02/09/2026
"የተከበሩ የአርጀንቲና አምባሳደር"!
🇦🇷️👑 በአርጀንቲና እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ የሊዮኔል ሜሲ ያህል የሀገሪቱን ስም በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ አድርጎ ያነሳ ተጫዋች ማግኘት ይከብዳል። ሜሲ ሜዳ ውስጥ በሚያሳየው አስደናቂ ጥበብ እና ከሜዳ ውጭ በሚታወቅበት ትህትና የአርጀንቲናን እሴት፣ ማንነት እና በጎ ምስል ለመላው ዓለም በተግባር ያስመሰከረ የዘመናችን ትልቅ ስፖርተኛ ነው።
ይህን ታላቅ አስተዋጽኦ ለመዘከርም የአርጀንቲና ኮንግረስ ለኮከቡ ልዩ እውቅና ለመስጠት ተዘጋጅቷል። በዚህም መሰረት ሊዮኔል ሜሲ "የተከበሩ የአርጀንቲና አምባሳደር" የሚል የክብር ማዕረግ የሚሰጠው ይሆናል።
የሜሲ ስም በሀገሩ አርጀንቲና ሲነሳ ሁልጊዜም ድንቅ ታሪኮችን ያስታውሰናል። ከዓመታት በፊት በሜሲ የትውልድ ከተማ ሮሳሪዮ፣ ወላጆች ለልጆቻቸው "ሜሲ" የሚል የመጀመሪያ ስም እንዳያወጡ በሕግ መከልከሉ ይታወሳል። የአካባቢው ባለስልጣናት ይህንን ውሳኔ አስተላልፈው የነበረው፣ አብዛኛው ወላጅ ልጁን "ሜሲ" ብሎ መጥራት በመጀመሩ ምክንያት በትምህርት ቤቶችና በመንግስት መዝገቦች ላይ የሚፈጠረውን ከፍተኛ የስም መደናገር ለመከላከል ነበር።
በአንድ ወቅት በገዛ ትውልድ ከተማው ስሙ ለህፃናት እንዳይሰጥ እስከ መከልከል ደርሶ የነበረው የሜሲ ስም፣ ዛሬ ግን የሀገሪቱ የክብርና የማንነት ምልክት ሆኖ በመላው አርጀንቲና ኮንግረስ የከበረ "የሀገር አምባሳደር" የሚል ማዕረግን ለመቀናጀት በቅቷል።👑⚽