14/06/2026
የስኳር ህሙማን ስፖርት ከመጀመራችሁ በፊት ማድረግ ያለባችሁ 3 ቅድመ ጥንቃቄዎች
1. የህክምና ባለሙያ ማማከር
• ማንኛውም ዓይነት የአመጋገብ ለውጥ ከማድረጋችሁ በፊት ወይም ስፖርት ከመጀመራችሁ በፊት የህክምና ባለሙያ ብታማክሩ ተመራጭ ነው።
2. የደም ስኳራችሁን መከታተል
• ከስፖርት በፊት እና በኋላ የደም ስኳራችሁን ቼክ ማድረግ ይኖርባችኋል። ይህም ስፖርት በደም ስኳራችሁ ላይ ያለውን ተጽዕኖ ለመረዳት ይጠቅማችኋል። ኢንሱሊን የምትወስዱ ከሆነ ደግሞ የደም ስኳራችሁን በደንብ መከታተል አለባችሁ። የደም ስኳራችሁ ከመቶ በታች ከወረደ ቀለል ያለ ነገር ብትበሉ ይመረጣል። ከዛ ከ30 ደቂቃ በኋላ በመለካት የደም ስኳራችሁ ጥሩ ከሆነ ስፖርት መስራት ትችላላችሁ። ስፖርት ስትሰሩ አጠገባችሁ ከረሜላ ወይም ሌላ አነስ ያለ ጣፋጭ ነገር መያዝ ይኖርባችኋል። ይህ ድንገተኛ የሆነ በጣም ዝቅተኛ የደም ስኳር ወይም Hypoglycemia ከተፈጠረ ቶሎ ለማስተካከል ይረዳችኋል። በተለይ ኢንሱሊን የሚጠቀሙ ህሙማን ላይ ይህ የመከሰት እድሉ ሰፊ ነው።
3. ለስፖርት የሚሆን ጫማ ማድረግ
• ከስኳር ህመም መዘዞች አንዱ የእግር ቁስለት ነው። ይህ መዘዝ እግራችሁን የማትንከባከቡት ፣ ጽዳቱን የማትጠብቁት እና ጥፍራችሁን የማትቆረጡ ከሆነ የመከሰት እድሉ ሰፊ ነው። እንዲሁም ለስፖርት የማይሆን ደረቅ ጫማ አድርጋችሁ መስራት የለባችሁም። ስለዚህ እግራችሁን በየቀኑ ማየት እና መንከባከብ ፣ ጥፍራችሁን በየጊዜው መቆረጥ እና ለስፖርት የሚሆን ጫማ አድርጋችሁ ብትሰሩ ይመረጣል።
ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡