Tadesse Terefe

Tadesse Terefe አዲስ ነገር

17/06/2022
02/04/2022

አስተማሪ አጭር ታሪክ .!

አንድ ቤተሰብ ውስጥ አባት ከሞተ በኋላ የሚመገቡት እስኪያሳስባቸው ድረስ ይቸገራሉ ። አንድ ጌጣጌጥ መሸጫ ሱቅ ያለው ዘመድ አላቸው እና እናትየው ለልጇ ያላትን ለረጅም ጊዜ የተቀመጠ የአንገት እና የጣት ዳይመንድ ጌጥ ሰጥታው እዛ ሱቅ ሄዶ እንዲሸጠው ትሰጠዋለች፡፡

ልጁ የተባለው የዘመድ ጌጣ ጌጥ ሱቅ ሄዶ እናቱ እንደላከችው አስረድቶ እንዲገዛው ይጠይቃል፡፡ ሰውየውም ከመረመረው በኋላ "አሁን ገበያው ወድቋል ትንሽ ግዜ ጠብቀን በጥሩ ዋጋ
እንሸጠዋለን፡፡" ብሎ ይመልስለትና የተወሰነ ገንዘብ ከሰጠው በኋላ ለልጁም እስከዛው በየጊዜው እየመጣ እዛው ሱቅ ስራ እንዲሰራ ያደርጋል ።

ልጁ በየግዜው እየሄደ የጌጣጌጥአሰራር ጥበብ ተካነ ፡፡ የገበያም እውቀት አካበተ በስራውም ታዋቂም ለመሆን ቻለ ፡፡

ይሄኔ ባለሱቁ "የሆነ ግዜ ልትሸጠው አምጠተኸው የነበረውን ጌጥ አሁን አምጣው አሁን ገበያው ጣራ ነክቷል እና ታተርፋላችሁ ፡፡ ብሎ ይልከዋል ፡፡ ልጁ እንደተባለው እቤት ሄዶ ጌጣጌጡን በአይኑ በማየት ብቻ አርቴፊሻል ሆኖ ያገኘዋል፡፡

ወደ ሱቅ ይመለሳል ፡፡ባለቤቱ ይጠይቃል "ዳይመንዱስ ?" ልጁም "አርቴፊሻል ነው ግን እያወክ ያን ጊዜ ለምን አልገርከኝም ?አሁንስ ለምን ላከኝ?ሲል ጠየቀው፡፡ ዘመዱም "ያን ጊዜ ለረጅም ዘመን ዳይመንድ ነው ብላችሁ ያመናችሁትን ነበር ይዘህ የመጣኸው ፡፡ያለምንም እውቀት፤ ባዶህን እና በሙሉ እምነት ብቻ ! በሰዓቱ ባለህበት ሁኔታ ልክ ያልሆነ ነገር ለማስረዳት ይከብዳል፡፡ ምናልባት ላታምኑኝ ትችሉ ነበር ፡፡ምናልባትም ባለመግባባት የሚፈጠሩ የቃላት ልውውጥ አሁን ላይ መጥፎ ስሜት ሊያሳድርብን በቻለ ነበር ።" ብሎ በትህትና መለሰለት፡፡

በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሶስት መጋዘን ያለአግባብ የተከማቸ የምግብ ዘይት ተያዘአዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሶስት መጋዘን ያለአግባብ የተከማቸ የምግብ...
07/03/2022

በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሶስት መጋዘን ያለአግባብ የተከማቸ የምግብ ዘይት ተያዘ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሶስት መጋዘን ያለአግባብ የተከማቸ የምግብ ዘይት በተቋቋመው ግብረሃይል ተያዘ፡፡
የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ሰው ሰራሽ የዋጋ ውድነት በመፍጠርና ምርቶችን በመደበቅ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ህገወጥ ደላሎችንና ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከትናንት በስትያ ጀምሮ ግብረ ሃይል አቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት ግብረሃይሉ እያደረገ ባለው ቁጥጥር በዛሬው እለት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ስሙ ሙሉጌታ መናፈሻ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በህብረተሰቡ ጥቆማ በአራት መጋዘን ውስጥ የምግብ ዘይት ክምችቱን መያዝ ተችሏል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

ዝንጉ አሽከርካሪዎችን የሚከታተለው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓትየአሽከርካሪዎችን ሁኔታ የሚከታተል ካቢን ሴንስ የተባለ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሶፍትዌር በእስራኤሉ ሲፒያ ተቋም መበልፀጉ ...
07/03/2022

ዝንጉ አሽከርካሪዎችን የሚከታተለው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት
የአሽከርካሪዎችን ሁኔታ የሚከታተል ካቢን ሴንስ የተባለ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሶፍትዌር በእስራኤሉ ሲፒያ ተቋም መበልፀጉ ተገለጸ፡፡
ሶፍትዌሩ የአሽከርካሪውን የምልከታ አቅጣጫ፣ የዓይን እርግብግቦሽ ምጣኔ፣ የእንቅልፍ ስሜት እና መዘናጋት ይከታተላል፡፡
በተጨማሪም አሽከርካሪዎች የደህንነት ቀበቶ ማድረጋቸውን፣ የአቀማመጥ ሁኔታ፣ የመኪናውን የመያዝ አቅም እና ተገቢው የህጻናት መቀመጫ መኖር አለመኖሩን የመለየት አቅም እንዳለው ዜድዲኔት ዘግቧል፡፡
ካቢን ሴንስ የተሳፋሪዎችን እድሜ እና ጾታ እንዲሁም በመኪና ውስጥ የሚገኙ ቦርሳ፣ ስልክ እና የመሳሰሉ ቁሶችን መለየት ይችላል፡፡
በዋናነት አሽከርካሪው ላይ ትኩረት ያደረገው ይህ ሶፍትዌር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ኮምፒዩተር ቪዥን በመጠቀም የአሽከርካሪውን አሁናዊ ሁኔታ እንደሚከታተል ተመላክቷል፡፡
በዓለም ጤና ድርጅት የ2021 (እ.ኤ.አ) መረጃ መሠረት በዓለም ዙሪያ በየዓመቱ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች በመንገድ ትራፊክ አደጋዎች ይሞታሉ፡፡ ከአደጋዎቹ ምክንያቶቹ መካከል የአሽከርካሪዎች ትኩረት ማነስ አንዱ ነው፡፡

 #መረጃ ለባህር ዳር ነዋሪዎች በሙሉ፦የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር  በነገው ዕለት በሁሉም  ክፍለ ከተሞች በተመጣጣኝ ዋጋ የዘይት ስርጭት ያካሄዳል።መንግስት  በአገራችን የተከሰተው የኑሮ ው...
07/03/2022

#መረጃ ለባህር ዳር ነዋሪዎች በሙሉ፦
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተመጣጣኝ ዋጋ የዘይት ስርጭት ያካሄዳል።
መንግስት በአገራችን የተከሰተው የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት የተለያዩ ሥራወችን በመስራት ላይ የሚገኝ ቢሆንም በህብረተሰቡ ላይ ያለው ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው።በተለይም ደግሞ በምግብ እህሎችና የምግብ ዘይት ላይ የዋጋ ጭማሪ ተከስቷል። መንግስት ይህንን ለማረጋጋት ከሚያደረገው እንቅስቃሴ በተጨማሪ ችግሩን ለመቀነስ በከተማ አስተዳደሩ ሁለት መሠረታዊ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ።
ይኸውም.....
1ኛ/ የባህር ዳር ከተማ አስተዳድር ከንቲባ ኮሚቴ በአደረገው አስችኳይ ስብሰባ እንደ ከተማ አስተዳደር ለሸማቾች ህብረት ስራ ዩኒየን 10 ሚሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ብድር በጀት በመመድበ ፣የግብርና ምርቶችና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተለይም መሠረታዊ የፍጁታ ዕቃዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ ሥራ የተሠራ ሲሆን በተመጣጣኝ ዋጋ ምግብ የሚሸጡ ቢያንስ በሶስት ክፍለ ከተሞች የቀበሌ ምግብ ቤቶችንና ስጋ ቤቶችን እንዲከፍቱ ድጋፍ እየተደረገ ነው።
2ኛ/ በበላየነህ ክንዴ ለከተማችን የሚቀርበው የፊቤላ ዘይት በወቅቱና በበቂ መጠን እየቀረበ ባለመሆኑ ከክልሉ ንግድ ቢሮ ጋር በመነጋገር 883,000 ሊትር ፓልም ዘይት ከውጭ ተገዝቶ በአለ በጅምላ በኩል ቀርቧል። በመሆኑም በነገው ዕለት በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የዘይት ስርጭት ያካሄዳል።
ስለሆነም መንግስት ከሚያደርገው የቁጥጥር ሥራ በተጨማሪ አቅርቦቱ ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ስለሆነ የከተማችን ነዋሪዎች በተፈጠረው ያልተገባ የዋጋ ንረት ያላስፈላጊ ወጭ እንዳትዳረጉ ከተማ አስተዳደሩ በጥብቅ እያሳሰበ ለሚደረገው የህግ ማስከበር ሥራ አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉ ጥሪውን ያስተላልፋል።
#የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር

04/03/2022
vacancy
26/02/2022

vacancy

25/02/2022

ሁላችንም የማለዳ ኮከቦች ላይ የምናውቃት እመቤት ካሳ እኔ ጋር አድሮ ሱሪዉን ለብሶ ቡታታዉን እረስቶት ሔዴ ትለናለች

22/02/2022
21/02/2022

ተነስ!

ሰበብ አታብዛ! ከእንቅልፍ መነሳት ካለብህ አሁኑኑ ተነስ አልጋ ውስጥ እየተገላበጥክ ምንም አትፈጥርም። መስራት ያለብህ ነገር ካለ ተነስና ስራ፤ መሄድ ያለብህ ቦታ ካለ በኋላ እሄዳለው አትበል። ዛሬን ሳትጨርስ ነገን እንዳትጀምር! ለዛሬ ያሰብካቸውን ሁሉ መፈፀም አለብህ።

አለበለዚያ ሰበብ ስታበዛ መኖር ከባድ ሸክም ሆኖብህ ባልህበት እየረገጥክ ቆመህ ትቀራለህ! አደርጋለው ያልከውን በጥንካሬ የምታደርግ ከሆነ ግን ህይወት ቀላልና አጓጊ ትሆናለች። ሰበብን ለሰነፎች ተውላቸው ያንተ ፀባይ አይደለም ወዳጄ!

የሚደንቅ ሰኞ ተመኘንላችሁ🙏

Address

Bahir Dar
Bahir Dar

Telephone

+251932836039

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tadesse Terefe posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tadesse Terefe:

Share

Category