12/10/2024
02/02/2017 ዓ.ም
በቦሌ 17 የጤና እግር ኳስ ማህበር እና በታገስ ስጋ ቤት አዘጋጅነት ለወንድማችን ፍፁም ብርሃኔ መታሰቢያ በሻላ ሁለገብ ሜዳ ሲካሄድ የቆየው የፉትሳል ውድድር በዛሬው ዕለት ፍፃሜውን አግኝቷል።
የፍፃሜ ጨዋታ ውጤት
ኪያ ስቱዲዮ 0-2 ሻላ አብሮ አደግ
የሻላ አብሮ አደግ ቡድን የውድድሩ አሸናፊ በመሆኑ የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን አብዲ እሸቱ ከሻላ አብሮ አደግ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች እንዲሁም ሄኖክ አለማየሁ ከእንጦጦ ስላሴ B በ 8 ጎል የውድድሩ ኮከብ ግብ አግቢ በመሆን ተሸላሚ ሆነዋል።
ለዚህ ውድድር መሳካት ድጋፍ እና ትብብር ላደረጉ:
ታገስ ስጋ ቤት
ደሬ ማስታወቂያ
ኪያ ስቱዲዮ
ሎጬ የስፖርት ትጥቅ መሸጫ
ቦሌ ፋና ሸማቾች ሕ/ስ/ሽ ማህበር
ወረዳ 3 ስፖርት ፅ/ቤት
ፍፁም ተዘራ
አዲስ ተ/ማርያም
ተመስገን ተሰማ እና
ይትባረክ ከተማ በተጨማሪም
ለአስሩም ተሳታፊ ቡድኖች የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።
ለመላው የሻላ አብሮ አደግ የጤና ቡድን አባላት እና ደጋፊዎች በሙሉ የውድድሩ አሸናፊ በመሆናችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ።
⚽️🏆🎉🎊