01/01/2023
የ16 ዓመት ታዳጊ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ8 አመት ከ5 ወር እስራት ተቀጣ።
በደሴ ከተማ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመዉ አባወራ በእስራት መቀጣቱ ተሰምቷል።
ተከሳሹ ሳሙኤል ሹሙ ይባላል በደሴ ከተማ ቧንቧ ዉሃ ክፍለ ከተማ በመገናኛ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነዉ፡፡
የ28 አመቱ ተከሳሽ አባወራ በቤቱ ዉስጥ በሠራተኝነት የቀጠራትን የ16 አመት ታዳጊ ህፃንን በማስፈራራት አስገድዶ መድፈሩን በደሴ ከተማ የ4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ገልጿል።
ተከሳሹ ድርጊቱን የፈፀመዉ ባለቤቱ ወደስራ የምትሄድበትን ሠአት እና እቤት ዉስጥ ሠዉ የማይኖርበትን አጋጣሚ በመጠቀም ታዳጊዋን በማስፈራራትና አፍና አፍንጫዋን በማፈን በተለያየ ግዜ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሲፈፅምባት መቆየቱ ተገልጿል።
ታዳጊዋ ህፃን ከደፋሪዋ ቤት ከወጣች በሗላ የደረሰባትን ጥቃት ለቤተሠቦቹዋ በመናገሯ ለፖሊስ ጥቆማ በማድረጋቸዉ አስገድዶ ደፋሪዉ አባወራ በቁጥጥር ስር ዉሎ ምርመራ ሲጣራበት ቆይቷል።
ፖሊስ በሠዉና ሀኪም ማስረጃ መዝገቡን በማጠናከር ወደሚመለከተዉ የፍትህ አካል ልኳል፡፡
መዝገቡን የተመለከተዉ የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በቅርቡ በዋለዉ ችሎት ጥፋተኝነቱን በማረጋገጡ ተከሳሽ ሳሙኤል ሹሙ በ8 አመት ከ5 ወር እስራት እንዲቀጣ የወሠነበት መሆኑን በደሴ ከተማ የ4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ዘግቧል፡፡
ሀገሬ ሚድያ