Red Zala Sport

Red Zala Sport Welcome to the Red Zala Sport page.
(16)

ጅላሉ በሜዳ ውስጥ በሚያሳየው የላቀ ብልሃት የመከላከል ጥበብ እና የጨዋታ አዛዥነት የማሊያን ትርጉም በተግባር የሚያሳይ ድንቅ ኮከብ ነው።የጅላሉ የጨዋታ ዘይቤ እና ሜዳ ላይ የሚያሳየው ረቂቅ...
29/08/2026

ጅላሉ በሜዳ ውስጥ በሚያሳየው የላቀ ብልሃት የመከላከል ጥበብ እና የጨዋታ አዛዥነት የማሊያን ትርጉም በተግባር የሚያሳይ ድንቅ ኮከብ ነው።

የጅላሉ የጨዋታ ዘይቤ እና ሜዳ ላይ የሚያሳየው ረቂቅ ብቃት የሜዳው ማርሽ ቀያሪ ነው እሱ ተከላካይ ብቻ አይደለም የጨዋታው ደራሲም የተጋጣሚን የማጥቃት ወረራ አስቀድሞ በማንበብ አደጋዎችን ሳይፈጠሩ የማክሸፍ እና ኳስን አረጋግቶ ወደ ማጥቃት የመቀየር ጥበብ ባለቤት ነው።

በአንድ ለአንድ ፍልሚያዎች በአየር ላይ ኳሶች እና በተደረቡ ኳስ መቆጣጠር ላይ ያለው የበላይነት የተከላካይ ክፍሉን ፍጹም ያደርገዋል።

ጅላሉ ካለ የተከላካይ ክፍል ተረጋግቶ እና ተማምኖ ይጫወታል እሱ አጫጭር እና ረጅም ኳሶችን በትክክለኛነት በመመገብ የቡድኑን የማጥቃት መስመር ከጀርባ ሆኖ በብልሃት ይመራል።

የተከላካይ ምሽግ የማጥቃት ድልድይም ነው በመከላከል ላይ ያለው ጥንካሬ እንደተጠበቀ ሆኖ በቅጣት እና ማዕዘን ምቶች ጊዜ ወደ ተጋጣሚ ሳጥን በመግባት በግንባር ግቦችን የማስቆጠር የላቀ ችሎታም አለው።

ቡድኑ በጫና ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ የመረጋጋት ድምፅ በመሆን ባልደረቦቹን የሚያነሳሳ እና ጨዋታውን ወደ ተፈለገው አቅጣጫ የሚመልስ ድንቅ አዛዥ ነው።

ረጅም ርቀት ሳይሮጥ እና ኃይሉን ሳይጨርስ አእምሮውን እና የማንበብ ብቃቱን ተጠቅሞ ተጋጣሚን ከአደጋ ክልል ውጭ የሚያደርግ የስልት አዋቂ ነው።

ጅላሉ የተከላካይነትን ብረት መሰል ጥንካሬ ከአማካይነት ረቂቅ የጥበብ ቅላጼ ጋር አዋህዶ የያዘ ድንቅ ተጨዋቾች ነው።

ሚሻላ ካፕ 2018  ቀይ ዛላ 4-0 ጤናን ባሸነፍንበት በዛሬው የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊአቶ ሰይፈ...
29/08/2026

ሚሻላ ካፕ 2018 ቀይ ዛላ 4-0 ጤናን ባሸነፍንበት በዛሬው የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ
አቶ ሰይፈ አለሙ ከልጆቻቸው ጋር በመሆን ጨዋታው በሀላባ ስታዲየም ተገኝተው ታድሟል ❤🌶🥰👍ከጨዋታው በኋላ የተገኘ ምስል!

❤🌶ዛላዊያን ለቀይ ዛላ ያላቸው ፍቅር ጥልቅ ነው🌶❤
29/08/2026

❤🌶ዛላዊያን ለቀይ ዛላ ያላቸው ፍቅር ጥልቅ ነው🌶❤

ቀይ ዛላ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፉን አረጋግጧል!የ2018 ሚሻላ ካፕ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ቀይ ዛላ 4-0 ጤናን አሸንፏል ቀይ ዛላ ሜዳውን የራሳቸው የትያትር መድረክ በማድረግ ጤናን 4-0 ...
29/08/2026

ቀይ ዛላ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፉን አረጋግጧል!

የ2018 ሚሻላ ካፕ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ቀይ ዛላ 4-0 ጤናን አሸንፏል ቀይ ዛላ ሜዳውን የራሳቸው የትያትር መድረክ በማድረግ ጤናን 4-0 በማሸነፍ ድንቅ ትርኢት አሳይቷል።

የጨዋታው ኮከብ ከቀይ ዛላ ምስጋና ተመርጧል የተመረጠው አስደናቂ ኮከብ እያንዳንዱ የፈጠረው አስደናቂ እንቅስቃሴ ተመልካቹን ከአፍታ እስከ አፍታ አስጨብጭቧል የሚገባውን የዕለቱ የጨዋታው ኮከብ Man of the Match በኩራት ተቀናጅቷል!

በዚህ ታላቅ ድል ቀይ ዛላ የምድቡን ዙፋን በአንደኝነት ተቆጣጥሮ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ተቀላቅሏል። የሚሻላ ካፕ አሁን የቀይ ዛላን አስፈሪ ግስጋሴ እየተመለከትን ነው።

2018 የሚሻላ ካፕ      ተጠናቋል ቀይ ዛላ 4 - 0 ጤና
29/08/2026

2018 የሚሻላ ካፕ
ተጠናቋል
ቀይ ዛላ 4 - 0 ጤና

2018 የሚሻላ ካፕ       እረፍት ቀይ ዛላ 2-0 ጤና
29/08/2026

2018 የሚሻላ ካፕ
እረፍት
ቀይ ዛላ 2-0 ጤና

2018 የሚሻላ ካፕ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ነገ ቅዳሜ ጠዋት 4:00 ሰዓት ሁላችንም ስታዲየም እንገናኝ !
28/08/2026

2018 የሚሻላ ካፕ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ነገ ቅዳሜ ጠዋት 4:00 ሰዓት ሁላችንም ስታዲየም እንገናኝ !

2018 የሀላባ ቁሊቶ የክረምት ወራት ሻምፒዮና U14 የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ          ተጠናቋል ቀይ ዛላ 1 - 2 ኤም ፋሚሊu14 ኤም ፋሚሊ ከምድቡ 1ኛ ሆኖ ቀይ ዛላ ከምድቡ 2ኛ ሆኖ...
28/08/2026

2018 የሀላባ ቁሊቶ የክረምት ወራት ሻምፒዮና U14 የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ
ተጠናቋል
ቀይ ዛላ 1 - 2 ኤም ፋሚሊ
u14 ኤም ፋሚሊ ከምድቡ 1ኛ ሆኖ ቀይ ዛላ ከምድቡ 2ኛ ሆኖ ማለፉን አረጋግጧል

የሚሻላ ካፕ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ነገ ቅዳሜ 4:00 ሰዓት ሀላባ 🏟️ስታዲየም አይቀርም !
28/08/2026

የሚሻላ ካፕ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ነገ ቅዳሜ 4:00 ሰዓት ሀላባ 🏟️ስታዲየም
አይቀርም !

የ2018 ሚሻላ ካፕ የምድብ የመጨረሻውና ወሳኙ ሰዓት ደርሷል! ቀይ ዛላ ምድቡን እየመራን ቀጣዩን ምዕራፍ ለማለፍ ወሳኝ ጨዋታ ላይ ደርሰናል ጨዋታው የብርታት የታታሪነትና የደጋፊነት ፍቅር መ...
27/08/2026

የ2018 ሚሻላ ካፕ የምድብ የመጨረሻውና ወሳኙ ሰዓት ደርሷል! ቀይ ዛላ ምድቡን እየመራን ቀጣዩን ምዕራፍ ለማለፍ ወሳኝ ጨዋታ ላይ ደርሰናል ጨዋታው የብርታት የታታሪነትና የደጋፊነት ፍቅር መግለጫ የሜዳው ውበት የደጋፊው ድምፅና የተጫዋቾቻችን ጀግንነት ቅዳሜ በ4 ሰዓት በአንድነት ይገናኛሉ።
ቅዳሜ | 4፡00| ሰዓት ጠዋት
ቀይ ዛላ 🆚 ጤና
ሀላባ ቁሊቶ 🏟️ስታዲየም
ማሊያውን ለብሰን ደምቀን በሙሉ ድምፅና ስሜት ቅዳሜ 4 ሰዓት ቀጠሮ ተይዟል ቅዳሜ ጠዋት 4 ሰዓት አይቀርም !❤🇮🇩🌶

Address

Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Red Zala Sport posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category