04/08/2019
MICHAEL JORDAN
ማይክል ጄፍሪ ጆርዳን, አሜሪካዊ የቀድሞ ታዋቂ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ሲሆን እ.ኤ.አ ጥቅምት 13, 1963 በብሩክልን, ኒውዮርክ ተወለደ።
ማይክል ጆርዳን ( MJ) በቅርጫት ኳስ ከታዩ ተጫዋቾች የምንግዜም ምርጡ እና ከአትሌቶች Brand መሆን ከቻሉ ስፖርተኞች ቀዳሚ ከዚም በተረፈ ለስፖርቱ በ 1980 ዎቹ እና 90ዎቹ ታዋቂነት ዋነኛ ተጠቃሽ ነው።
ማይክል በ NBA ለ ቺካጎ ቡልስ እና ዋሺንግተን ዊዛርድስ ተጫውቶ አሳልፏል።
ማይክል በNBA ለ 15 ሲዝኖች መጫወት የቻለ ሲሆን በዚም 6 ግዜ ከቡልስ ጋር የNBA ቻምፒዮን መሆን ችሏል።
ጆርዳን 3 ግዜ ጡረታ የወጣ ሲሆን የመጀመሪያው በ1993- 94 ከወጣ ብኋላ በ1995 ተመልሷል። ለ2ኛ ግዜ በ1999 ቢወጣም በ2001 በመመለስ እስከ 2003 ለዊዛርድስ ተጫውቷል ። ማይክል በ 2003 ከፊላዴልፊያ ጋር በተደረገ ጨዋታ ለሁለተኛ ግዜ ወደ ተቀያሪ ሲቀመጥ 21 ሺ የሚደርሱ ጨዋታውን የታደሙ ተመልካቾች ለ 3 ደቂቃ ቆመው አጨብጭብውለታል ይህም የማይክል በNBA የመጨረሸው ጨዋታ ነበር።
ጆርዳን አየር ላይ ተነስቶ በሚያስቆጥራቸው ኳሶች ይታወቃል። ይህም "AIR JORDAN" የሚለውን የቅፅል ስም አሰጥቶታል።