04/10/2025
ሰማያዊዎቹ ወሳኝ ድል አሳክተዋል !
በሳምንቱ ተጠባቂ የፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ ከሊቨርፑል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
የቼልሲን የማሸነፊያ ግቦች ሞይሰስ ካይሴዶ እና እስቴቫኦ ሲያስቆጥሩ ለሊቨርፑል ኮዲ ጋክፖ ከመረብ አሳርፏል።
ሊቨርፑል በሁሉም ውድድሮች ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
ቼልሲ ከሶስት የሊግ ጨዋታዎች ነጥብ መጣል በኋላ ወደ ድል ተመልሰዋል።
የሊቨርፑልን መሸነፍ ተከትሎ አርሰናል ሊጉን መምራት ጀምሯል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
2️⃣ ሊቨርፑል :- 15 'ነጥብ
6️⃣ ቼልሲ :- 11 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
ቅዳሜ - ኖቲንግሃም ከ ቼልሲ
እሁድ - ሊቨርፑል ከ ማንችስተር ዩናይትድ