04/04/2023
+ + +
ፕሮቴስታንቶችና የጣና ገዳማት፦
* * *
ፕሮቴስታንቶችና የጣና ገዳማት ማለት፡ ልክ አይሁዶችና አክሱም ጽዮን ማለት ናቸው። አይሁዶቹ፡ ታቦተ ጽዮንና ድንግል ማርያምን ክደው ሳለ፡ በስሕተት፡ እስካሁን የነርሱ ንብረት እንደምትመስላቸውና ሊወስዷት እንደሚፈልጉ ኹሉ፡ የአውሮፓ ፕሮቴስታንቶችም፡ በጣና ያሉና የነበሩ መንፈሳዊ እውነታዎችን ኹሉ ክደው፡ በወደቁ መላእክት መሪነት፡ የውሸት ክርስትና ይዘው ለዘመናት ኮትልከው ሲንገዳገዱ ከኖሩ በኋላ፡ ዛሬ ከመሬት ተነሥተው ጣና፡ የነርሱ ንብረት እንድትኾንላቸው ይፈልጋሉ።
ነገሩ እንዲህ ነው፦
የመጀመሪያዋ ፕሮቴስታንት የእንግሊዝ ንግሥት፡ ኤልሳቤጥ አንደኛ፡ "እኔ ንግሥተ ሳባ ነኝ፤ እኔ የድንግል ማርያምን ቦታ የተካሁ ባል ያላገባሁ ድንግል ነኝ፤ እኔ የጽዮን ንግሥት ነኝ" ብላ፡ ሕዝቧን ከሮም ግዛት አላቅቃ፡ በራሷ አምባገነን ዘውድ ሥር፡ በAnglican church በኩል እንዲደራጅላት ካደረገች በኋላ፡ የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብር ለመገዳደር ስትል፡ በመላዋ እንግሊዝ፡ እንደ ድንግል እንድትወደስና እንዲዘመርላት አስደረገች።
ሴትዮዋ፡ አንድ ከድቅሎች የተወለደ የሬኔሳንስ ሳይንቲስትን፡ ጭንቅላቱን አይታ፡ አማካሪዋ አደረገችው። ሰውየው፡ በሳይንሱ ዓለም እጅግ ስሙ የገነነ ነው። ያው የድቅል ልጅ ስለኾነ፡ የወደቁት መላእክትን "ጥበብ እና ፍልስፍና" በጣም ይወድዳል።
ከጊዜ በኋላ ግን፡ እውነተኛው ጥበብና ፍልስፍና፡ በሐዋርያት የተሰበከውና በመንፈስ ቅዱስ መውረድ የጸናው የኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ጥበብ መኾኑን ተረዳ። ስለዚህ፡ ወዳጁን ቆሪጥን (ሉሲፈርን) እየጠራ፡ ኢትዮጵያን ሰልሎ እንዲመጣ ይልከው ጀመር።
ቆሪጡ፡ ወደ ኢትዮጵያ እየመጣ፡ ሰልሎ መመለስ ጀመረ። መረጃም ይነግረው ነበር። በተለይ ሰልሎ የሚመለሰው፡ ጣና ገዳማትን ነበር። ምክንያቱም፡ ከመጀመሪያው የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ("በዓለ ጴንጤ ቆስጤ") ጋር የተያያዙ አስደናቂ መንፈሳዊ ክስተቶች፡ ታሪካቸው፡ በጣና ገዳማት ተጽፈው ስለሚገኙ ነው። ይኽ ደግሞ፡ ለጴንጤነታቸው ማጠናከሪያ እንዲኾንላቸው ወደራሳቸው ታሪኩን ማዞር ፈለጉ። መንፈስ ቅዱስ ወርዶባቸው "በልሳን" መለፍለፍ ያለባቸው እነርሱ እንጂ፡ ሌላ መኾን የለበትማ! ምክንያቱም ሌላው አልበራለትም። በተለይ ኢትዮጵያዊ!
ሰውየውም፡ ቆሪጥ የሚያመጣለትን የተቆራረጠ መረጃ በመያዝ፡ ወደ አሜሪካ በማዞር፡ "ታሪኳን የጻፈ የለም እንጂ፡ አሜሪካ ወንጌልን የተቀበለችው ጥንት ነበር፤ መንፈስ ቅዱስ እዚያም ወርዷል። ለእኛም፡ መንፈስ ቅዱስ በዘመናችን ተገልጾልን ተረዳነው" በማለት፡ የውሸት የክርስትና ታሪክ፡ ለአሜሪካ ጻፈላት። የኤደን ገነትና የሥነ ፍጥረት ታሪክም ከእንግሊዝና ከአሜሪካ እንደጀመረ ብዙ መጻሕፍት ተጻፉ። "አሜሪካዊው አዳም" የሚባል እንቅስቃሴም ተጀመረ። ሌላውም "ዝንጀሮ ነው" ተባለ። ይኽ፡ የፍሪሜሰኖችም ቋሚ ትምህርትና እምነት ኾነ። ኤቫንጀሊካን ክርስቲያኖች፡ በአሜሪካዊው/እንግሊዛዊው አዳም እሳቤ፡ በድብቅ በጥልቀት ያምናሉ።
ነገር ግን፡ ፈጠራ ምን ጊዜም ፈጠራ ነውና፡ ታሪኩ ሊጸናላቸው አልቻለም። በተለይ፡ ይኽን ኹሉ የሚያወሩት፡ "ኢትዮጵያ፡ አንድ ቀን በእስልምና ወረራ፡ ወይም በእርስ በርስ ጦርነት ትጠፋልናለች። እኛም የኢትዮጵያን ታሪክ በሙሉ ወስደን የእኛ ነው እንላለን" በሚል ምኞት ነውና፡ ያ ሳይኾን ስለቀረ፡ ታሪኩ በስፋት በዓለም ሕዝብ ሳይታመንላቸው ቀረ።
ስለዚህ፡ ከቅርብ ዘመናት ወዲህ ሊጀምሩ የሚፈልጉት አዲስ ፕሮፓጋንዳ ፈጥረው ዳር ዳር እያሉ ነው። እሱም "የጴንጤ መሠረቱ ጣና ነው፤ ከጣና ተነሥቶ፡ እምነቱ ወደእንግሊዝ ኼደ፤ ነገር ግን እንግሊዝ ኼዶ ተዳከመ። አሁን በጣና ተመልሶ ክርስትና እንዳይጠፋ፡ እንዲህ ያለ ሥልጠና ውሰዱ" በማለት፡ መጻሕፍትን ማስገባት ጀምረዋል። አስገቢዎቹም፡ ቢጫ ለብሰው ተመሳስለው የገቡ ኢትዮጵያውያን ካቶሊክ መነኮሳት ናቸው። ከሥልጠናው ፍሬ ሃሳብ አንዱ፡ "ክርስትናን ለመጠበቅ፡ ሥጋን በጾም ማድከም ተገቢ አይደለም፤ ሰው ታሪክ ለመጠበቅ ከፈለገ፡ መብላትና በሥጋው መጠንከር አለበት" የሚል ነው። እናም፡ መነኮሳቱ በጠዋት ተነሥተው ምግብ ላይ እንዲሰየሙ የሚያበረታቱ የሹክሹክታ ሥልጠናዎች፡ በጣና ገዳማት መነገር ከጀመሩ፡ ቆይተዋል። ምን ያኽል እንደተሳካላቸው እንጃ።
የአሁኑ ጉብኝት፡ የቀጠለው የቆሪጡ ስለላ ክፍል 405 መኾኑ ነው።
በጣና ያሉ የሥነ ፍጥረት መጻሕፍትም፡ በብርቱ ይፈለጋሉ። "አዳም በእንግሊዝ ተፈጠረ" የሚሉ ሞኛ ሞኝ ድርሰቶቻቸውን ለመደገፍ ማለት ነው።
የእኔ ቢጤው፡ ስለኢትዮጵያ የሥነ ፍጥረት መጀመሪያ መኾን ሲያወራ፡ ጴንጤውና ካቶሊኩ ተግቶ የሚያንጓጥጠው፡ ይኽን በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ቅርንጫፍን ጽ/ቤት (ማለትም የአራት ኪሎውን መንግሥት ተብዬ) ዓላማ ለማሳካት ነው።
ስንት ይኾን የሚከፍሏቸው?! አበስኩ ገበርኩ!!
የሌላው አይደንቀኝም። ስለኢትዮጵያ ለየት ያለ መንፈሳዊ ታሪክ በተነገረ ቁጥር፡ ከጴንጤውና ከካቶሊኩ ጋር አብረው የሚያሽሟጥጡትንና ተናጋሪውን የሚያሳድዱትን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መምህራንን ግን፡ ምን ይሏቸዋል?! በምን ቃልስ ይገለጻሉ?!
እግዚአብሔር ልቦና ይስጣቸው!
+ + +
© Dr. Meskerem Lechissa