Coach Terefe Mekonnen

Coach Terefe Mekonnen Kontaktinformationen, Karte und Wegbeschreibungen, Kontaktformulare, Öffnungszeiten, Dienstleistungen, Bewertungen, Fotos, Videos und Ankündigungen von Coach Terefe Mekonnen, TrainerIn, Graz.

አገሬ ኢትዮጵያ በነበርኩ ጊዜ እንደ ሌሎቹ አትሌቶች ውጤት አምጥቼ አገሬንና ወገኔን ለማስጠራት የነበረብኝ ችግር ምንድን ነበር? እንዴትስ ከማንም፥ ከምንም በላይ አብልጬ ከምወዳት እናት ሀገሬ...
26/10/2025

አገሬ ኢትዮጵያ በነበርኩ ጊዜ እንደ ሌሎቹ አትሌቶች ውጤት አምጥቼ አገሬንና ወገኔን ለማስጠራት የነበረብኝ ችግር ምንድን ነበር? እንዴትስ ከማንም፥ ከምንም በላይ አብልጬ ከምወዳት እናት ሀገሬና ወገኔ እንዲሁም ቤተሰቤ ተለይቼ ለስደት በቃሁ?
++++
በዓለማቀፍ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ አገራችንን ኢትዮጵያንና ባህር ኃይል መልሕቅ ስፖርት ክለብን ወክዬ በ1975 ዓ/ም (እኤአ 1983) እንግሊዝ አገር ጌትሼድ ከተማ በተደረገው የዓለም አገር አቋራጭ ውድድር በወጣቶች ተካፍዬ በግል 6ኛ የወጣሁበት ሲሆን አገራችን የቡድን አሸናፊ ሆና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ እንድትሆን ካደረጉት መካከል አንዱ ነኝ። ከዚያም በዚሁ ዓመተ ምህረት ሊቢያ ትሪፖሊ ላይ በተደረገው የአፍሪካ ወጣቶች ፌስቲቫል በ8 ኪ/ሜትር የመንገድ ላይ ውድድር እኔ 1ኛ፣ አንጋሶ ታልጋ 2ኛ፣ ዲሶ ዲሳሳ 3ኛ በመሆን ተከታትለን ገባን ከዚህ በኋላ ከላይ በጠቀስኳቸው ውድድሮችና ባስመዘገብኳቸው ውጤቶች ሞራሌ ተገነባ የበለጠ ውጤት ላሳደገኝና በጣም ለምወደው ባህር ኃይል መልሕቅ ስፖርት ክለብምም ሆነ ለአገራችን ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ጀመርኩ። ሆኖም የቀድሞ የኢትዮጵያ አትሌቶች አሰልጣኝ የነበረው ከ1976 ዓ/ም ጀምሮ በተከታታይ በደል ይፈፅምብኝ ጀመር ከላይ እንደጠቀስኩት በዓለም ሻምፒዮናውም ሆነ በሊቢያው ውድድር ውጤት ለሌላ ዓለማቀፍ ውድድሮች በወጣቶች መላክ ሲገባኝ እኔን በማስቀረት ከኔ በታች ውጤት ያላቸውን አትሌቶች ወደ ውጪ ይልክ ጀመር። እስከ 1978 ዓ/ም እንዲሁ ስታገል ቆይቼ በዚሁ ዓ/ም ባህር ኃይል የመኰንንነት እድል ሰጠኝ ወደ ካዴት ኮርስ ገብቼ ከዓመት በኋላ በሰብ ሌፍትናንት (ምድር ጦር አጠራር ምክትል መቶ አለቅነት) መዓረግ ተመርቄ የአስመራ ባህር ኃይል ማሰልጠኛ ማእከል የስፖርት ክፍል ሀላፊ ሆኜ ተመድቤ ሳገለግል የነበረኝ የአትሌቲክስ ስሜት አሁንም ሊቀዘቅዝ ባለመቻሉ በወቅቱ በነበረው የአስመራ አካባቢ በሻቢያ የቅርብ ርቀት ስለነበር ፀጥታው አስተማማኝ አልነበረም ከከተማ ወጣ ብሎ ልምምድ ለመስራት ሆኖም ግን ፀጥታው ደህና በሆነበት በከተማው ውስጥ ልምምድ በመስራት የስፖርት ጥማቴን ለማርካት መጣር ጀመርኩ። አንድ ቀን እኔም በጥረቴ እንደታወቁት አትሌቶች ያሳደገኝንና የምወደውን ባሕር ኃይልንም፣ የኢትዮጵያ ህዝብንም ሆነ ኢትዮጵያ አገራችንን የማስጠራት አላማዬ ስላልሞተ ዓላማዬን ለማሳካት ልምምዴን በፅናት ቀጠልኩ። በዚሁ ወቅት አዲስ አበባ ላይ በሰኔ ወር በየዓመቱ ለሚካሄደው የሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ የማራቶን ውድድር የኤርትራን ክፍለ ሀገር የሚወክል ቡድን ምርጫ የማራቶን ማጣሪያ ውድድር አስመራ ላይ ይካሄዳል ተባለ እኔም ለዚህ ውድድር እራሴን አዘጋጀሁ በዚህ ውድድር በአምላክ ኃያልነት አሸንፌ ለአዲስ አበባው ውድድር እድል አጋጠመኝ። ከዚያም አዲስ አበባ ላይ በተደረገው የሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ ውድድር ላይ በአጠቃላይ በዓለማቀፍ ደረጃ ከተካፈሉት 7ኛ፣ በ14ቱ ክፍለ ሀገር መካከል የአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ከተካፈሉት አትሌቶች መካከል 1ኛ እኔ ኤርትራን በመወከል፣ 2ኛ ተክዬ ገብረ ሥላሴ አርሲን በመወከል የኃይሌ ገብረ ሥላሴ ታላቅ ወንድም፣ አንድ ስሙን የዘነጋሁት ከባሌ 3ኛ ሆንን።
ውድ ይህን ፅሁፍ አንባቢያን ወገኖቸ ወደ ዋናው ቁምነገር እየገባሁ ነው በዚህ ባመጣሁት ውጤት ለሌላ ዓለማቀፍ ውድድር መታጨት ሲገባኝ ከኔ በኋላ 19ኛና 33ኛ የወጡትን ለኢንተርናሽናል ውድድሮች ወደ ጃፓንና ሆላንድ ሲልክ እኔን አስቀረኝ፡ አሁንም ተስፋ ባለመቁረጥ ልምምዴን በብሄራዊ ቡድንም ሆነ በክፍሌ ጠንክሬ በእልህ መስራት ቀጠልኩ። ከሁለት ዓመት በኋላ በ1981 ዓ/ም በፅናት ልምምዴን ቀጥዬ ከእኔና አሁን አውስትራሊያ የሚኖረው ወንድሜ አትሌት ዘሪሁን ግዛው ያልተሻለ ውጤት ያላቸውን ወደ አውሮፓ ላካቸው የተሻለ ሰዓት ማምጣት የሚቻልበትና ጥሩ የገንዘብ ክፍያ ያለበት ቦታ ዘሪሁንንና እኔን ግን ወደ ታንዛኒያ አሩሻ ማራቶን ላከን ታንዛኒያ አሩሻ ሀይለኛ ሙቀት ያለው ቆላማ ቦታ ነው ከ35 ኪ/ሜትር በኋላ እኔም ሆንኩ ዘሪሁን ግዛው በሙቀቱ የተነሳ ቀለጥን ጉልበታችንን በከንቱ አፍስሰን ወደ አገራችን ተመለስን።
ከአንድ ወር በኋላ ለሌላ ለ4 ዓለማቀፍ የማራቶን ውድድሮች ማለት ሦስት፣ ሦስት አትሌት ለእያንዳንዱ ውድድር ለቦስተን ማራቶን፣ ለንደን፣ ለሮተርዳም፣ ለሮም ማራቶን 12 አትሌቶች ያስፈልጋሉ ለዚህ ማጣሪያ ይደረጋል ተባለ በማጣሪያው እኔ 7ኛ ሆንኩ ማለት ከሚፈለጉት ውድድሮች አንዱን መወከል የሚያበቃ ውጤት አመጣሁ። ምርጫውና የት አገር እንደምንወዳደር ከ3 ቀን በኋላ ተነገረን በዚህም ለቦስተን ማራቶን በ1ኛ ደረጃ አበበ መኰንን፣ 2ኛ ጫላ ኡርጌሳ፣ 3ኛ መኮንን ቱሉ፣4ኛ ተረፈ መኰንን አለ የወቅቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ረጅም ርቀት አሰልጣኝ የነበረው አቶ ንጉሴ ሮባ ማራቶን አዘጋጁ 4 ሰው እጋብዝልሃለሁ ስላለ አለ። እኔም በዚህ ጊዜ በምርጫው ደረጃው ቅር አለኝ በአበበ መኰንን ቅሬታ የለኝም ምክንያቱም ከኔ የበለጠ ታዋቂና በበርካታ ዓለማቀፍ ውድድሮች ያሸነፈ ጀግና አትሌት ነው በማጣሪያውም 1ኛ ነው የወጣው፣ በጫላ ኡርጌሳም ቅር አልተሰኘሁም ምክንያቱም በማጣሪያው ከኔ በልጦ 6ኛ ነው የወጣው መኮንን ቱሉ ግን እኔ 7ኛ ስወጣ መኮንን ቱሉ 13ኛ ስለሆነ የወጣው በእርሱ ቅር ተሰኘሁ። ምክንያቱም ምናልባት ውድድሩ የተወሰነ ቀን ሲቀረው አዘጋጁ የ4 ሰው ወጪ አልችልም ቢል እኔን ሊያስቀር አይደለም ወይ ብየ ከሚግባቡኝ አትሌቶች ጋር ስንጨዋወት የእኔንና የአሰልጣኙን አለመግባባት የሚያውቁ ተረፈ ዝም በል ትሄዳለህ አትጨቃጨቅ አሉኝና ዝም አልኩ በመሃል 3 ሳምንት ጊዜ ነበረ ውድድሩ የቀረው። ውድ ወገኖቼ ሆይ! የሚያሳዝን ሁኔታ ተፈጠረ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለዚህ ዓለም ያበቃችኝ እናቴ ታማ ነበር ቅዳሜ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየችብኝ የእናቴን ሀዘን በደንብ ሳላወጣ በ4ኛው ቀን ወደ ልምምድ ሄድኩ ምክንያቱም እናቴን እንደሁ አጥቻለሁ ግን ይህን እድሌን ልጠቀምበት ብዬ። ከተወሰነ ቀን በኋላ ስብሰባ ተደረገና አበበ መኰንን፣ ጫላ ኡርጌሳ፣ መኮንን ቱሉ ዛሬ ከሰዓት በኋላ አሜሪካ ኤምባሲ ሄዳችሁ የቪዛ ፎርም ሙሉ ብሎ አሰልጣኙ አቶ ንጉሴ ሮባ ከአራታችን የሦስቱን ስም ሲናገር እዚያው ሰውነቴ ውኃ ሆነ እኔን እጂግ በጣም ያሳዘነኝ መቅረቴም ብቻ ሳይሆን ምትክ የማላገኝላትን የእናቴን ሀዘን በቅጥ ሳልጨርስ በመነሳቴና ወደ ልምምድ ሄጄ እንዲህ ዓይነት ሥራ መሰራቴ ነው “ወገኖች የዱላ ቁስል ይድናል፤ የሞራል ቁስል ግን አይድንም እጂግ በጣም ጎጂ ነው” ሞራሌ ተነካ፣ ህይወት አስጠላኝ፣ ተስፋዬን አከሰመው። ምን መሰላችሁ እኔን አስቀርቶ መኮንን ቱሉን ሊወስድ የቻለው በቦስተን ማራቶን ከውድድር በፊት የመግቢያ ክፍያ ስለነበረውና አትሌቱ ዘመዱ አሜሪካ ስለነበር እርሱ ጋ ለመሄድና መቅረት ስለሚፈልግ እርሱን ከወሰደው ያን የሚሰጠውን የመግቢያ ክፍያ ለአሰልጣኙ ለመስጠት እንደተነጋገሩ ፍንጭ ሰምቼ ነበር። እናም መቅረቴን እንደሰማሁ አሁን በህይወት የሉም ከዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬና ማስተር ቺፍ ሳህሌ ሙሉነህ የሚባሉ አሰልጣኞች ስለነበሩ ከነሱ ጋር ስለምግባባ በደል ደርሶብኛል የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ኮሚቴ ላይ መቅረብና በደሌን መክሰስ እፈልጋለሁ አልኩ ግን ሰሚ አጣሁ እንደተባለውም አሜሪካ ሄዱ አትሌቱም ሳይመለስ እዚያው ቀረ። ይህ ስለራሴ ገለፅኩላችሁ እንጂ በርካታ አትሌቶች ውጤት ሳያንሳቸው ለግለሰቡ አናጎበድድም ብለው የተቀበሩ ሲኖሩ በአንፃሩ ደግሞ በውጤታቸው ሳይሆን ወሬ በማንሿከክና ውጪ ሲልካቸው ውስኪ፣ ሽቶና የእጅ መንሻ በመስጠት ከሌላቸው ውጤት በላይ የተጠቀሙም እንዳሉ አውቃለሁ። እናም ከ3 ዓመት በኋላ ከላይ እንደገለፅኩት ወያኔ አዲስ አበባንና መላ አገሪቱን ሲቆጣጠር የወጣትነት አፍላ ጉልበቴንና ጥሩ ሰዓት ማምጣትና እንደሌሎቹ ጓደኞቼ ለአገሬ ማገልገል ሲገባኝ ይህ ሳይሆንልኝ በደረሰብኝ በደል በ34 ዓመቴ አገሬን፣ ቤተሰቤንና የምወደውን ወገኔን ጥዬ ለመውጣት ተገደድኩ።
አንድ ለወገኔ ልገልፀው የምፈልገው በ1975 ዓ/ም ወደ እንግሊዝ አገር ለመሄድ መመረጤን የሰሙ የለገሀር ሰፈር የቅርብ አብሮ አደግ ጓደኞቼ ተረፈ እንግሊዝን የመሰለ አገር ደርሶሃል እንዳትመለስ ጥፋ ሲሉኝ ሰዎች አገሬን፣ ወገኔን እናቴን ጥዬ አልከዳም ብዬ ተመልሼ የደረሰብኝን በደል እስከሚሰለች ድረስ ነው የዘረዘርኩላችሁ። በኋላ ግን ግፍና በደል ሲበዛብኝ ተመልሼ አገሬ የገባሁበትን ቀን እስከማማረር ድረስ ነው የሩጫ እድሜዬ ከተላለፈ በኋላ ሳሎድ በግዴ ከምንም በላይ ከምወዳት አገሬ፣ ቤተሰቤና ኢትዮጵያዊ ወገኖቼ ተለይቼ ኦስትሪያ ቬይና ማራቶን የውድድር ግብዣ (competition invitation) አግኝቼ ተሰደድኩ። እናም በርካታ ወንድና ሴት አትሌቶች ዜግነታቸውን ቀይረው የተሰለፉበትን አገር በኦሎምፒክ፣ በዓለም ሻምፒዮና፣ በዓለም አገር አቋራጭ፣ ሻምፒዮና፣ በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናና በሌሎችም ዓለማቀፍ ውድድሮች በመወከል አሸናፊ የሆኑ ታላላቅ አትሌቶች ናቸው ዜግነታቸውን እንዲቀይሩና ለሌላ አገር እንዲወዳደሩ ያደረጋቸው በተወለዱበት አገር በደረሰባቸው ግፍ ነው። የአትሌቶቹ የኩብለላ ምክንያት በስፖርቱ ዘርፍ ያለው አድሎ እና መገለል እንዲሁም ጥሎ ማለፍ ሲሆን፤ አትሌቶች ለረጅም ጊዜ ላባቸውን ገብረው ልምምዳቸውን ሰርተው ለውድድሮች ዝግጁ ከሆኑ በኋላ በምክንያት፤ በመተዋወቅ፤ በምቀኝነት፤ በጓደኝነት፤ በጥቅማጥቅም፤ በወንዜ ልጅነት እና በመሳሰሉት ከውድድር ማሰናከል አትሌቶች የሚወዱትን ሀገር ጥለው እንዲኮበልሉ ምክንያት ነው።
ኢትዮጵያ በደረሰብኝ የ8 ዓመት በደል ሞራሌ ላሽቆ በተለይ እናቴን በሞት ካጣሁና ከቦስተን ማራቶን ካስቀረኝ በኋላ ሞራሌ ወድቆ ነበር ነገር ግን አውሮፓ ከገባሁ ጀምሮ ያ ጨልሞብኝ የነበረው የበደል ተስፋ መቁረጥ ጠፍቶ የነበረውን አምላኬ ጭለማውን ገፎልኝ እጂግ በጣም የማምናት እጣ ክፍሌ ኪዳነ ምህረት ሀይልና ብርታት እየሰጠችኝ አገር ቤት በተደጋጋሚ በደል ሲያደርስብኝ እኔም መሮኝ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ለራሴ መጠበቂያ ሰጥቶኝ የነበረውን የጀርመን ስሪት ሉገር ሽጉጥ ይዤ ወደ ስታዲየም በመሄድ የሰውዬውን ቢሮ ሳንኳኳ የለም መኪናውም ከቆመችበት የለችም አምላክ አላገናኘንም እንጂ በተስፋ መቁረጥ እልህ ተገናኝተን ቢሆን ዛሬ በህይወት ቆይቼ ይህን ልፅፍም በደሌን ለህዝብ ላካፍልም ባልበቃሁ ነበር።
እናም ተስፋ ሳልቆርጥ ከፈተናዎች በኋላ በ1988 በ 10,000 ሜትር የኦስትሪያ ሻምፒዮን የሆንኩበት ቀን በህይወቴ ከተደሰትኩበት ቀን አንዱ ነው። 5,000 ና 10,000 ሺ ሜትር የትራክ ላይ ውድድር ከኢትዮጵያ ከመውጣቴ ከ 5 ዓመት በፊት ነው ያቆምኩትና ወደ ማራቶን የገባሁት እዚህ አውሮፓ ከመጣሁ በኋላ ትኩረቴ ግማሽ ማራቶንና የጎዳና ላይ ውድድሮች ነበር የክለቤ የPonigl road runners Austria club ፕሬዚዳንት Dr. Herbert EDERER ተረፈ 10 ሺ ሜትር የ Styria ክፍለ ሀገር ሻምፒዮና ውድድር አስመዝግቤሃለሁ አለኝ ተወዳደርኩና አሸነፍኩ ከዛ 1 ወር በኋላ የኦስትሪያ ሻምፒዮና በዚህ ጊዜ እዚህ ቦታ ይደረጋል እንድትወዳደር አስመዝግቤሃለሁ አለ እኔም ዶክተር እኔ ለትራክ ውድድር የሚያበቃ የዙር ልምምድ ለትንፋሽና ጥንካሬ እንዲሁም የፍጥነት ልምምድ አልሰራሁም በዛ ላይ ጤናዬን ታውቃለህ የጡንቻ መታወክና የጉልበት ችግር ደርሶብኝ ስታክመኝ ቆይተህ በቅርቡ ነው የተሻለኝ ይህ የመላው የኦስትሪያ ሻምፒዮና ነው ሁሉም ጎበዞች የሚሳተፉበት ውድድር ነው ቀላል አይደለም ብዬ ብለው ተረፈ አምናለሁ ታሸንፋለህ አለኝ እኔም በጣም ጥሩ ክለቤንና በርካታ ጥቅማጥቅም የሚያደርጉልኝን ስፖንሰሮቼን ላለማስቀየም እሺ እሞክራለሁ ብዬ የውድድሩ ቦታ 300 ኪ/ሜትር ካለሁበት ከተማ ይርቃል ወደ ጀርመን ቦርደር አካባቢ Salzburg የተባለ ቦታ የሱን ረዳት በመኪና ይዞኝ ሄደ መንገድ ላይ ቀለል ያለ ምሳ በላን እንዳይከብደኝ ውድድሩ ከሰዓት 11 ሰዓት ነው የሚጀምረው የአውሮፓ የቀበጠ የበጋ ሙቀት ለጉድ ነው ያሰክራል ያቺ የበላኋት ምሳ በሙቀቱ ተቃጥላ አልቃለች ሰውነት ስናሟሙቅ አንጀቴ እጥፍጥፍ አለ እርቦኝ እንዳይሆን የለም ውድድሩ ተጀመረ እኔን ለማስለቀቅ ተራ በተራ እየተፈራረቁ ይሉት ጀመር እኔም ሳልንቀለቀል የሚመሩትን እግር ይዤ ስንለው ዋልን ከዛ ሁሉን አራግፈን 2 ኪ/ሜትር ሲቀር 3 ብቻ ቀረን ያው ጀግናው ምሩፅ ይፍጠር ያስተማረኝ ፍጥነት አለ ልክ 1 ዙር ሲቀር ያለ የሌለኝን ተተኮስኩ ለአምላክ የሚሳነው የለም በህልሜም በውኔም ያላሰብኩትን የኦስትሪያ ሻምፒዮን ሆንኩ።
“ይኸው የቀድሞ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን የረጅም ርቀት አሰልጣኝ የነበረው አቶ ንጉሴ ሮባ ደርግ ወድቆ ወያኔ ስልጣን እንደያዘ በደርግ ስርዓት የጥቁር አባይ ኒሻን ተሸላሚ ያደረገውን ደርግን ለማጥላላት ሲሞክርና እኔንና መሰል ለሱ ያላጎበደድን የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ያለን አትሌቶችን ለመንካትና ለማሸማቀቅ ያረጁ የደርግ መኮንኖች ስራዬን እንዳልሰራ ይረብሹኛል ብሎ ያለው ሁል ጊዜ ትዝ ይለኛል፤ የደከምኩላት አገሬ የነበረው ደም መጣጭ አሰልጣኝ አርጅተሃል ቢለኝም በከፋኝ ጊዜ የተሰደድኩባትና አንቀባራ የምታኖረኝ ኦስትሪያ ደግሞ ወድቆ የነበረውን ሞራሌን ገንብታልኝ አምላኬ ሀይልና ብርታት ሰቶኝ ይህን በማየቴና ለዚህ ላበቃኝ አምላኬ፤ ኪዳነ ምህረት ክብር ምስጋና አቀርባለሁ።”
ይህን የኦስትሪያ ሻምፒዮና የሆንኩበትን ውጤት በፌስቡክ ላይ ፖስት አድርጌ አንዱ ጓደኛዬ አንቦ ይህን አስተያየት አሰፈረ “በኦስትሪያ ላይ ያገኘኸው ድል የልፋትህ ያፈሰስከው የላብህ ውጤት ነው እኔ ከኢትዮጵያ ት/ቤቶች ሻምፒዮና ጀምሮ እስከ ጌትሸድ የዓለም ሻምፒዮና ድረስ ያለውን ተሳትፎ እና ውጤትህን ታታሪነትህን አውቃለሁ የኦስትራ ሻምፒዮን መሆንህም ሲያንስህ እንጂ አይበዛብህም የበለጠውንም አይተሃልና።” አለ አዎ ይህ ከላይ የዘረዘርኳቸው ግፎች ባይፈፀሙብኝ እኔማ አይደለም በኦስትሪያ ሻምፒዮና አገሬንና ወገኔን በኦለምፒክም ሆነ የዓለም ሻምፒዮና ላይ ወክዬ ውጤት ማምጣት ምኞትና አላማ ነበረኝ ይህን ከላይ የጠቀስኳቸውን ፈተናዎች ተስፋ ሳልቆርጥ ተቋቁሜ ለዚህ በመብቃቴ ደስታዬን ለመግለፅና አምላክን ለማመስገን ብዬ ነው።
እናም ምክሬ በተለይ ለአትሌቶች ብዙ ፈተና፣ ችግሮችና መሰናክሎች ያጋጥሟችኋል በምንም ተዓምር ተስፋ አትቁረጡ ያን መሰናክል አልፋችሁ ነገ ሌላ ቀን ይሆንላችኋል።

"Thank God, my wife Birzaf Tesfaye and I have been married for 27 years."====“እግዚአብሄር ይመስገን እኔና ባለቤቴ ብርዛፍ ተስፋዬ 27 ዓመት የት...
03/08/2025

"Thank God, my wife Birzaf Tesfaye and I have been married for 27 years."
====
“እግዚአብሄር ይመስገን እኔና ባለቤቴ ብርዛፍ ተስፋዬ 27 ዓመት የትዳር ህይወት”
=====================================
እኔና ባለቤቴ በ1990 ዓ/ም ስንጋባ የምኖርበት ክፍለ ሀገር ባለስልጣን ለባለቤቴና ለኔ የክፍለ ሀገሩ አርማ ያለበትን የባህል ስጦታ ሲያበረክትልን አብረውን ያሉት ጓደኞቼ Dr. Herbert Ederer እና Mr. Gerhard Nöhrer ስንጋባም የሁለታችን ሽማግሌዎች ናቸው፤ እንዲሁም የምኖርበት የWeiz ከተማ ምክትል ከንቲባው የእንኳን ደስ ያላችሁ ስጦታ ሲያበረክትልን።
ከላይ በጋብቻችን ቀን ማዘጋጃ ቤት የስፖርት ልብስም ለብሰው የመጡ ጓደኞቼ አሉ የሯጭ ጋብቻ በማለት እናም እዚህ ፎቶው ላይ እንደምትመለከቱ የሯጭ ቅርፅ ያለው ኬክ አሰርተው 1ኛ 2ኛ 3ኛ በሚል ደረጃ ላይ ወጥተው አትሌቶች እንደሚሸለሙ የዛን ቅርፅ አስመስለው የሯጮች ጋብቻ በማለት ነበር ጋብቻችንን ያደመቁልን።
ባልና ሚስት ሯጮች በሚል ስለ ጋብቻችን በማግስቱ የተለያዩ ጋዜጦች ላይ ከወጣው
ወገኖች ያደግንበት ኢትዮጵያዊ ባህል ከአውሮፓው ጋር በፍፁም ይለያያል ጋብቻችንን ለመዘገብ የመጣው ጋዜጠኛው እሰው ፊት ካሜራውን ደቅኖ ተሳሳሙ ሲል እንዴት የምንተ እፍረታችንን ያው አፍንጫ ላፍንጫ አስነካክተን።
ባለቤቴን ከኢትዮጵያ ሳመጣ የ3 ወር በቱሪስት ቪዛ ነበር እዚህ ካመጣኋት በኋላ የጋብቻ መፈፀሚያና የኦስትሪያ የመኖሪያ ፈቃድ ቪዛ የሚሰጥበት ቦታ ሄጄ ስጠይቅ መኰንን በኦስትሪያ ህግ መሰረት ከጋብቻ በኋላ ቪዛ ለመጠየቅ ቢያንስ ከኦስትሪያ አዋሳኝ አገሮች መውጣትና ማመልከት ነበረባችሁ ሆኖም አንተ ከተማችንንና ክለብህን ስላስጠራህና ስላስተዋወቅህ ቪዛው ሳያልቅ ጋብቻ ከፈፀማችሁ የባለቤትህን ቪዛ አራዝምላታለሁ ብላኝ ለነዚህ ጓደኞቼ ነግሬ በክብር እንድንጋባ ከማድረጋቸውም በላይ ኒኪ ላውዳ በተሰኘ አንድ የኦስትሪያ አየር መንገድ እኔና ባለቤቴን ሳናቅ አውሮፕላን ውስጥ ከፓይለቶች ጋር እንድንቀመጥና ሻምፓኝ እንዲከፈትልን አድርገዋል ከላይ በጋብቻችን ቀን የስፖርት ልብስም ለብሰው የመጡ ጓደኞቼ አሉ የሯጭ ጋብቻ በማለት ጋብቻችንን ያደመቁልን።
Niki Lauda የሚባል የመኪና እሽቅድምድም Formula 1 ኦስትሪያዊ የዓለም ሻምፒዮና የነበረና በአንድ ወቅት አደጋ ደርሶበት አካሉ ተጎድቶ በኢንሹራንሱ አማካኝነት በተከፈለው ከፍተኛ ገንዘብ በመጀመሪያው አዲስ አውሮፕላን Niki Lauda Air በሚል በከፈተው የበረራ ድርጅት ባለቤቴንና እኔን ልዩ እንግዳ በመሆን ጋብቻችንን እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እኛንም Surprise ለማድረግ በአውሮፕላን ለ1 ሰዓት በኦስትሪያ ምድር ከፓይለቶቹ አጠገብ ሆነን እየበረርን ከአስተናጋጆቹ ሻምፓኝ ተከፈተልን ይህ ልዩ ስሜትን ፈጥሮብናል።
በዚሁም ገጠመኝ ልንገራችሁ ምን ሆነ መሰላችሁ እኛ ሰፊ ሰርግ አላዘጋጀንም ምክንያቱም ከላይ እንደገለፅኩት የባለቤቴ ቪዛ ከማለቁ በፊት ጋብቻ መፈፀም ስለነበረብን ለዛ ቶሎ ብለን ጋብቻ አደረግን እናም ሰው ብዙ ሳናበዛ እኔ የተወሰኑ ጓደኞቼን ለኛ ሽማግሌ ሆነው የሚፈርሙልንን ከማዘጋጃ ቤት ፊርማ በኋላ ማታ እቤት እንዲመጡ ነግረናቸው ባለቤቴ ምርጥ ዶሮ የማያቃጥላቸው፣ አልጫና አትክልቶች ሰርታ ከዳድነን ቤታችንን አዘጋጅተን ወደ ማዘጋጃ ቤት ሄድን ከዛ ከፊርማ በኋላ አንዱ ስፖንሰሬ የነበረው ሆቴል ወስደውን ኬክ ከተቆረሰና ሻምፓኝ ከተከፈተ በኋላ አንደኛው ጓደኛዬ ተረፈ ተነሱ ለጉዳይ ግራዝ ደርሰን እንመጣለን ብሎን ሳይነግረን እኔና ብርዛፍ እንግዶቻችንን ትተን በመኪና መሄድ የቤታችንን ቁልፍ ሶሪያውያን ጓደኞች አሉን ለነሱ ሰጠንና መሄድ ከዛ ምድረ ነጭ ተረፈ አገባ ተብሎ በስልክ ተጠራርተው ወደኛ ቤት መሄድ በፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት ሳሎኑ ጠቦ ኩሽናችንም ቁጭ ብለዋል ያን ብርዬ የሰራችውን ወጦች ሳህን ያቀርቡና ያን ጊዜ የዱቄት እንጀራ መጋገር አለመደችም የተለያዩ ለወጥ መበያ የሚሆኑ ቆንጆ ዳቦዎችን ገዝተናል እናም አቅርበው ምንም ሳያስተርፉ፥ ድስቶቹ ማጠብ እስከማያስፈልግ ጥርግ፥ ግጥም አድርገው በልተው ወይናቸውን ሲጠጡ እኛ ተመልሰን እቤት ደረስን መብላታቸው ደስ ብሎናል ግን ማታ ለጠራናቸው እንግዶች ምን እናብላቸው ከዛ ለጋበዝናቸው ከመምጣታቸው በፊት ደውዬ ይቅርታ ብለናቸው ሌላ ቀን በደንብ ጋበዝናቸው እንዲህ ሆንን እላችኋለሁ።

03/08/2025
The competitions I did in the United States 33 years agoከ33 ዓመታት በፊት በአሜሪካ ያደረግኳቸው ውድድሮች
31/07/2025

The competitions I did in the United States 33 years ago
ከ33 ዓመታት በፊት በአሜሪካ ያደረግኳቸው ውድድሮች

Adresse

Graz

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von Coach Terefe Mekonnen erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Service Kontaktieren

Nachricht an Coach Terefe Mekonnen senden:

Teilen

Kategorie