29/08/2026
በማድረግ ለደጋግ ሰዎች እንዲደርስ እናድርግ🙏
ጃፋር መሀመድ የተባለው ወንድማችን ነዋሪነቱ በወሊሶ ከተማ 02 ኢጀርሳ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን የሁለት ልጆች አባት ነው።
ትልቁ መስጂድ ጀርባ ላይ በብረታብረት ብየዳ ስራ የሚታዳደር ታታሪ ሰራተኛ ነበረ በአሁኑ ስዓት ግን በህመም ምክንያት ስራውን አቁሞ ከወሊሶ ቅዱስ ሉቃስ ሆስፒታል ወደ በአዲስ አበባ ለከፍተኛ ህክምና ተልኮ በአለርት በአሚን ሆስፒታሎች ምርመራ አድርጎ የጨጓራና የጉበት ካንሰር እንዳለበት ተነግሮት አፋጣኝ የቀዶ ጥገና እንደሚያስፈልገው እስከዛው ግን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኬሞቴራፒ ሕክምና እንዲያደርግ በተሰጠው የሀኪም ትዕዛዝ መሰረት እያደረገ ይገኛል።
ሆኖም ለቀዶ ህክምናው ገንዘብ የሚያስፈልግ ሲሆን ወንድማችን ለቀዶ ህክምና የተጠየቀው ገንዘብ ቀርቶ በየጊዜዉ ለሚያደርገው የኬሞቴራፒ ወጪ እጅ እያጠረው ስለሚገኘ ሁላችንም በቻልነው አቅም ሁሉ ወንድማችንን እንርዳው ።
ለዚህም ይሆን ዘንድ በራሱና በሰፈር ልጅ እንዲሁም በመስኪድ አካባቢ ጓደኞች የተቆቆመ ኮሚቴ በከተማችን ወሊሶ ውስጥ እርዳታ ለማሰባሰብ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ።
ለዚህ እርዳታ እንዲሆን የባንክ አካውንት የተከፈተ ሲሆን በከተማ ውስጥ ያላቹ በአጠቃላይ አነሰ በዛ ሳትሉ ያቅማቹን እጃችሁን ትዘረጉላቸው ዘንድ በአክብሮት እየጠየቅን🙏 ከከተማ ውጪ በተለያዩ ከተሞች እና ከሀገር ውጪ ያላችሁ የከተማችን ተወላጆች እና ደጋግ ኢትዮጲያውያን በሙሉ 50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለ50 ሰው ጌጡ ነው እንደሚባለው አነሰ በዛ ሳንል ሁላችንም በሚከተሉት አካውንቶች በመጠቀም የአቅማችንን ድጋፍ በማድረግ ከፈጣሪ በታች ህይወቱን እንታደግ።
CBE 1000786020267
Coop 1002100406671
Awash 0132017957599001
ለበለጠ መረጃ
0904174515
0912209189