

🔥 ጥራት ላላቸው ደንበኞቻችን ጥራት ያላቸው ምርቶቻችንን ማቅረባችንን እንቀጥላለን! 🔥

አንተህ ተፈራ ውሉን አድሷል ....________________ስም :- አንተነህ ተፈራየሚጫወትበት ቦታ :- አጥቂበጥር የዝውውር መስኮት የጣና ሞገዶቹን የተቀላቀለውና ድንቅ እንቅስቃሴ ያደረገው...
14/08/2026

አንተህ ተፈራ ውሉን አድሷል ....
________________
ስም :- አንተነህ ተፈራ
የሚጫወትበት ቦታ :- አጥቂ

በጥር የዝውውር መስኮት የጣና ሞገዶቹን የተቀላቀለውና ድንቅ እንቅስቃሴ ያደረገው በዓመቱ 7 ጎሎች ማስቆጠር የቻለው አንተነህ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በክለቡ የሚያቆየውን ውል አራዝሟል ።

መልካም የውድድር ጊዜ

13/08/2026

𝗡𝗢𝗪𝗛𝗘𝗥𝗘 𝗪𝗜𝗧𝗛𝗢𝗨𝗧 𝗕𝗔𝗛𝗜𝗥 𝗗𝗔𝗥! 🌊

​ #𝗪𝗘𝗟𝗖𝗢𝗠𝗘𝗣𝗘𝗣𝗘 #𝗕𝗗𝗞𝗙𝗖

ቻርለስ ሙሴንጌ የጣና ሞገዶቹን ተቀላቅሏል ....ስም :- ቻርለስ ሙሴንጌ የሚጫወትበት ቦታ :- አጥቂ የነበረበት ክለብ :- መቻል
13/08/2026

ቻርለስ ሙሴንጌ የጣና ሞገዶቹን ተቀላቅሏል ....

ስም :- ቻርለስ ሙሴንጌ
የሚጫወትበት ቦታ :- አጥቂ
የነበረበት ክለብ :- መቻል

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bahir Dar kenema Sport club fans posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Bahir Dar kenema Sport club fans:

Shortcuts

Share