Gabbi rasuk Leeda Ku/buxa ገቢ ራሱ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Awash
  • Gabbi rasuk Leeda Ku/buxa ገቢ ራሱ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት

Gabbi rasuk Leeda Ku/buxa ገቢ ራሱ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት Alhamdulillah

ሣምንታዊ መልዕክት!የፓርቲያችን አመራሮችና አባላት የሕዝብ አገልጋይነታቸውን በተጨባጭ ውጤት ማረጋገጥ አለባቸው።የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ የውይ...
29/07/2026

ሣምንታዊ መልዕክት!

የፓርቲያችን አመራሮችና አባላት የሕዝብ አገልጋይነታቸውን በተጨባጭ ውጤት ማረጋገጥ አለባቸው።

የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ የውይይት መድረክ ባሳለፍነው ሳምንት ከሀምሌ 13 እስከ 15/2018 ዓ.ም ተከታታይ ቀናት በስፋት ተካሂዷል። በዚህ መድረክ የአፈጻጸም ውጤቶችን በጥልቀት ተገምግሟል፤ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በኑሮ ውድነት ቅነሳና ገበያ ማረጋጋት ዙሪያ በንቅናቄ የተከናወኑ አበይት ተግባራት ውይይት ተደርጎባቸዋል፤ በቀጣይም የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የትኩረት አቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል።

2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ነፃና ተዓማኒ የሆነውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ያካሄደችበት ነው። ፓርቲያችን ብልፅግና ይህ ታሪካዊ ስኬት በዋናነት በመምራት አንፀባራቂ ድል ያስመዘገበ ሲሆን በመራጩ ህዝብ ዘንድ ባገኘው ቅቡልነትም ሀገርንና ህዝብን ለቀጣይ 5 ዓመታት የመምራት እድል አግኝቷል።

2019 በጀት ዓመት ደግሞ መራጩ ህዝብ የሰጠውን ታሪካዊ ኃላፊነት መወጣት የምንጀምርበት፤ ህዝቡ በተለያዩ ጊዜያት የሚያነሳውን የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና ሌሎች ጥያቄዎችን ለመፍታት በትጋት የምንሰራበት እንዲሁም ፓርቲያችን የጀመራቸውን የልማት ኢኒሼቲቮች ስኬት በይበልጥ የምናረጋግጥበትና የዜጎችን ተጠቃሚነት የምናረጋግጥበት ነው። ለዚህ ስኬት ደግሞ የላቀ የአመራርና አባላት ቁርጠኝነት፤ የህዝብ የነቃ ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል።

በ2018 በጀት ዓመት በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በገበያ ማረጋጋትና በኑሮ ውድነት ቅነሳ ዙሪያ የተከናወኑ ስራዎች የፓርቲያችን አቅጣጫ ትክክለኛ መሆኑን ያረጋገጡ ናቸው። በሁሉም ክልሎች በተፈጠሩ የስራ ዕድሎች፣ በምርት አቅርቦት መጨመር፣ በገበያ ማረጋጋትና በሕዝቡ የኑሮ ሁኔታ ላይ የተመዘገቡ መሻሻሎች የፓርቲያችን የሕዝብ ተጠቃሚነትን ያማከለ ፖለቲካ ውጤቶች ናቸው።

ይሁን እንጂ የተገኙት ውጤቶች የጉዟችን መጨረሻ ሳይሆኑ የቀጣይ ከፍተኛ ስኬት መነሻዎች ናቸው። ከሀገራችን አቅምና ከሕዝባችን ፍላጎት አንጻር ገና ብዙ ሊሰራ የሚገባ ስራ አለ። በመሆኑም በየደረጃው ያለው አመራር የሕዝብን ችግር ዋና የስራ አጀንዳው በማድረግ የተጀመሩ ለውጦችን ወደ ከፍተኛ ውጤት ማሸጋገር አለበት።

የስራ ዕድል ፈጠራና የኑሮ ውድነት ቅነሳ የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ዘርፍ ብቻ ኃላፊነት አይደሉም። እስከ ቀበሌ ድረስ በሁሉም የፓርቲ አደረጃጀቶች፣ በመንግሥት ተቋማትና በሕዝቡ የተቀናጀ እንቅስቃሴ ሲኖር ብቻ ዘላቂ ውጤት ማስመዝገብ ይቻላል።

በቀጣይ የእያንዳንዱን አካባቢ እምቅ አቅም በአግባቡ በመጠቀም፣ የሕዝብ ተሳትፎንና ባለቤትነትን በማጠናከር፣ ከአሰራር፣ ከአመለካከትና ከአስተሳሰብ ጋር የተያያዙ ማነቆዎችን በመፍታት የብልፅግናን ጉዞ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ማሸጋገር አለብን።

በተለይም የፓርቲያችን አመራሮችና አባላት የሕዝብ አገልጋይነታቸውን በተጨባጭ ውጤት ማረጋገጥ አለባቸው። ሕዝባችንም በልማት ስራዎች የጀመረውን ንቁ ተሳትፎና ባለቤትነት በቀጣይነት በማጠናከር የሀገራችንን የብልፅግና ጉዞ የበለጠ እንዲፋጠን የበኩሉን ሚና መወጣት ይጠበቅበታል።

በ2019 በጀት ዓመት የተቀመጡትን ዕቅዶች ከግብ ለማድረስ በአንድነት፣ በቅንጅት፣ በተጠያቂነትና በውጤት ተኮር አሰራር መስራት ይገባል። የሕዝባችንን ተስፋ ወደ ተጨባጭ ውጤት፣ የሀገራችንን አቅም ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና ለመቀየር ሁላችንም በላቀ ቁርጠኝነት ልንረባረብ ይገባል።

ብልፅግና ፓርቲ
ሀምሌ 20/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

29/07/2026
በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር 800 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል የሚያስችል ዝግጅት ተጠናቋልአዲስ አበባ፤ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ) :-በዘንድሮው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ...
29/07/2026

በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር 800 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል የሚያስችል ዝግጅት ተጠናቋል

አዲስ አበባ፤ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ) :-በዘንድሮው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር 800 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሀምሌ 27 ቀን 2018 በሚካሄደው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር 800 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ይፋ አድርገዋል።

በመልዕክታቸውም አምስት ቀናት በቀሩት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር መላው ኢትዮጵያውያን ታሪካዊ አሻራቸውን ለማሳረፍ እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈፃሚና የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የቴክኒክ ኮሚቴ ጸሐፊ ፋኖሴ መኮንን ለኢዜአ እንዳሉት፤ በዘንድሮ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር 8 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተግባር እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡

በዚህም በማህበረሰቡ የነቃ ተሳትፎና ቁርጠኝነት እስካሁን 4 ነጥብ 8 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ጠቁመዋል፡፡

በአረንጓዴ ዐሻራ የሚተከሉ ችግኞች 40 በመቶ ሀገር በቀል ለደን ልማት እንዲሁም 60 በመቶ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡

የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ሰፊ ህዝብ በማሳተፍና ትብብርን በማሳየት ጎልቶ እንደሚታይ በመግለጽ፤ ለዘንድሮው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል ብለዋል።

የችግኝና ጉድጓድ ዝግጅት፣በዕለቱ ለችግኝ መትከያ በተለዩ ቦታዎች /Georeference/ ላይ መትከል የሚያስችል ዝግጅት ማድረግ፣ ችግኞችን ወደ ሚተከሉበት አካባቢ ማድረስ እና ባለሙያዎች የማብቃት ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በአንድ ጀምበር መርሃ ግብሩ 800 ሚሊዮን ችግኞች የሚተከሉባቸው ከ290 ሺህ ሄክታር መሬት የሚሸፍኑ ከ10 ሺህ በላይ ቦታዎች እንደተለዩ ገልጸው፤ በዕለቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬና የቡና ችግኞች በብዛት ይተከላሉ ብለዋል፡፡

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር የግብርናን ዘርፍ ምርታማነት ከማሳደግ ባለፈ ግድቦች በደለል እንዳይሞሉ በማድረግ ለመስኖ ልማት የሚውል በቂ ውሀ ለመፍጠር እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ከዚህ ቀደም በአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ የነበራቸውን የነቃ ተሳትፎ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ችግኝ ተከላ ላይ እንዲደግሙት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

29/07/2026
Chifra^Daaqaral Wakti Caalat Wagsiisak Ayyuntallk walal GexsenAwasi Rasuk Chifra^ Daaqaral Wakti caalatal Ayyunti Exaaxi...
29/07/2026

Chifra^Daaqaral Wakti Caalat Wagsiisak Ayyuntallk walal Gexsen

Awasi Rasuk Chifra^ Daaqaral Wakti caalatal Ayyunti Exaaxilluk Walal Gexsen

Ta Gudgudul Geytimteh Tan Ayyunti Dagorti Ayyunti Isi Caddol Saay Kee Salaam Diggoosak Gexaanam kee madaqa^ dagarraaqah Rammitak waagisaanam tannah yan Gudgud fanah Baahak Doolat kee Ummatta bagu kee Boor Tikka inteh taamitaanam faxaanamay Qadosen

baxaabasa Le mablooli Acayuk Ayyuti Salaam Kee Saay diggoosak Daddos kee Biso^ maxocy Qibisneh Nani digoosak Gexenno iyyen

Qafar Agatih Ramaakayih Doolatlak xiinissoh Abba ajji Awwal Qarba tama Gudguduk Amoggacasal Geytimak Ayyunti Saay Kee Salaam Diggoyak Isinni Dariifal Salaam Kee saay Diggoosak Gexaanam faximtaay iyye

Ayyunti Salaam Darraqootuh Irooyo Addal Tangiicille Ganeenit Kee Umam Abenitil Doolat Gaanun Dagarraq Diggosak Gexe Loonum kee Ganuun Dagarraq Digoowuh Chifrah Ayyonti Abah yan Macalah kulsa le Gadda Keenih Gacasay iyye

Uamam Abeenit Daalaay kedo kee Buxa^ mariyyol madaqa^Dagarraaqak Isinni umaane Rebisoonuh Abaanah yanin Uma taamoomi Ayyunti Aakamal Cedak Umam Abeenit Isinni Addak Ayyaaquk Madaqal kah Esseriman innah Abaanam kaxxa taamay iyye

Chifrah Ayyunti loonuh yanin Inkittiino Diggoysak Qimiseenih Yanin Dadal Kee daddos taama maqarosak Gexanam faximmtay iyye

Ella cabol masakaxxale Cajji Awwal Qarba iyyemih

Doolat ginniime waqdi akah ginnimeemik Qembo Sabab:-Umatta Salaam dacrisu kinni,
Umeyni kedo mali, yeelle kaak tekkek,
1. Umaanet kaaluk yenegel mara kedo kaak,
2. Umaane Malat kaa luk yengele mara kedo kaak, tonna kinnuk
Sifrah Ummattak Salaam xiq kee xaqamu tubleenih, Salaam dacrisa,
salaam dacayrih Masuuliyat kulli numih amol yan, toomeemil Gaanuunuk daga raaaqa num miyan, kulli num gaanunuh gubat xiinam ixiga, Nasabah, reedah, mango kedo leh, gaanun elle abbinoowe wayu waa num inkinnah miyana.
le Qakli, le Abbah migaq, leh yan yallak meesi xiinise wayya hayte mara xiinissam Ghaanunuy, doolat akah ginniimem kaadu too mara.

"Kedok orban Doolat yani

Asakih ayro 21/11/2018 L.L.L  gabbi rasuk awash fantiqele daqaaral  incetive tamom kee abaxsaluk culekal wagitamal barri...
28/07/2026

Asakih ayro 21/11/2018 L.L.L gabbi rasuk awash fantiqele daqaaral incetive tamom kee abaxsaluk culekal wagitamal barrile walal abak doolat girari gabbat le culekalah adoytit ekitanuk difaqafan culsanamal ,rakakay doolatih yontocowemeh yan afkanak uguttak rakakay culekal samilsanamih tama elle uddurut gaba kalanamal sittageyak meqenal gabba kallite

Gabbi rasuk Leeda Ku/buxa ገቢ ራሱ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት

26/07/2026
24/07/2026
22/07/2026

Address

Awash
7240

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gabbi rasuk Leeda Ku/buxa ገቢ ራሱ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share