15/10/2023
የእንግሊዝ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ትላንት እና ዛሬ ቀጥለው ተከናውነዋል።
▪️የአርሰናል ሴቶች ቡድን የአስቶን ቪላ አቻቸውን በኤምሬትስ ስቴዲየም ባስተናገዱበት ጨዋታ ላይ እስከ መደበኛው 90 ደቂቃ ድረስ 1-0 ሲመሩ ቢቆዩም 88ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይራ የገባችው ቤዝ ሚድ ልዩነት ፈጣሪዋ ተጫዋች ሆናለች። በተጨመሩት ደቂቃዎች አርሰናል 2 ግቦችን አከታትለው በማስቆጠር ጨኻዋታውን አሸንፈው ወጥተዋል። ታዲያ 94ኛው ደቂቃ ላይ አሌሲራ ሩሶ ለአርሰናል የማሸነፊያዋን ግብ እንድታስቆጥር ኳሱን አመቻችታ ያቀበለችው ቤዝ ሚድ ናት።
▪️እንደሚታወቀው ይህች እንግሊዛዊት የፊት መስመር ተጫዋች ረዘም ላለ ጊዜ በጉልበት ጅማት መበጠስ (Acl) አስተናግዳ ለ11 ወራት ከሜዳ ርቃ እንደነበር የሚታወስ ነው።