26/03/2024
የኬቨን ዴብሮይን የማንችስተር ሲቲ ቆይታ ?
ቤልጂየማዊው የማንችስተር ሲቲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን በአሜሪካ እና ሳውዲ አረቢያ ክለቦች እየተፈለገ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ኬቨን ዴብሮይን አሁን ላይ ሙሉ ትኩረቱን ማድረግ የሚፈልገው የመጨረሻ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በሚገኘው የውድድር አመት ማጠናቀቂያ ወቅት ላይ እንደሆነ ተነግሯል።
በውድድር አመቱ መጨረሻ ኬቨን ዴብሮይን ከሌሎች ክለቦች ጋር ከመነጋገሩ በፊት በኮንትራቱ ዙሪያ ከማንችስተር ሲቲ ባለስልጣናት ጋር እንደሚነጋገር ተዘግቧል።