በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት በከተማ አስተዳደሩ የሚከናወኑ የስፖርት ትምህርት ስልጠና መርሃ ግብርች የሚገለፁበት

20/04/2024
በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውና ቤተሰቡ አካዳሚ የልምድ ልውውጥ ተደረገ።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና  ስፖርት ቢሮ በከተማ የሚገኙ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ልማት መርሃ ግብር የስፖርት ...
31/03/2024

በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውና ቤተሰቡ አካዳሚ የልምድ ልውውጥ ተደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በከተማ የሚገኙ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ልማት መርሃ ግብር የስፖርት ትምህርት ስልጠና መአከላት ስራ አስኪያጆች ቡድን መሪዎች እና በመንግስት ድጋፍ የሚያሰለጥኑ የእግር ኳስ አሰልጣኞች እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በተገኙበት በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው አካዳሚ የልድ ልውውጥ ተደረገ።

በእግርኳስ ስፖርት ጥሩ ስም ያላቸው የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ታዳጊ ስፖርተኞችን ታሳቢ ያደረገ አካዳሚ በማቋቋም እየሰሩ ነው።
በከተማችን በ20 የስፖርት አይነት በ413 የስልጠና ጣቢያዎች 13723 በወንድ 4045 በሴቶች በመንግስት ድጋፍ; በስፖርት ትምህርት ስልጠና መአካላት በስፖርት ማህበራት ድጋፍ በግለሰብ ማበልፀጊያ መአከላት በ388 ወንድ በ25 ሴት አሰልጣኞች ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙ ሲሆን።
ልምድ ልውውጡም በስልጠና ጣቢያዎች ያሉ ተሞክሮዎችን ለማስፋፋት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አመላክቷል።
መጨረሻም ለአካዳሚው የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ የደረገ ሲሆን አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውም ለተሰጣቸው ትኩረትና ማበረታቻ ምስጋና አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ወጣቶች ስፖርት ቢሮ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የወራ አባባ ንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ አደረገማንኛዋም ሴት በንጽህና መጠበቂያ ችግር ምክንያት ከስፓርት ል...
31/03/2024

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ወጣቶች ስፖርት ቢሮ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የወራ አባባ ንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ አደረገ

ማንኛዋም ሴት በንጽህና መጠበቂያ ችግር ምክንያት ከስፓርት ልምምድ ቦታ መቅረት የለባትም የሚሉት የስፓርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ በልዩና መደበኛ ስልጠና ጣቢያ ለሚሰለጥኑ ከ 4045 በላይ ሴቶች የንጽህና መጠበቂያ መስጠቱን ገልጸዋል

የስፓርት ህክምና ቡድን መሪ ወይዘሮ ሐያት ኪያር በበኩላቸው የሞዴስ ድጋፉ በስፓርት ስልጠና የሚሳተፉ ሴቶች በንጽሕና መጠበቂያ እጥረት ሳቢያ ከስፓርት እንዳይቀሩ እንደሚያስችል ገልጸው ድጋፉ በስልጠና ጣቢያ ያሉ ሴቶችን ለመርዳት ዓላማ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል

በድጋፉ በአምስቱ የስፖርት ትምህርት ስልጠና መአከላት እና በ11 ክፍለ ከተማ ላሉ በታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ልማት መርሃ ግብር ታቅፈው በመሰልጠን ላይ ላሉ ልጃገረዶች ሲሆን። ሰልጣኞች በልምሜድ ወቅት የሚያጋጥማቸውን የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ችግር በመቅረፍ ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑ ተመልክቷል

ቢሮው የታዳጊ ወጣቶች ልዩ ስልጠና ልማት መርሃ ግብር  ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዋችን አስቀመጠበመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ...
31/03/2024

ቢሮው የታዳጊ ወጣቶች ልዩ ስልጠና ልማት መርሃ ግብር ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዋችን አስቀመጠ

በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮሚሽነር ተስፋዬ ኦሜጋ ተተኪ ስፓርተኞችን በጥራትና በብዛት ለማፍራት ስልጠናዎች ሳይንስን ጥበብና እውቅት ተከትለው መሰጠት አለባቸው ብለዋል

ኮሚሽነር ተስፋዬ አያይዘውም በስፓርቱ የሚፈለገው ውጤት እንዲመጣ ፌድሬሽኖች ሚናቸውን ከፍ በማድረግ በትምህርታቸው የተመሰገኑ አገርን የሚወክሉ ምርጥ አትሌቶች ለማፍራት በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል

የቢሮ አማካሪ አቶ ታሪኩ እሸቴ በበኩላቸው በማዕከሉ የሚሰጡ ልዩ ስልጠና ከቢሮው ጋር በቅንጅት መስራቱ የሚፈለገው ውጤት መምጣቱን ገልጸው ታዳጊዎቹ የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማቸው በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራ ማሳተፍ አስፈላጊ ነው ብለዋል

ልዩ ስልጠና መርሃ ግብሩ ከፌድሬሽኖች እና ከወላጆች ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ወንደሰን የምገባ ሥርዓት ማሥጀመር፣የምዘና ውድድር ማዘጋጀት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆናቸውን ገልጸዋል

በግምገማው የተገኙ ባለድርሻ አካላት ውይይቱ ፍሬያማ እንደነበረ ገልጸው ለልዩ ስልጠና አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች እንዲሟላላቸው ጠይቀዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እየተሳተፋ ለሚገኙ  የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊ ማህበር አመራሮች በስፖርት ዲጂታል ማርኬቲንግ እና በማህበራዊ ሚዲ...
14/12/2023

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እየተሳተፋ ለሚገኙ የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊ ማህበር አመራሮች በስፖርት ዲጂታል ማርኬቲንግ እና በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።

በማጠቀላያ መርሃግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ስፖርቱን በተለይ እግር ኳስ ክለቦችን ህዝባዊ መሰረት እንዲኖራቸው እና ከመንግስት ድጎማ እንዲላቀቁ ሁሉም አካል በየደረጃው ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎችም ለክለባቸው ሁለንተናዊ እድገት የማይተካ ሚና እንዳላቸው የተናገሩት አቶ በላይ በቀጣይ የክለባቸው የገቢ ምንጭ በማሳደግ በአፍሪካ እና በአለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ተወዳዳሪ እና ተፎካካሪ የሆኑ የእግር ኳስ ክለቦችን ለመፍጠር አስበው እንዲሰሩ አሳስበዋል።

እግር ኳስ ከውድድር ባለፈ በደጋፊዎች ዘንድ የእርስ በእርስ ግንኙነትን የሚያጠናክር፣ ወድማማችነት የሚያጎለብት፣ ማህበራዊ ትስስርን በመፍጠር ሰዎች የሚረዳዱበት እና የሚጠያየቁበት፣ ከዘር እና ከሀይማኖት የራቀ ሰላማዊ የውድድር መስክ በመሆኑ ይህን አጠናክሮ በማስቀጠል ለቀጣዩ ትውልድ ማስረከብ የደጋፊዎች ሀላፊነት እንደሆነ የቢሮው ሀላፊው ተናግረዋል።

ለሁለት ቀን የተሰጠው ስልጠና የደጋፊዎችን አቅም ከመገንባቱ ባሻገር ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገት በጋራ ለመስራት እንደሚያስችል አቶ በላይ ገልጸው ሰልጣኞች በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ሀሰተኛ ዜናዎችን በመለየት ጠቃሚ መረጃን ለስፓርቱ እድገት በማዋል የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል

ስልጠናውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ደጋፊዎች ጥምር ማህበር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑን ተመላክቷል።

በክ/ከተማው ለሚገኙ በ10 ፕሮጀክቶች ለታቀፉ ታዳጊ ስፖርተኞች የስፖርት ትጥቅና የግብዓት ድጋፍ ተበረከተ፡፡ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር በክ/ከተማው ለሚገኙ በ10 ፕሮጀክቶች ለታቀፍ ...
06/12/2023

በክ/ከተማው ለሚገኙ በ10 ፕሮጀክቶች ለታቀፉ ታዳጊ ስፖርተኞች የስፖርት ትጥቅና የግብዓት ድጋፍ ተበረከተ፡፡

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር በክ/ከተማው ለሚገኙ በ10 ፕሮጀክቶች ለታቀፍ 250 ታዳጊ ስፖርተኞች የስፖርት ትጥቅና የግብዓት ድጋፍ አበረከተ፡፡

በክ/ከተማው የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አህመድ መሀመድ እና የክ/ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀይለማሪያም አበራ በድጋፉ የርክክብ መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በስፖርት ዘርፉ ታዳጊ ስፖርቶኞችን ማፍራት ቀዳሚ ተግባር እንደሆነ ተናግረው፤ የክ/ከተማው አስተዳደር በሀሳብ፤ በሞራልና በግብዓት የሚያደርገው ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

በጽ/ቤቱ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ቡድን መሪ አቶ ፈለቀ ብርሃኑ በክ/ከተማ ደረጃ 410 ወጣቶች በ17 የተለያዩ የታዳጊ ፕሮጀክቶች እንደታቀፉ ጠቁመው፤ በዛሬው ዕለትም በ10 ፕሮጀክቶች ለ250 ታዳጊ ወጣቶች በክ/ከተማው አስተደዳር የስልጠና ቁሳቁስ ድጋፍ እንደተደረገ ተናግረው፡፡

በመጨረሻም የስራ ሀላፊዎቹ ድጋፍ የተደረገላቸው የታዳጊ ስፖርተኞች ክ/ከተማውን፣ ከተማ አስተዳደሩን ብሎም ሀገርን የሚያስጠራ ብቁ ተወዳዳሪ ለመሆን ጠንክረው እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ከስፓርት ለሁሉም ኮሚቴ እና ከቅዱስ ጳዉሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ  ጋር በመተባበር ለአካል ብቃት አሰልጠኞችና  ለስፖርት ባለሙያዎች ሲ...
02/12/2023

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ከስፓርት ለሁሉም ኮሚቴ እና ከቅዱስ ጳዉሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ጋር በመተባበር ለአካል ብቃት አሰልጠኞችና ለስፖርት ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው የፌዝዮትራፒ ስልጠና ተጠናቀቀ

የትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ እንደገለጹልን ስልጠናውን ወስደው ያጠናቀቁ ሰልጣኞች በውድድር እና በስልጠና ጊዜ የሚደርስን ጉዳት ለመቀንስና አፋጣኝ ህክምና እርዳታ ለመስጥ እንደሚያስችላቸው ነው

ስልጠናውን ከቅዱስ ጳውሎስ የመጡ በሙያው ከፍተኛ ልምድ ያላቸው አሰልጣኞች የሰጡ ሲሆን በተግባር እና በንድፈ ሐሳብ በተደገፈው ስልጠና ላይ 33 የስፓርት ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል

የተዘጋጀው ስልጠና ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር ተዛማች መሆኑን የገለጹት ስልጠኞች በፊዚዮቴራፒ ህክምና አሰጣጥ በቂ ግንዛቤ እንዳገኙ ገልጸዋል

እንደ ስፓርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት መረጃ ከሆነ በስልጠናው የተሳተፉ የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና ስልጠና የወሰዱ የአሰልጣኝነት ስልጠና ስርተፊኬት ያላቸው በሙያው እያገለገሉ መሆናቸውን ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ለፌድሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊዎች, ለፌዴሬሽን ቴክኒክ ባለሙያና ለስፓርት ዘርፍ አመራሮች በአመራር ክህሎት Sales attitude and m...
26/11/2023

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ለፌድሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊዎች, ለፌዴሬሽን ቴክኒክ ባለሙያና ለስፓርት ዘርፍ አመራሮች በአመራር ክህሎት Sales attitude and mindset, Sales skill and techniques, Motuvation and Goal achievemnt, Sales strategy and leadership and skill development በሚሉ ርእሶች የአቅም ግንባታና በስልጠና።

ለሦስት ቀናት በዘለቀው ስልጠና የአመራሮቹን አቅም ከማሳደግ በተጨማሪ ስፖርቱን ወደ ሀብት የመቀየር አቅም ይፈጥርላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ የስፖርት ትምህርት ስልጠና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ዮናስ ካሳሁን ገልፀዋል።

በእንቅስቃሴ ጊዜ የሚደርሱ ጉዳቶች  የከፋ አደጋ እንዳሳያስከትሉ የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና ወሳኝ መሆኑ ተገለጸየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከቅዱስ ጳውሎስ ሚሊንየም ሕ...
20/11/2023

በእንቅስቃሴ ጊዜ የሚደርሱ ጉዳቶች የከፋ አደጋ እንዳሳያስከትሉ የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከቅዱስ ጳውሎስ ሚሊንየም ሕክምና ኮሌጅ ጋር በመተባበር የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ ስልጠና ከስፖርት ማህበራት እና ከክፍለ ከተማ ተመርጠው ለተላኩ ባለሙያዎች መስጠት ጀመረ ፡፡

ስልጠናው ለአምስት ተከታይ ቀናት እንደሚሰጥ የገለጹልን ጤና መኮንን ሃያት ኪያር በንድፈ ሐሳብ እና በተግባር ተደግፎ በውድድርና በልምድ ጊዜ አደጋ ሲያጋጥም ወደሃኪም ቤት ሄደዉ ተገቢዉ የህክምና አገልግሎት እስኪደረግላቸዉ ድረስ በቦታዉ ሊያገኙት የሚችለዉን ሕክምና መስጠት እንዲችሉ ታስቦ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በአደኛ ደረጃ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያሰለጠናቸውን 73 ሰልጣኞች ዛሬ በልዩ ስፖርታዊ ፌስቲቫል አስመርቆል።በአራት ኪሎ ስፖርት ትም...
19/11/2023

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በአደኛ ደረጃ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያሰለጠናቸውን 73 ሰልጣኞች ዛሬ በልዩ ስፖርታዊ ፌስቲቫል አስመርቆል።

በአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርት እና ስልጠና ማዕከል በተካሄደው የምረቃ ፕሮግራም የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶች እና ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ አባላት የተገኙ ሲሆን ከተመራቂ ሰልጣኞች ጋር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሰርተዋል።

በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች እና ማህበራዊ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ለመፍጠር የአካል ብቃት አሰልጣኞችን በብዛት እና በጥራት ማፍራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ዛሬ የተመረቁ ሰልጣኞችም ወደ ማህበረሰቡ በመውረድ እና በማሰልጠን ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ወ/ሮ ዘይነባ አሳስበዋል።

ተመራቂ ሰልጣኞችም የወሰዱት የአንደኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት ስልጠና የነበራቸውን የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር እውቀት እንዳሳደላቸው እና በቀጣይም በእውቀት ላይ የተመሰረተ ስልጠና ለመስጠት እንደሚረዳቸው ተናግረዋል።

ለ15 ቀናት በሙያው ሰፊ ልምድና የዳበረ እውቀት ባላቸው ኢንስትራክተሮች በተሰጠው የንድፈ ሀሳብ እና የተግበራ ስልጠና 25 ሴቶች እና 48 ወንዶች ስልጠናቸውን በሚገባ ተከታትለው ዛሬ የተመረቁ ሲሆን በዘርፉ የሚታየውን የአሰልጣኝነት እጥረት በተወሰነ ደረጃ እንደሚቀርፈው የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ለሁሉም ኮሚቴ የፅ/ቤት ሀላፊ ከአቶ ፈለቀ ዋቄ ተናግረዋል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category