11/08/2023
👉 የኢትዮጵያ ቡና ዋናው ቡድን የ2016 ዓ.ም የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ዛሬ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም የመጀመሪያ ልምምዱን አድርጓል።
👉 በአሰልጣኝ ካቫዞቪች ኒኮላ የሚመራው ዘጠኝ የአሰልጣኝ ቡድን እና ሃያ ዘጠኝ ተጫዋቾችን በመያዝ ትላንት ተጠቃሎ ወደ ሆቴል የገባው የኢትዮጵያ ቡና ቡድን በቀን ሁለት ጊዜ ልምምዱን ያደርጋል።
👉 በብሔራዊ ቡድን ጥሪ የተደረገለት አንበሉ #አማኑኤል ዮሐንስ ዕረፍት የተሰጠው ሲሆን፤ ሰኞ ቡድኑን ይቀላቀላል።
👉 በነገው ዕለት የክለባችን እና የደጋፊ ማህበሩ አመራሮች ቡድኑን ልምምዱን ለመመልከት እና ለማበረታታት አዳማ ይገኛሉ።