05/11/2022
መስማት የሚፈልጉትን ብቻ እንድትነግርዋቸው የሚፈልጉ ብዙዎች ናቸው። እነርሱ የሚያስቡትን ካላወራችሁ እናንተ ስህተተኞች ናችሁ። እነርሱ አረንጓዴና ቀይ ቀለም ከወደዱ እናንተ ቢጫ የመውደድ መብት የላችሁም፤ እንደውም ቢጫ የሚባል ቀለም የለም ሁሉ ሊልዋችሁ ይችላሉ። እናንተ እንጂ እነሱ ምንም የማለት መብት አላቸው። እነርሱ ያሰቡትን፥ እነርሱ የሚፈልጉትን ካላላችሁ እናንተ ልክ ብትሆኑም እንኳ ልክ አይደላችሁም። እንደ አህያ መልክ አንድ አይነት በሚዘመርበት "እኔን" ሆኖ መቆም በኛ ሀገር ኃጢአት ነውና።
ኤፍሬም ስዩም
የይሁዳ ድልድይ እና ሌሎች ሃሳቦች
ገጽ:-72