04/10/2025
በለንደን ደርቢ አርሰናል ከ ዌስትሀም ዩናይትድ
************
አርሰናል በ7ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር ከዌስትሀም ዩናይትድ የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
11 ሰዓት ላይ በኢምሬትስ በሚደረገው ጨዋታ መድፈኞቹ ሊቨርፑል እስኪጫዎት ድረስ ሊጉን ለመምራት ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
ከዌስትሀም በሜዳው ባደረጋቸው ያለፉት ሁለት ጨዋታዎች የተሸነፈው አርሰናል ሦስት ነጥብ ለማግኝት ወደ ሜዳ በሚገባበት ጨዋታ ትልቅ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡
ከግርሀም ፖተር ስንብት በኋላ ኑኖ ስፕሪቶ ሳንቶን አሰልጣኝ አድርጎ የሾመው ዌስትሀም ዩናይትድ በአራት ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ቀን 8 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ ቶተንሀም ሆትስፐር ከሜዳው ውጭ ከሊድስ ዩናይትድ ይጫወታል፡፡