Ethiopia karate-do エチオピア空手道

Ethiopia karate-do エチオピア空手道 All style Karate do federation �

የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን ከኦሮሚያ ካራቴ የፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የ2018ዓ/ም የሙያማሻሻያ እና ፈተና በጥሩ ሁኔታ ተጠናቋልየካቲት /2028 ዓ/ም አዳማ
17/02/2026

የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን ከኦሮሚያ ካራቴ የፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የ2018ዓ/ም የሙያማሻሻያ እና ፈተና በጥሩ ሁኔታ ተጠናቋል
የካቲት /2028 ዓ/ም አዳማ

15/02/2026

የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን የዳን ፈተና እና ስልጠና በአዲስ አበባ ከየካቲት 14-15/2018ዓ/ም ይካሄዳል

የ2018ዓ/ም የካራቴ ስፖርት አጠቃላይ የታዳጊ ወጣቶች ምዘና ውድድር ውጤት
13/02/2026

የ2018ዓ/ም የካራቴ ስፖርት አጠቃላይ የታዳጊ ወጣቶች ምዘና ውድድር ውጤት

የኢትዮጲያ ካራቴ ፌዴሬሽን የዳንፈተና ና የሙያማሻሻያ ነገ ጥር 26/2018ምዝገባ ይካሄዳል ሮብ ጥር 27/2018 ስለጠናው ይጀመራል የስልጠና ቦታ ደሴ ወጣቶች ማእከል
02/02/2026

የኢትዮጲያ ካራቴ ፌዴሬሽን የዳንፈተና ና የሙያማሻሻያ ነገ ጥር 26/2018
ምዝገባ ይካሄዳል
ሮብ ጥር 27/2018 ስለጠናው ይጀመራል
የስልጠና ቦታ
ደሴ ወጣቶች ማእከል

21/12/2025
አንጎላ ለሚካሄደው 4ኛው የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር የኢትዮጵያ ካራቴ ቡድን መልካም እድል 🥰
08/12/2025

አንጎላ ለሚካሄደው 4ኛው የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር የኢትዮጵያ ካራቴ ቡድን መልካም እድል 🥰

የምስራቅ አፍሪካ ካራቴ ሻምፒዮና በመጭው ወር ይካሄዳል ( የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን)ጥቅምት 28፣ 2018 ዓ.ም አዲስ አበባየኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን ኢትዮጵያ በምታስተናግደው የምስራቅ አፍ...
08/11/2025

የምስራቅ አፍሪካ ካራቴ ሻምፒዮና በመጭው ወር ይካሄዳል ( የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን)

ጥቅምት 28፣ 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን ኢትዮጵያ በምታስተናግደው የምስራቅ አፍሪካ ካራቴ ሻምፒዮናን አስመልክቶ ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥቷል።

የምስራቅ አፍሪካ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከዲሴምቨር 16-22/2018ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉነህ ጎሳዬ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ በምታስተናግደው የምስራቅና የመካከለኛው አፍሪካ ውድድር 14 ሀገራት እንደሚሳተፉም ፕሬዚዳንቱ አክለዋል።

የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን ከአፍሪካ ካራቴ
ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የዳኝነት፣ የአሰልጣኝነት፣ የአትሌትና የባለሙያዎች ስልጠናዎችን ከውድድሩ ዝግጅት ጉን ለጉን በተሳካ ሁኔታ መስጠቱን ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።

ስልጠናው በሀገራችን የሚታየው የዳኝነት ችግር የሚቀርፍ እና አለም አቀፍ ስታንዳርድን መሰረት ያደረገ እንደሆነም በመግለጫው ተካቷል።

በስልጠናው ከ82 በላይ ባለሙያዎች ስልጠናውን የተከታተሉ ሲሆን ይህም ለካራቴ ስፖርት እድገት አንድ እምርታ ማሳያ ነው ተብሏል።

በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ አማረ በበኩላቸው የበስፖርት ልማት ዘርፍ ከያዛቸው እቅዶች መካከል የተለያዩ አህጉራዊ፣ ክፍለ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ውድድሮችን በሀገራችን የማስተናገድ እቅድ እንደሆን ገልፀዋል።

በዚሁ መሰረት በካራቴ ስፖርት የሚጀመረው የምስራቅ አፍሪካ ሻምፒዮና አንዱ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

በሀገራችን በሚካሄደው የካራቴ ሻምፒዮና መንግስት አስፈላጊ የሆኑ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በበቂ ሁኔታ እንዳመቻቸም በመግለጫቸው አክለዋል።

ከሻምፒዮናው ጉን ለጎን በከተማዋ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ፣ ማደሪያ ሆቴሎች በማመቻቸት አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውንም ወ/ሮ አበባ አስታውቀዋል።

በሀገራችን በሚካሄደው የምስራቅ አፍሪካ ሻምፒዮና ሀገራችንን የሚወክሉና የተሻለ ውጤት የሚያመጡ አትሌቶችም መዘጋጀታቸውን በመግለጫው ተጠቁሟል።

በመግለጫው የታደሙት በአፍሪካ የዳኛ ኮሚሽን
ሮዳ ሻምፒዮናው ተወዳዳሪ አትሌቶች ለአለም አቀፍ ውድድር ልምድ የሚቀስሙበት መሆኑን አስረድተዋል።

የምስራቅ አፍሪካ ካራቴ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ እንድካሄድ መንግስት እና ባለድርሻ አካላት ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና ይገባቸዋልም ብለዋል።

በሻምፒዮናው ከ17 ዓመት እና ከ14 ዓመት በታች እንዲሁም በሲኔር ውድድር ሀገራችንን የሚወክሉ አትሌቶች ይሳተፋሉ።

የመረጃ የኢትዮጵያ ባህልእና ስፖርት ሚኒስተር

M.RHODA LA'EEQእንኳን ወደ ኢትዮጵያ በሰላም ገባህ የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ሙሉነህ ጎሳየ ከፌዴሬሽኑ የዳኞች ሰብሳቢ ሲነር ማስተር በላይ ዘሚካኤል እና ከፌዴሬሽኑ ቴ...
02/11/2025

M.RHODA LA'EEQ
እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በሰላም ገባህ
የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ሙሉነህ ጎሳየ ከፌዴሬሽኑ የዳኞች ሰብሳቢ ሲነር ማስተር በላይ ዘሚካኤል እና ከፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ኮሚቴ ማስተር ነጋሽ ግርማ እና ማስተር ተስፉ ጎሹ እንዲሁም የብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ዋና አሰልጣኝ ማስተር ማስረሻ ዮሃንስ ጋር በኢትዮጵያ አለማቀፍ አውረፕላን ማረፍያ ከምሽቱ 5:00 ላይ አቀባበል አድርገዋል
የመጣው አለማቀፍ የካራቴ ዳኛ የኢትዮጵያ ካራቴ የዳኝነቱን ከፍታ የሚለውጥ ስልጠናዎችን ከነገ ጀምሮ በወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ የሚሰጥ ይሆናል

ማስታወሻተቀያሪ ፕሮግራምለሁሉም ክፍት የሆነ ውድድርየኢትዮጵያ ካራቴ ፈዴሬሽን በማዳጋስካር ለሚኖረው የምስራቅ አ ፍሪካ ሻምፒዮና ውድድር ከጥቅምት 2-4/18 በአዲስ አበባ ኢ ትዮጵያ ስፖርት ...
06/10/2025

ማስታወሻ

ተቀያሪ ፕሮግራም

ለሁሉም ክፍት የሆነ ውድድር

የኢትዮጵያ ካራቴ ፈዴሬሽን በማዳጋስካር ለሚኖረው የምስራቅ አ ፍሪካ ሻምፒዮና ውድድር ከጥቅምት 2-4/18 በአዲስ አበባ ኢ ትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ለማድረግ መታቀዱ የሚታወስ ነው።

ቢሆንም ከጥቅምት 8-15/18 የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድርበአዲስ አበባ ሰለሚካሄድ የኦፕን ውድድሩን አብሮ በማስተሳሰርበደማቅ መልኩ ማስኬድ ስለታሰበ ፡እንዲሁም የተወዳዳሪዎች መመላለስን ለማስቀረት እና በቂ የዝግጅት ጊዜ እንዲኖር ለማ ስቻል የውድድሩ ቀን የወጣቶች ኦሎምፒክ በሚካሄድበት ቀን ላ ይ ከጥቅምት 12-14/18 የተቀየረ እና ምዝገባ ያላካሄዳችሁ መጨረሻ ቀን እስከ ጥቅምት 2/18 ድረስ እንድታከናውኑ እናሳ ስባለን።
የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን

Address

Bole/Addis Ababa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia karate-do エチオピア空手道 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopia karate-do エチオピア空手道:

Share

Category