25/08/2025
የጨዋታው ውጤት፡ ኒውካስል 2 – 3 ሊቨርፑል 🔥
በሴንት ጀምስ ፓርክ (St. James’ Park) ላይ የተከናወነው ጨዋታ እውነት አስደናቂ ነበር!
ሊቨርፑል በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር ከኒውካስል ጋር ያደረገውን ጨዋታ በድራማዊ ሁኔታ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፎ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል።
የሊቨርፑል የማሸነፊያ ጎሎችን ግራቨንበርች፣ ሁጎ ኤኪቲኬ እና የ16 አመቱ ወጣት ሪዮ ንጉሞሀ ሲያስቆጥሩ፣ ለኒውካስል ደግሞ ብሩኖ ጉማሬሽ እና ዊሊያም ኦሱላ ጎል አስቆጣሪዎች ነበሩ።
በተለይ የጨዋታውን ውጤት የወሰነው የ16 አመቱ ተጨዋች ሪዮ ንጉሞሀ በ100ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ያሳረፋት ድንቅ ጎል ናት።
በዚህ ድል ሊቨርፑል የሊጉን የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች በድል በማጠናቀቅ ስድስት ነጥቦችን ማግኘት ችሏል።
የቀጣይ ጨዋታዎች መርሐግብር፡
* እሁድ: ሊቨርፑል ከ አርሰናል
* ቅዳሜ: ሊድስ ዩናይትድ ከ ኒውካስል ዩናይትድ
እያያችሁ ነበር ግን ?
What a game
⚽️🧐
🌴🌴🌴Mudu Baba Butajira official