14/05/2026
የጥቁር ቀበቶ ትርጉም በሶስት ዋና ዋና ነጥቦች ይጠቃለላል፦
እውነተኛ ጀማሪ መሆን፦ ማርሻል አርቱን መጨረስ ሳይሆን፣ መሰረቱን አውቆ እውነተኛውን ጥልቅ ትምህርት አሁን መጀመር ነው።
የባህሪ እና የሞራል አምባሳደርነት፦ በትህትና፣ በራስ መቆጣጠር (Ego) እና በከፍተኛ ስነ-ምግባር ለሌሎች አርአያ መሆን ነው።
የመጠበቅና የማስተማር ኃላፊነት፦ ታናናሽ ተማሪዎችን መደገፍ፣ ጥበቡ እንዳይበረዝ መጠበቅ እና ጉልበትን ለጥቃት ሳይሆን ለደህንነት ብቻ መጠቀም ነው።
ስለዚህ ጥቁር ቀበቶ የስልጣን ሳይሆን የትህትና እና የከባድ ኃላፊነት መሸከሚያ ምልክት ነው።
by sensei yared
https://t.me/yjoshotokankarateclub