26/08/2026
የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከፓርቲያቸው ብልጽግና የተለየ አቋም በመያዝ እና በፓርላማው ይህንኑ ካንፀባረቁ በኋላ ወደ አሜሪካ በመሰደድ ተቀጥረው በመስራት ላይ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ እርሳቸው ያሉበት የስራ ዘርፍ በቪዲዮ ተቀርፆ መሰራጨቱን ተከትሎ አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁት አቶ ገዱ "ራሴን በራሴ ለማስተዳደር መቻሌ ኩራትና ክብር እንጂ ዝቅጠት አይሰማኝም" ብለዋል ።
በተለይ እንደ አንድ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣንና ኃላፊነት ላይ እንደነበረ ሰው፣ ከስልጣናቸው በኋላ የተስተካከለ ኑሮ ሊያኖራቸው የሚችል ገንዘብ ባለመያዛቸው ይቆጫቸው እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ገዱ "እኔ በነበረኝ የስልጣን ዘመን የማምንበትን ዓላማ ለማሳካት ነው የሰራሁት እንጂ ከህዝብ ሀብት ላይ የግል ኑሮዬን ለማደላደል አስቤ አላውቅም" ብለዋል። ይህም አሁን ንጹህ ህሊና ኖሮኝ እንድኖር ረድቶኛል ሲሉ ገልጸዋል።
አሁን ላይም ሰው በተለይ ኢትዮጵያውያን ትኩረት ሊያደርጉበት የሚገባው የእኔ የስራ ጉዳይ ሳይሆን በሀገሪቱ የሰላም ጉዳይ ነው ሲሉ "ሰው መጨነቅና አጀንዳ ማድረግ ያለበት እኔ በምሰራው ስራ ሳይሆን ሀገር ቤት በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ስላለው ህዝብ መሆን አለበት" ያሉት አቶ ገዱ ትልቁ ጉዳይ መሆን ያለበት ሀገራችን እንዴት ወደ ሰላም እንመልሳት የሚለው ነው ብለዋል።
ስራዬም ተረጋግጬ እንዳስብ፣ የቤት ኪራዬን እና ሌሎች ክፍያዎቼንም እንድከፍል የሚረዳኝ ነው ያሉት አቶ ገዱ በተለይ ከህዝቡ ለተቀበሉት ገንቢ አስተያየትና ላገኙት አክብሮት ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ምስጋናቸው የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።
የበለጠ መረጃ t.me/times_mereja_ethiopia