03/05/2026
ከ2008 በሗላ በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ አዲስ ነገረ ወደ ስታዲየም መጣ። እነዛ 20 ናቸው 30 ናቸው የሚሉትን የተቃራኒ ክለብ ደጋፊዎች እና ጋዜጠኞችን ኩም ያደረገ ሪቮሊውሽን ተፈጠረ። በተለያየ መንገድ ብትንትን ብሎ የነበረው የኢትዮጵያ እግርኳስ ድጋፍ ወደ የሚያምር ወደ የሚያስደነግጥ የህብረት የቅብብሎሽ ድጋፍ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ቀየሩት። ለዚህ ለውጥ ብዙ ዝግጅት በህብረት በመተጋገዝ በመተባበር ቢደረግም ዋናው መሪ ደሞ ኢዮባ ሳንጃው አበባ ነች። ብዙ ነገር ቀየረች እዮባ ብዙ አዳዲስ የሚያማምሩ የድጋፍ ስልቶችን ይዛ መጣች፣ በአንዴ የስታዲየም ድባብ ከተራ ነቆራና ብትንትን ካሉ ጩኸቶች ወደ ሚያምር ውብ ወደሆነ ድባብና ድጋፍ ተቀየረ። የተቃራኒ ክለብ ደጋፊዎች ካቅማቸው በላይ ያላሰቡት ነገር ስለገጠማቸው በድንጋጤ ኩም አሉ፣ በአድናቆት እስኪፈዙ ጋዜጠኞች ጊዜ ሰተው እስኪዘግቡ እና እስኪቀኑ ድረስ ተደነቁ። ቅዱስ ጊዮርጊስ ከማንም ጋር ሲጫወት ስታዲየሞች መሙላት ጀመሩ ከ 2008 በፊት ሚስማር ላይ በድፍረት ማሊያ ለብሰው የሚገቡት 4 ልጆች ብቻ ነበሩ (ተስፍቲ , እዮብ ,ቴዲ እና ብራቮ ብራቮ ሳንጃው) ብቻ ነበሩ። ከ 2008 በሗላ ግን ሚስማር በቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ ተወረሰ። አትደነቅም ያኔ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በተለያየ ምክንያት ከሜዳ የራቀው ደጋፊ ወደ ስታዲየም እዲመለስ አዳዲስ ደጋፊዎችም አስገራሚ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችን የስታድየም የድጋፍ ውበት በማየት ወደ ስታዲየም በአስደናቂ ሁኔታ በጣም በብዛት መምጣት መትመም ጀመሩ።
ሌላው አስገራሚ ነገር ከተቃራኒ ክለብ ደጋፊዎች ያንን ክለብ በመተው ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊነት በብዛት መቀየር ጀመሩ፣ በየ ሀገሩ በየከተማው በየሰፈሩ የቅዱስ ጊዮርጊስ ማሊያን በሚያረጉ ወጣቶች በየቀነኑ መተራመስ ጀመረ። በእውነት ይሔን ማየት ህልም ነበር። ደስታዬ ወደር አልነበረውም አስቡት እስኪ ቀስ እያሉ እኮ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊን እየሸረሸሩ እያጠፉት ነበር።
በፊት የቅዱስ ጊዮርጊስን ማሊያ ያረገ ሰው መንገድ ላይ ማየት ብርቅ ነበር፣ በተለይ ከ 2003 እስከ 2007 ድረስ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊን ከሜዳ የማጥፋት ነገር ቴክኒካሊ ሲሰራ ነበር። እድሜ ለጋዜጠኞች ሚድያው የአንድ ክለብ እስኪመስል ድረስ ቅዱስ ጊዮርጊስን አገለሉት፣ ስለእኛ ሚድያ ላይ መስማት ብርቅ ነበር። በተጨማሪም ሙስና የሚል ቅጽል ስም በመስጠት በአሉባልታና በተለያየ መንገድ ደጋፊውን አሸማቀው እያጠፉብን ነበር። ነገር ግን አልተሳካላቸው።
ከ 2008 በሗላ የተጀመረው የደጋፊዎች ወደ ስታዲየም የመመለስ ሪቮሊውሽን ከሚያማምር የስታዲየም የቅብብሎሽ ድጋፍ ጋር ደጋፊው ወደሜዳ ተመለሰ አስገራሚ ነው፣ ሙሉ እታዲየም በቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በቁጥጥር ስር ዋለ። 20 ናቸው ብለው ሲጨፍሩብን የነበሩ አፈሩ ፣ እነሱ የሚቀመጡበትን ሚስማር ተራን ጨምሮ ቀኝ ጥላፎቃቸው ሁሉንም መቀመቻቸውን ወረስነው፣ ፈነጨንበት፣ ጨፈርንበት 2009 አይወራ የደጋፊው ድባብ እየጨመረ መጣ፣ ፍላሽ ላይቶች መጠቀም ጀመርን፣ የኛ የድጋፍ ስልቶችም ሌላ ክለቦች መኮረጅ መዝረፍ ጀመሩ አይፈረድባቸውም የሚያምር ነገር አይተው እዴት ይለፉት። የሚገርመው ነገር እነ እንትና 2010 አስፈርቷቸው ስለነበር 2009 ክረምት ድጋፍ ጥናት ብለው ተሰብስበው ሜክሲኮ ቡና እና ሻይ ማጥናት ጀመሩ። ነገር ግን የፈሩት አልቀረም 2010 የቅዱስ ጊዮርጊስ አዲሱ ትውልድ በገፍ ወደ ስታድየም መትመም ጀመረ። ከዚህ በላይ ምን ደስታ አለ በአዲሱ ትውልድ ልበ ሙሉ ማንንም የማይሰማ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ የኢትዮጵያ እግርኳስን ተቆጣጠረ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ እደ አሸን ፈላ በእውነት በጣም አስደሳች ነው ጥሩ መስመር ላይ ባለንበት ኮሮና የሚባል ምቀኛ በሽታ መጣና እስታዲየሞችን ወና አረጋቸው ኮሮናም ካለፈ በሗላ በከተማችን ጨዋታዎችን ማረግ አልቻልንም ነገር ግን አሁን ላይ ጨዋታዎች ለደጋፊ ክፍት እየሆኑ ስላሉ የድጋፍ ነገር አሳሳቢ ነው ክለባችንን ቅዱስ ጊዮርጊስ ለመደገፍ ከመሯሯጥ አዲስ ነገር ከማምጣት ይልቅ ደጋፊውን ወደ እስቴድዮም ከመመለስ ይልቅ ካታንጋ ጥላፎቅ እየተባባሉ አዱን ከፍ አንዱን ዝቅ ለማረግ በሚመስል መልኩ መንቀሳቀስ ይታያል ይህ ተገቢ አይደለም ሁሉም ቦታዎች የቅዱስ ጊዮርጊስ ቦታዎች ናቸው ሁሉም መድመቅ አለበት የአንዱ ቦታ መፍዘዝ የቅዱስ ጊዮርጊስ መፍዘዝ ነው ተራ ነገሮች ቀርተው ደጋፊው በሙሉ ሀይይሉ ወደ እስታዲየም የሚመለስበትን ነገር በማሰብ ከወዲሁ ለ 2019 ዝግጅት ማድረግ አለብን በእዮባ ሳንጃው የተሰሩ መዝሙሮች በበቂ ሁኔታ እስታድየም ውስጥ እየተዘመሩ አይደለም በግል ተጫዋች እና አሰልጣኝን ከቡዱኑ ነጥለን ከሚጨፈር ሙሉ ቡዱናችንን መስዋት ከፍሏል ስለዚህ ሁሉንም የሚያበረታቱ መዝሙሮቻችንን ብንጠቀም መልካም ነው አስጨፋሪዎችም አዳዲስ ነገር እስኪፈጠር ይሔን አርጉ በህብረት መዝሙሮቻችን ከፍብለው ይዘመሩ ጣፋጭ ናቸው።
በመጨረሻም አዳዲስ ፊት አቅም ያላቸው ግጥም መፍጠር የሚችሉ አዳዲስ ነገር መፍጠር የሚችሉ አስጨፋሪዎች መጨመር አለባቸው ለ 2019 ካሁኑ ስራዎች መሰራት አለባቸው ያ ውብ ድጋፍ መመለስ አለበት ሞዛይኮች መሰራት አለባቸው እስታዲየም ነፍስ እዲዘራ ውብ እዲሆን ማድረግ አለብን✌️❤
ምንጊዜም ቅዱስ ጊዮርጊስ ✌️❤
#ሼር #ቅዱስ #ጊዮርጊስ