Ethio Sport 343 ኢትዮ ስፖርት 343

Ethio Sport 343 ኢትዮ ስፖርት 343 "Join the Ethio Sport 343 family for the latest, breaking sports news along with in-depth analysis." ወቅታዊና ትኩስ ስፖርታዊ መረጃዎች ወደ እናንተ እናደርሳለንደርሳለን

ጋሞ ጨንቻ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ መሳተፉ ለፕሪሚየር ሊግ ዝግጅቱ የጎላ አስተዋፆ እንደሚኖረው ተገለፀለ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ዝግጅቱን በይፋ የጀመረው ጋሞ ጨንቻ...
04/09/2026

ጋሞ ጨንቻ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ መሳተፉ ለፕሪሚየር ሊግ ዝግጅቱ የጎላ አስተዋፆ እንደሚኖረው ተገለፀ

ለ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ዝግጅቱን በይፋ የጀመረው ጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ መሳተፉ የቡድኑን ወቅታዊ ቁመና ለመመዘንና ለሊጉ ብቁ ሆኖ ለመቅረብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገለፀ፡፡

ከመስከረም 9 እስከ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚካሄደው በዚሁ 20ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ውድድር ላይ ጋሞ ጨንቻ እና አዳማ ከተማ በክልል ተጋባዥነት የሚሳተፉ ሲሆን፤ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ መቻል፣ ኢትዮጵያ መድን፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ካሉ የዋና ከተማዋ ጠንካራ ክለቦች ጋር የሚፎካከሩ ይሆናል።

የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ማቴዎስ ለማ እንደተናገሩት፣ ቡድኑን በፕሪሚየር ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ለማድረግ የነባር ተጫዋቾችን ውል ከማደስ ባለፈ ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ አዳዲስ ተጫዋቾችን በመቀላቀል በቀን ሁለት ጊዜ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ስልጠናዎችን እየሰጡ ይገኛሉ።

አሰልጣኙ አክለውም ይህ ውድድር የቡድናቸውን ዝግጅት ለማጠናከር መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥርላቸው ጠቁመዋል።

ምክትል አሰልጣኝ አበው ታምሩ በበኩላቸው ለሊጉ የሚመጥኑ ነባርና አዳዲስ ተጫዋቾችን በማቀናጀት ጥሩ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ገልፀው፣ ለክለቡ እየተደረገ ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍና ክትትል የሚበረታታ በመሆኑ በቀጣይ የውድድር ዘመን ጠንካራ ጋሞ ጨንቻን ለማሳየት ትልቅ ጉጉት እንዳላቸው ተናግረዋል።

የቡድኑ አንበል ወርቅይታደስ አበበ ከዝግጅቱ አስቀድሞ የተሰጠው የስነ-ልቦና ስልጠና በተጫዋቾች ዘንድ ከፍተኛ ተነሳሽነት መፍጠሩን ጠቅሶ፣ የከተማው ዋንጫ ውድድር የቡድኑን አሁናዊ ደረጃ ለመገምገምና ለፕሪሚየር ሊጉ በቂ ዝግጅት ለማድረግ የሚረዳ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ክለቡን የተቀላቀሉት አዳዲስ ተጫዋቾችም በጥሩ ተነሳሽነት ከቡድኑ ጋር በመቀናጀት በቀጣይ የውድድር ዘመን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ብርቱ ጥረት እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

20ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ውድድር መስከረም 9 በአዲስ አበባ ስታዲም በይፋ ይጀመራል።
GAMO TV
በዮሐንስ ባይሳ

ጋብርኤል ማርቲኔሊ በይፋ የአል ሂላል  ተጨዋች ሆነ*********ብራዚላዊው አጥቂ  ጋብርኤል ማርቲኔሊ ወደ ሳዑዲ ፕሮ ሊግ በማምራት የአል ሂላል ተጨዋች ሆኗል።የ25 ዓመቱ ማርቲኔሊ ከ7 ዓመ...
03/09/2026

ጋብርኤል ማርቲኔሊ በይፋ የአል ሂላል ተጨዋች ሆነ
*********

ብራዚላዊው አጥቂ ጋብርኤል ማርቲኔሊ ወደ ሳዑዲ ፕሮ ሊግ በማምራት የአል ሂላል ተጨዋች ሆኗል።

የ25 ዓመቱ ማርቲኔሊ ከ7 ዓመት የሰሜን ለንደን ቆይታ በኋላ ከክለቡ ጋር ተለያይቷል። በመድፍኞቹ ቤተ ቆይታው 278 ጨዋታዎችን አድርጎ 62 ግቦችንም አስቆጥሯል።

በ60 ሚሊዮን ፓውንድ የአል ሂላል ንብረት የሆንው ማርቲኔሊ የአርሰናል ሪከርድ ዝውውርም ሆኖ ተመዝግቧል።

3.46 ቢሊዮን ፓውንድ በማውጣት አዲስ ክብረወሰን ያስመዘገበው ፕሪሚየር ሊጉየእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በይፋ ተዘግቷል። ሊጉ ለ2ኛ ተከታታይ ዓመት አዲስ የዝውውር ክብረወሰን ያስመዘገበበት ሆኗ...
02/09/2026

3.46 ቢሊዮን ፓውንድ በማውጣት አዲስ ክብረወሰን ያስመዘገበው ፕሪሚየር ሊጉ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በይፋ ተዘግቷል። ሊጉ ለ2ኛ ተከታታይ ዓመት አዲስ የዝውውር ክብረወሰን ያስመዘገበበት ሆኗል።

በእግር ኳስ ዝውውር ታሪክ ከተፈጸሙ 10 ታላላቅ ዝውውሮች ሦስቱ በዚህ የዝውውር መስኮት ውስጥ መሆኑ ሪከርዱ እንዲሰበር ምክንያት ሆኗል።

ኢንዞ ፈርናንዴዝ፣ ሞርጋን ሮጀርስ እና ኢሊዮት አንደርሰን ከፍተኛውን የዝውውር ዋጋ የያዙ ሲሆነ ፕሪሚየር ሊጉ 3.46 ቢሊዮን ፓውንድ በማውጣት አዲስ ክብረወሰን ያስመዘገበበት ሆኗል።

አርሰናል ተከታታይ ድሉን አሳክቷል ! በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሃግብር ከሜዳው ውጪ አስቶን ቪላን የገጠመው አርሰናል 1ለ0 አሸንፏል።በቪላ ፓርክ በተከናወነው ተጠባቂ ጨዋ...
31/08/2026

አርሰናል ተከታታይ ድሉን አሳክቷል !

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሃግብር ከሜዳው ውጪ አስቶን ቪላን የገጠመው አርሰናል 1ለ0 አሸንፏል።

በቪላ ፓርክ በተከናወነው ተጠባቂ ጨዋታ ቡካዮ ሳካ የአርሰናልን ድል ያረጋገጠች ግብ አስቆጥሯል። እንግሊዛዊ የፊት መስመር ተጫዋች የውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ግብ ሆኖ ተመዝግቦለታል።

አዲስ አዳጊው ኮቨንትሪ ሲቲን በማሸነፍ ውድድሩን የጀመረው ያለፈው ዓመት የሊጉ ዋንጫ ባለቤት አርሰናል ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን አሳክቷል።

የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታም 250ኛ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታውን መርቷል።

በብራይተን 4ለ0 ተሸንፎ የጀመረው አስቶን ቪላ ዛሬም ነጥብ ማግኘት አልቻለም። የኡናይ ኤሜሬ ቡድን በሁለቱም ጨዋታ ግብ ሳያስቆጥር ወጥቷል።

አርሰናል በቀጣይ አጀማመሩን ያሳመረው ቼልሲን በኤምሬትስ ይገጥማል። አስቶን ቪላ በበኩሉ አዲስ አዳጊው ሀል ሲቲን ይፋለማል።

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው “ኢትዮ ፋይት ናይት” የተሰኘው አለም አቀፍ የፍልሚያ ውድድር፣ የውድድሩን ይፋዊ የፍልሚያ ካርድ ይፋ ማድረጉ ተገለጸ።በዚህ በ...
31/08/2026

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው “ኢትዮ ፋይት ናይት” የተሰኘው አለም አቀፍ የፍልሚያ ውድድር፣ የውድድሩን ይፋዊ የፍልሚያ ካርድ ይፋ ማድረጉ ተገለጸ።

በዚህ በጉጉት በሚጠበቀው ታላቅ የፍልሚያ ምሽት በአጠቃላይ በ5 የተለያዩ የንክኪ ስፖርት ዘርፎች — በኤምኤምኤ (MMA)፣ በቦክሲንግ፣ በኪክ ቦክሲንግ፣ በሙአይ ታይ እና በዉሹ ሳንዳ — 10 አስደናቂ ፍልሚያዎች እንደሚካሄዱ ታውቋል።

የዕለቱ ዋነኛ ትኩረት የሚስበውና በዋና ፍልሚያነት የተያዘው የኤምኤምኤ (MMA) ግጥሚያ ሲሆን፣ ቢንያም ሽብሬ (ቢኒ) ከአገረሰላም አርባ (ቦንጆ) ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ ከፍተኛ የደጋፊዎች ትኩረት ስቧል።

በተጨማሪም በሁለተኛ ዋና ፍልሚያ (2nd Main Event) ጆአዎ ፍሊፕ ኔቶ (ሚሞሴ) ከ ጆሴ አጉስቲን ጂሜኔዝ ጋር በኤምኤምኤ የሚፋለሙ ሲሆን፤ በሦስተኛው የኤምኤምኤ ፍልሚያ ደግሞ GARCIA PINTO (አናኮንዳ) ከ JEFFERSON COSTA (ሱፐር ቾክ) ጋር እንደሚገናኙ ተረጋግጧል።

በሌላ በኩል በኪክ ቦክሲንግ ዘርፍ በሚካሄደው አራተኛ ፍልሚያ ክብሮም ንጉሴ (ዘ ፕሪዴተር) ወደ መድረክ እንደሚወጣ ታውቋል።

ውድድሩን በተመለከተ ተጨማሪ አዳዲስ መረጃዎች እንደደረሱን ወደ እናንተ ማድረሳችንን እንቀጥላለን።

" ለዝውውር በር አልዘጋንም “ ማይክል ካሪክየማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ከጨዋታው በኋላ ስለ ዝውውር ተጠይቀው ነበር።“ እስካሁን በፈረሙ ተጨዋቾች ደስተኛ ነኝ "ያሉት ማይክ...
30/08/2026

" ለዝውውር በር አልዘጋንም “ ማይክል ካሪክ

የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ከጨዋታው በኋላ ስለ ዝውውር ተጠይቀው ነበር።

“ እስካሁን በፈረሙ ተጨዋቾች ደስተኛ ነኝ "ያሉት ማይክል ካሪክ አሁን የተሻለ ስብስብ አለን በማለት ተናግረዋል።

ራሽፎርድን እንደ አዲስ ፈራሚ እንደሚመለከቱት የገለፁት ካሪክ " አሁንም በራችንን አልዘጋንም ነገርግን መጠበቅ አለብን " ብለዋል።

በተጠባቂው ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኡጋብዳው ካዌምፔ ሙስሊም ጋር ይገናኛልበሩዋንዳ ኪጋሊ እየተካሄደ በሚገኘው የ2026 የአፍሪካ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን (CECAFA) ማጣ...
29/08/2026

በተጠባቂው ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኡጋብዳው ካዌምፔ ሙስሊም ጋር ይገናኛል

በሩዋንዳ ኪጋሊ እየተካሄደ በሚገኘው የ2026 የአፍሪካ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን (CECAFA) ማጣሪያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በግማሽ ፍፃሜው ጨዋታ ካዌምፔ ሙስሊም (ኡጋንዳ) ጋር ይገናኛል።

ንግድ ባንክ ከምድቡ በሁለተኛነት የጨረሰ ቢሆንም፣ ከሁሉም ምድቦች በምርጥ 2ኛነትን በመያዝ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።

በግማሽ ፍፃሜው መልሶ የምድብ ተጋጣሚው ከነበረችው ካዌምፔ ሙስሊም (ኡጋንዳ) ጋር ዛሬ ቀን 8፡00 ሰዓት ላይ ይገናኛል።

በምድብ ጨዋታ የታየውን ክፍተት አርሞ በዛሬው ጨዋታ ድል በማስመዝገብ ወደ ፋይናል እንደሚሸጋገር እና ሀገራችንን በድጋሚ በዋናው የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ መድረክ እንደሚያኮራ ሙሉ እምነት አለን።

ይህ ውድድር ሶሻል ሚዲያው በፈጠረላቸው ዕድል ሜዳው ተመቻቸ ብለው ያለ ፀጋ በረከታቸው በየቦታው እየደፈሩ ላስቸገሩ የዚህ ዓለም ወገኖች ጥሩ ትምህርት የሚሰጥ ነው  ።ሊበረታታ የሚገባ ጅምር ...
28/08/2026

ይህ ውድድር ሶሻል ሚዲያው በፈጠረላቸው ዕድል ሜዳው ተመቻቸ ብለው ያለ ፀጋ በረከታቸው በየቦታው እየደፈሩ ላስቸገሩ የዚህ ዓለም ወገኖች ጥሩ ትምህርት የሚሰጥ ነው ።

ሊበረታታ የሚገባ ጅምር ETFCም የማርሻል አርት አለም ጆኒ ከላቀ ስፖርታዊ ጨዋነት ጋር ሴዶን ቃሉ ያንሰዋል ፎጣ አስጥሎ ዘርሯል ።

ሁሉን አዋቂ ተንታኝ ገሳጭ መከሪና በየሰው ትከሻ የሚንጠላጠል በበዛበዘት በዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ዓለም መንቀዝቀዥ ሴዶን እንደ እንደሚያደርግ ማወቅ ልቦና ላለው ወገን ትክክለኛዋ መልዕክት ነው ።

እናም ሴዶ እንደ ክኖር ማክሬገር እና ጄክ ፖል ከሪንጉ መሃል ያ ጉራ ሁሉ ተንፍሶ መታየት ዕጣፈንታው ሆኗል ።

ይህ ከሽቀላው በተጓዳኝ ሶሻል ሚዲያው በፈጠረላቸው ዕድል ሜዳው ተመቻቸ ብለው ያለ ፀጋ በረከታቸው በየቦታው እየደፈሩ ላስቸገሩ የዚህ ዓለም ወገኖች ጥሩ ማሳያው ነው ።

ዋናው ቁም ነገር ደግሞ ክብርት ከንቲባዋ ጭምር በታደሙበት መድረክ መንግስት ስፖርቱን በሁሉም ዘርፍ ለማሳደግ እያካሄደ ባለው ጥረት በተለይ በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በኩል እየተካሄዱ ያሉ እንቅስቃሴዎች የሚደነቁ ናቸው ።

የመዲናይቱን ወጣቶች በተፈጠሩ አማራጭ ምቹ የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎች መሃከል ያነቃቁም ናቸው ።

ዝምተኛው ገዳይ ጆኒ ሰዶን በበቃኝ አሸነፈውአገሪቱን በጉጉት አሳስሮ የሰነበተው የታሪኩ ባለቤት ጆኒ፣ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተካሄደው የ ETFC 2 ዋና ፍልሚያ ላይ ተጋጣሚውን ሴዶን...
28/08/2026

ዝምተኛው ገዳይ ጆኒ ሰዶን በበቃኝ አሸነፈው

አገሪቱን በጉጉት አሳስሮ የሰነበተው የታሪኩ ባለቤት ጆኒ፣ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተካሄደው የ ETFC 2 ዋና ፍልሚያ ላይ ተጋጣሚውን ሴዶን በማሸነፍ አዲሱ የቻምፒዮንነት ዘውድ ደፍቷል!

ውድድሩ እንዲህ ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጠውና መላው ኢትዮጵያዊ እንዲናፍቀው የአንበሳውን ድርሻ የተወጣው ሴዶ «በቀሉ በቀሉ ቀንሽ ደረሰ» እያለ ያሳየው ተወዳጅነትና ለውድድሩ የሰጠው ድምቀት የሚደነቅ ነበር። ይሁን እንጂ ጆኒ በስፖርቱ ክብር የሚገባው፣ የላቀ የኤምኤምኤ (MMA) ቴክኒክ የታጠቀ እና ማንኛውንም ተጋጣሚ በሰከንዶች ውስጥ ከውድድር ውጭ የማድረግ ትልቅ አቅም ያለው ከባድ ሰው መሆኑን አስመስክሯል።

በስፖርቱ ዓለም የማይረሳ ታሪክ የጻፈው ጆኒ፤ እንኳን እንኳን ደስ አለህ ፣እንኳን ደስ አላችሁ!

ሰዶን ያላችሁ እስኪ እንያችሁ?
27/08/2026

ሰዶን ያላችሁ እስኪ እንያችሁ?

Address

Arbaminch
Arba Minch'
****

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Sport 343 ኢትዮ ስፖርት 343 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share