31/05/2026
ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች በውጤት የደመቁበት የ2026 የምስራቅ አፍሪካ ካራቴ ሻምፒዮና ተጠናቀቀ።
ካሳለፍነው አርብ ጀምሮ በኬኒያ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የካራቴ ሻምፒዮና ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝ በውድድሩ ኢትዮጵያውያ ስፖርተኞች አኩሪ ድል አስመዝግበዋል።
በዚህም መሰረት በሻምፒዮናው በሴቶች ኢትዮጵያን በብቸኝነት የወከለችው እፁብ ድንቅ በላይ በነጠላ ካታ የወርቅ እና በነጠላ ፋይት የነሃስ ሜዳሊያ በማስመዝገብ ደማቅ ታሪክን ፅፋለች።
በወንዶች የነጠላ ፋይት ምርጥ ብቃቱን ያሳያው ፀጋዘአብ ጎሳ የወርቅ ሜዳሊያን ሲያሰገኝ, በሲኒየር የነጠላ ካታ እዮብ አለሙ የነሀስ ሜዳሊያን አስመዝግቧል።
የወርቅ ሜዳሊያ እና ዋንጫ ከተገኘበት የወጢቶች የቡድን ፋይት በተጨማሪ
ያብስራ አሰፋ, እዮብ አለሙ እና አህመድ ጡሃ በቡድን የሲኒየር ካታ ብርቱ ፉክክር አድርገው 2ኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል።
ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች በቡድን ካስመዘገቡት ግሩም ውጤት በተጨማሪ በግል ፋይት ለሚ ሎሊ የወርቅ, ናትናኤል ሀብታሙ የብር እና ኑር ሙሀመድ የነሀስ ሜዳሊያ ለአገራቸው ኢትዮጵያ አስገኝተዋል።
በግል የወንዶች ሲኒየር ፋይት እልህ አስጨራሽ ፉክክር ያደረገው አህመድ ጡሃ የነሃስ ሜዳሊያን አስመዝግቦ አጠናቋል::
በሻምፒዮናው የተሳተፈው የኢትዮጵያ ካራቴ ልዑክ ቡድን ነገ ወደ አገሩ ይመለሳል::
# # # ማሳሰቢያ:
በምንም መልኩ የምንጽፋቸው ጽሑፎች እና መጣጥፎች እንድሁም ልጥፎች የተለያዩ የራሳቸው ሀሳብ እና ህመም ያለባቸውን ግለሰቦች ለማሳዘን ወይም የግል ጥቅማቸውን ለማሳጣት ሳይሆን፣ የካራቴን ህብረተሰብ ለማነቃቃት እና ባልተለመደ መልኩ ካራቴን ለማስተዋወቅ መሆኑ እንዲታወቅልን ! በአክብሮት እናሳስባለን 🙏
# # # JKS ኢትዮጵያን ይከታተሉ!
የJKS ኢትዮጵያን የቅርብ ጊዜ እንቅስቃሴዎች፣ ዜናዎች፣ የስልጠና መርሃ ግብሮች እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የተዘረዘሩትን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይጎብኙ፦
* ቴሌግራም: [https://t.me/JKSEthiopia](https://t.me/JKSEthiopia)
* ድረ-ገጽ: [https://jkskarateethiopia.com/](https://jkskarateethiopia.com/)
* ዩቲዩብ: [https://www.youtube.com/](https://www.youtube.com/)
* ፌስቡክ: [https://www.facebook.com/JKSEthiopia/](https://www.facebook.com/JKSEthiopia/)
* ቲክቶክ: [https://www.tiktok.com/](https://www.tiktok.com/)
* 𝕏: [https://x.com/3b31a9069ae149c?t=9yhS_7r94I2CQAzOKPtWow&s=09](https://x.com/3b31a9069ae149c?t=9yhS_7r94I2CQAzOKPtWow&s=09)