13/08/2026
ተጨዋቾች ከረጅም አድካሚ የውድድር ዘመን በሁዋላ ምን አይነት ባህል ሊኖራቸው ይገባል !
⚽ የተጫዋችነት ዘመን ከፍ ለማድረግ ዘንድ — እረፍት፣ አመጋገብ እና የሕይወት ስነ-ምግባር ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።
አንድ ፕሮፌሽናል ተጫዋች ከአንድ ከባድ የውድድር ዘመን በኋላ የሚያደርገው እረፍት ለቀጣዩ ሲዝን ዝግጅት አካል ነው። እረፍት ማለት ሙሉ በሙሉ ከእንቅስቃሴ መራቅ ሳይሆን ሰውነትንና አእምሮን መልሶ ማደስ ነው።
በ2025 የFIFPRO የሕክምናና የHigh-Performance ባለሙያዎች የጋራ ምክረ-ሀሳብ ቢያንስ 4 ሳምንት Off-season break እንዲኖር፣ ከዚህም ውስጥ 2 ሳምንት ከክለብና ከብሔራዊ ቡድን ሙሉ በሙሉ ነፃ እንዲሆን እና ከዚያ በኋላ ቢያንስ 4 ሳምንት የgradual re-training እንዲኖር ይጠቁማል።
🧠 እረፍት ማለት “ምንም አልሰራም” ማለት አይደለም
ተጫዋቹ በመጀመሪያ ሰውነቱን እና አእምሮውን ማሳረፍ ይገባዋል። ከዚያ ቀስ በቀስ ወደ Active Recovery እና በመጨረሻ ወደ Pre-season ዝግጅት መሸጋገር ይኖርበታል።
REST → RECOVER → REACTIVATE → RE-TRAIN → PERFORM
ይህ ሂደት በተለይ ከከባድ ሲዝን በኋላ አስፈላጊ ነው።
🥗 አመጋገብ — እረፍት ላይ እንኳን የተጫዋቹ ስራ ነው
“ልምምድ የለም፣ ስለዚህ ምግብም ምንም አይደለም” የሚለው አስተሳሰብ ተጫዋቹን ሊጎዳ ይችላል።
በእረፍት ወቅት፦
* የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
* በቂ ፕሮቲን ማግኘት
* አትክልትና ፍራፍሬ ማብዛት
* በቂ ውሃ መጠጣት
* ከመጠን በላይ ስኳር፣ ፈጣን ምግብ እና ከፍተኛ ካሎሪ መመገብን መቆጣጠር
ክብደትና የሰውነት ስብ እንዳይጨምር መጠን መጠበቅ
ያስፈልጋል።
እረፍት ማለት የተጫዋችነት ሕይወትን ማቆም ሳይሆን ሰውነትን ለቀጣዩ ሲዝን መጠበቅ ነው።
🍺 አልኮል —
“እረፍት ነው” ብሎ መጠን ማጣት አይገባም
ተጫዋች በእረፍት ጊዜ ማህበራዊ ሕይወቱን መደሰት ይችላል፤ ግን ከፍተኛ የአልኮል መጠጥን መደበኛ ልማድ ማድረግ ከተጫዋችነት ሕይወት ጋር አይጣጣምም።
በተለይ ከመጠን በላይ መጠጣት የእንቅልፍ፣ የhydration እና የrecovery ሂደትን ሊያበላሽ ይችላል። ስለዚህ ተጫዋቹ የራሱን ጤና፣ አካል እና የሙያ ዕድሜ ከጊዜያዊ ደስታ በላይ ማስቀመጥ አለበት።
🏆 ትልቁ ትምህርት
ተጫዋችነት በሜዳ ላይ ብቻ አይገነባም።
በልምምድ ይገነባል፤
በእረፍት ይጠበቃል፤
በአመጋገብ ይጠናከራል፤
በእንቅልፍ ይመለሳል፤
በስነ-ምግባር ይረዝማል።
* ስለዚህ ወጣት ተጫዋቾች፣ የእረፍት ጊዜያችሁን በጥበብ ተጠቀሙ። ቤተሰብዎን አግኙ፣ ይጓዙ፣ ይዝናኑ፣ በቂ እንቅልፍ ውሰዱ፤ ግን ሰውነታችሁን፣ አመጋገባችሁን እና የተጫዋችነት ስነ-ምግባራችሁን አትተዉ።
“ዛሬ ራሴን በጥበብ አሳርፋለሁ፤ ነገ በጠንካራ አካልና አእምሮ ወደ ሜዳ እመለሳለሁ።”
የተጫዋችነት ዕድሜህን ለማራዘም የምታደርገው እንክብካቤ የዛሬ ልምምድህን ያህል አስፈላጊ ነው። ⚽