01/08/2026
አርሰናል ቡሩኖ ጉማሬሽን ለማስፈረም ሙሉ ስምምነት ላይ ደረሰ።
መድፈኞቹ የኒውካስትሉ ብራዚላዊ የመሐል ሜዳ ተሰላፊ ቡሩኖ ጉማሬሽን ለማስፈረም ሙሉ በሙሉ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ለንደን ኢቭኒንግ ዘግቧል።
እንደ ሜትሮ እና ሚረር ያሉ የመረጃ ምንጮች እንደዘገቡት አርሰናል 70 ሚሊዮን ፓውንድ ለኒውካስትል አስቀድሞ የሚከፍል ሲኾን ከተጫዋቹ እና ከክለቡ ስኬት ጋር የተያያዘ 10 ሚሊዮን ፓውንድ ተጨማሪ ክፍያም በስምምነቱ ውስጥ ተካትቷል።
የፈረንሳዩ ሌኪፕ ጋዜጣ በበኩሉ አርሰናል ጉማሬሽን በ90 ሚሊዮን ዩሮ ለማስፈረም እንደተስማማ መረጃ አውጥቷል።
በግል ጥቅማጥቅ ዙሪያ ቀደም ብሎ ከስምምነት ላይ የደረሰው ተጫዋቹ የመድፈኞች ሦሥተኛው የክረምት ፈራሚ ለመኾን በዚህ ሳምንት ወደ ለንደን ተጉዞ የሕክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
ከቀናት በፊት የኒውካስትል ዩናይትዱ ዋና አሠልጣኝ ከክለቡ ጋር በስምምነት ለመለያዬት የወሰኑት እንደ አንቶኒ ጎርደን እና ሳንድሮ ቶናሊ ያሉ ቁልፍ ተጫዋቾች ክለቡን መልቀቃቸው ሳያንስ የጉማሬሽን መልቀቅ አይቀሬ መኾኑን በመረዳታቸው እንደኾነ ሲነገር ቆይቷል።
ተጫዋቹ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ ስፔን በረራ ካደረገው የኒውካስትል ቡድን ሥብሥብ ውስጥ እንዳልተገኘ እና ዝውውሩን በማጠናቀቅ ላይ መኾኑን ዘጋርዲያን ዘግቧል።
በአድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!