24/07/2026
💥በየዓመቱ ክረምት ላይ የሚካሄደው የባህር ዳር ከተማ ፉትሳል ውድድር በዚህ ዓመት የስያሜ ለውጥ በማድረግ "የፌደራል ዳኛ ደረጀ አመራ ፉትሳል ውድድር" በሚል እንደሚካሄድ ይታወቃል።
ይህ የፉትሳል ውድድር ቅዳሜ ሀምሌ 18/2018 ዓ/ም የሚጀምር ሲሆን ማህበራችን ከባህርዳር የቀድሞ ተጨዋቾች ጋር የመክፈቻ ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል።
ጨዋታውም ውድድሩ በሚደረግበት ሚሊኒየም ሜዳ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ የሚካሄድ ሲሆን ዋና ዓላማውም የማህበራችንን አባል ፌደራል ዳኛ ደረጀ አመራን ለማስታወስ ይሆናል።
ይህንን ፕሮግራም ላዛጋጁ አካላት ታላቅ ክብርና ምስጋና እናቀርባለን።