13/01/2021
ረዕቡ የወጡ የዝውውር ዜናዎችና መረጃዎችን ያንብቡ - Latest Transfer News Update!
ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማድረግዎን አይርሱ!
ከተመቻቹ ደግሞ ሼር ያርጉት።
═════════════════════════
ባርሴሎና በቀጣዩ ክረምት ከማንችስተር ሲቲ ጋር ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን ሰርጂዮ አጉዌሮን በነፃ ዝውውር ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል።( Sun Sport)
════════════════════════
ዶርትመንድ አሁን ጄደን ሳንቾን ለመሸጥ ተዘጋጅቷል የስቱት ጋርቱን የፊት መስመር ተጫዋች ታንጉይ ኳሊባሊን ለመተካት እየተመለከቱ ነው ተብሏል።(France Football)
════════════════════════
የቸልሲው ባለቤት ሮማን አብራሃምኦቪች የቀድሞ የሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ የነበረውን አቭራሃም ግራንትን የአሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ምክትል አሰልጣኝ አድርገው ወደ ስታምፎርድብሪጅ ለማምጣት እያጤኑ እንደሚገኙ ተዘግቧል። (Sky Sports)
═════════════════════════
ሬያል ማድሪድ ፈረንሳያዊውን የ 22 አመት አጥቂ ኬለን ምባፔን በቀጣዩ በቀጣዩ ክረምት ወደ ሳንቲያጎ በርናበው ለማምጣት 6 ተጫዋቾችን የመሸጥ እቅድ እንዳላቸው ተነግሯል።ጋሬዝ ቤል፣ማርሴሎ፣ሉካ ዮቪች፣ኢስኮ፣ሴባዮስ እና ብራሂም ዲያዝ ናቸው።(AS - in Spanish)
═════════════════════════
የማንችስተር ዩናይትዱ ተከላካይ ቲሞቲ ፎሱ ሜንሳ በቀያይ ሴጣኖቹ የቀረበለትን አዲስ ኮንትራት አልፈርም በማለት ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ በ £1.5m ወደ ጀርመኑ ክለብ ባየርሊቨርኩሰን ሊዘዋወር መሆኑ ተዘግቧል።(Manchester Evening News)
═════════════════════════
አሰልጣኝ ኑኖ ሳንቶስ ስፕሪንቶ የአጥቂ ክፍል ችግራቸውን ለመቅረፍ ከቸልሲ ኦሊቨር ዤሩድን እና የሊቨርፑሉን አጥቂ ዲቮክ ኦሪጊን እንዲጉለት እንዲገዙላቸው ለክለቡ ቢነግሩም ክለቡ ግን በጥሩ የዝውውር መስኮት ምንም አይነት ገንዘብ ለተጫዋቾች ለመመደብ ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ነግረውታል። (Mirror)
═════════════════════════
ባየርሙኒክ በክረምቱ ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን የሬዲንጉን የ 22 አመቱን ተከላካይ ኦማር ሪቻርድስን ቅድመ ኮንትራት ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።ኤቨርተን እና ዌስትሃም የተጫዋቹ ፈላጊ ናቸው ተብሏል።(Guardian)
═════════════════════════
የናፖሊው ተከላካይ ካሊዶ ኩሊባሊ ስሙ በስፋት ከሊቨርፑል፣ከማንችስተር ሲቲ እና ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ተያይዞ እየተነሳ ይገኛል የኔፕልሱ ክለብም £100m የሚያቀርብለት ክለብ ካለ በዚህ በጥሩ የዝውውር መስኮት የ 29 አመቱን ሴኔጋላዊ ለመሸጥ ዝግጁ ናቸው ተብሏል።(Talksport)
═════════════════════════
ብራዚላዊው አማካይ ካስሜሮ በአሁን ሰዓት በሬያል ማድሪድ ከሚገኙ ተጫዋቾች አሁን ባለው ገበያ ውዱ ተጫዋች ነው ሲል የ audit Specialists KPMG ሪፖርት ያሳያል። (Mundo Deportivo - in Spanish)
═════════════════════════
የ 24 አመቱ ስፔናዊ የግራ መስመር ተከላካይ ጁኔሮ ፊሪፖ በተለያዩ ክለቦች ቢፈለግም በዚህ የዝውውር መስኮት የመልቀቅ ፍላጎት ስለሌለው በካምፕኑ መቆየት ምርጫው ነው ተብሏል። (Marca)
═════════════════════════
ሚሱት ኦዚል ከቲውተር ተከታታዮቹ ጥያቄ እና መልስ እያደረገ ነበር በዚህ ግዜ ለቶተንሃም ከመፈረም እና ጫማክን ከመስቀል የተኛውን ትመርጣለክ ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ ኦዚል "ለ ቶትንሃም ከምፈርም ጫማየን ብሰቅል ይሻለኛል" ሲል መለሰ ይህን ጋዜጠኞች ጆሴን ሲጠይቋቸው ጆዜ ሞሪኒሆ "ማነው ቶትንሃም ሊአስፈርምህ ይፈልጋል ብሎ የነገረው ሲል ጥያቄ በሚመስል መልኩ በነገር ሸንቆጥ አድርገውታል። (The Sun)
═════════════════════════
ኤስሚላን የ 23 አመቱን እንግሊዛዊ የመሀል ተከላካይ ፊካዮ ቶሞሪን እስከ ሲዝኑ መጠናቀቅ ድረስ በውሰት የማስፈረም ፍላጎት አላቸው።(The Guardian)
═════════════════════════
የሌስተር ሲቲው አልጄሪያዊ አጥቂ ኢስላም ስሌማኒ ወደ ፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን ለመዘዋወር የጤና ምርመራ እያደረገ ይገኛል። (Sky Sports)
═════════════════════════
የአርቢላይፕዚኩ ፈረንሳያዊ ተከላካይ ዳዮት አፕሜካኖ በባየርሙኒክ እየተፈለገ ይገኛል፤ቸልሲ እና ማንችስተር ዩናይትድም የተከላካዮ ፈላጊ ክለቦች ናቸው። (Marca)
═════════════════════════
ቶተንሃም፣ሼፊልድ ዩናይትድ፣ሬንጀርስ እና ሴልቲክ የ 19 አመቱን አጥቂ ኬየል ጆሴፍን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል።(Mirror)
═════════════════════════
ዌስትሃም £7m በመደብ ከማርሴ ጋር እየተፎካከረ ይገኛል የ 26 አመቱን ፖላንዳዊ አጥቂ አርካዲዝ ከናፖሊ ለማስፈረም።(Radio Kiss Kiss via SportWitness)
═════════════════════════
የሞናኮ የቀኝ መስመር ተከላካይ ጂብሪል ሲዲቤ በክሪስታል ፓላስ እና ኒውካስል ቢፈለግም ወደ እንግሊዝ የመምጣት ፍላጎት ስለሌለው አሁን ባለበት ፈረንሳይ መቆየት ምርጫው ተብሏል። (France Football via Sport Witness)
═════════════════════════
ቶተንሃም ሆስፐር የ 22 አመቱን ብራዚላዊ ተከላካይ ኤደር ሚሊቶን ከሬያል ማድሪድ በውሰት ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው፤ሮማ፣ኤስ ሚላን እና ኢንተር ሚላንም ተጫዋቹን በውሰት በመውሰድ እንደብቃቱ በቋሚነት ለመግዛትም እቅድ አላቸው ተብሏል።(Corriere dello Sport - in Italian)
═════════════════════════
የስፐርሱ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪኒዮ ሊድስ እና ዩቬንቱስን በመቀላቀል የስቱት ጋርቱን የ 22 አመት አርጀንቲናዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ኒኮላስ ጎንዛሌዝን ከወዲሁ ለቀጣዩ ክረምት ኢላማቸው አድርገውቷል።(Athletic subscription required)
═════════════════════════
ቫሌንሺያ የ 24 አመቱን እንግሊዛዊ አማካይ ሀሪ ዊንክስን በውሰት የማስፈረም ፍላጎት አላቸው ተብሏል።(Football London)
═════════════════════════
ብራይተን የማንችስተር ዩናይትድ ኢላማ የነበረውን ኢኳዶራዊውን አማካይ ሞይስ ካይሴዶን ከኢንዲፔንዴንቴ ኒውካስልን በመርታት እንደሚያስፈርሙት እርግጠኛ ናቸው። (Talksport)
═════════════════════════
ማንችስተር ዩናይትድ እና ቸልሲ ደግሞ የ 19 አመቱን አማካይ ካይሴዶን ማስፈረም የሚፈልጉት በውሰት ብቻ መሆኑ ተነግሯል።(Mail)
═════════════════════════
አርሰናል ከብራይተን የ 24 አመቱ ማሊያዊ አማካይ ዩቪስ ቤሳውማን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ኢላማቸው አድርገውታል። (Football London)
═════════════════════════
የሊዮኑ ፈረንሳያዊ አጥቂ ሙሳ ዴንቤል ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ለመዘዋወር ከጫፍ ደርሰዋል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ቀጣዮቹ ቀናት ዝውውር ይፋ እንደሚደረግ ተዘግቧል።ዝውውሩ ይህ ሲዝን እስከሚጠናቀቅ በውሰት ይሆን እና ከወደዱት ደግሞ በ €35m የውሰት ውሉ በአመቱ መጨረሻ በቋሚነት የማስፈረም አማራጭም ማካተታቸው ተዘግቧል። (Telefoot via Sky Sports)
═════════════════════════
DEAL DONE: ሮብ ሆልዲንግ በአርሰናል እስከ 2024 የሚያቆየውን የረጅም ግዜ ኮንትራት መፈረሙ ተረጋግጧል።(Arsenal)
════════════════════════
ኬቨን ስትሩትማን ከማርሴ በመልቀቅ ወደ ጄኖዋ በቋሚ ዝውውር ለመዘዋወር ወደ ጣልያን ማምራቱ ተዘግቧል።(DiMarzio)
════════════════════════
ሰርቢያዊው አጥቂ ሉካ ዮቪች በሬያል ማድሪድ ያልተሳካ ግዜን እያሳለፈ መሆኑን ተከትሎ ወደ ቀድሞ ክለቡ ኢንትራንክፍራንክፈርት እስከ አመቱ መጨረሻ በውሰት ሊያመራ መሆኑ ተራግሯል።( GOAL)
════════════════════════
ሜሱት ኦዚል ስለ ሰርጂዮ ራሞስ :
"ሰርጂዮ ራሞስ በእኔ ጊዜ ካሉ ተከላካዮች ምርጡ ተከላካይ ነው" ሲል ተናግሯል።
═════════════════════════
አርሰናል ኢላማ ያደረገውን የ 24 አመቱን አርጀንቲናዊ አማካይ ኤሚሊ ቡዌንዲያን በዚህ በጥሩ የዝውውር መስኮት የማስፈረም እድል የለውም ተብሏል ምክንያቱ ደግሞ የተለጠፈበት የዝውውር ዋጋ £40m በመሆኑ ነው ተብሏል። (Express)
═════════════════════════
የቸልሲው አማካይ ቲሞ ባካዮኮ ወደ ጣልያን በሄደበት ናፖሊ መልካም የሚባል ግዜ እያሳለፈ በመገኘቱ የጣልያኑ ክለብ ተጫዋቹን በቋሚነት የግሉ ለማድረግ ተዘጋጅቷል።(Star)
═════════════════════════
ትላንት በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እና በስፔን ላሊጋ የተደረጉ ጨዋታዎች
🏴 በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ
ወልቭስ 1-2 ኤቨርተን
ሼፊልድ 1-0 ኒውካስትል
በርንሌይ 0-1 ማንችስተር ዩናይትድ
🇪🇸 በስፔን ላሊጋ
ግራናዳ 2-0 ኦሳሱና
አትሌቲኮ ማድሪድ 2-0 ሴቪያ
════════════════════════
ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች
🏴 በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ
03:00 | ማንችስተር ሲቲ ከ ብራይተን
05:15 | ቶተንሀም ከ ፉልሀም
🇪🇸 በስፔን ሱፐር ካፕ
05:00 | ሪያል ሶሲዳድ ከ ባርሴሎና
🇮🇹 በኮፓ ኢታልያ
11:00 | ፊዮሬንቲና ከ ኢንተር
01:45 | ናፖሊ ከ ኢምፖሊ
04:45 | ዩቬንቱስ ከ ጄኖዋ
════════════════════════
👍) ከተመቻቹህ ላይክ ያድርጉ
✍🏾አሳብ አስተያየት ካላቹህ ኮመንት ላይ ፃፉልን ፣
👌ለሌሎች ጎደኞቻቹህ እዲድርስ ሸር ያድርጉ፣