21/10/2025
💵👀 ከ16 አመት በፊት ሞሮኮ ለመሀመድ ስድስተኛ አካዳሚ ግንባታ 65 ሚሊየን ዶላር ፈሰስ አድርጋ ነበር።
በዚህ አካዳሚ ውስጥ 30 ሄክታር የሚሸፍን የእግር ኳስ ሜዳዎች፣ የቅንጦት ሆቴሎች፣ ጂም እና ትምህርት ቤቶች ሳይቀር ይገኙበታል።
ሞሮኮ ዋና አላማዋ የወደፊት ኮከቦችን ለማፍራት ነው። በዕቅዱ መሰረትም ጎዳና ላይ የሚጫወቱትን በመመልመል ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ ላይ ያተኮረ ነበር።
ፕሮጀክቱ ፍሬ አፍርቷል፡-
➡ ከ20 አመት በታች ቡድነለ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ።
➡ ከ23 አመት በታች ቡድኑ የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ።
➡ ከ17 አመት በታች ቡድኑ የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ።
➡ ከ20 አመት በታች ቡድኑ የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ተፋላሚ ሆነ።
➡ በ2024 የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይዛ አጠናቀቀች።
➡ በኳታር በ2022 የአለም ዋንጫ ለግማሽ ፍፃሜ የደረሰች የመጀመሪያዋ የአፍራካ ሀገር በመሆን አራተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች።
በታዳጊዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ለወደፊት እግርኳስ ብሩህ መንገድ ነው 👏🏻