31/08/2026
ወንድማችን ይቅርታ ጠይቋል፤ ይሁን እንጂ ይቅርታዬ ለተሳዳቢዎቼ አይደለም በማለት የራሱን አቋም በግልጽ አስቀምጧል። ከዚህም በላይ ነገሮችን ወቅታዊ ከሆኑ የሀገር ጉዳዮች፣ ስፖርት እና ከሃይማኖት ጋር አላግባብ አቆራኝቶ መቀየር ፍጹም ተቀባይነት የሌለው አደገኛ አካሄድ መሆኑን በአጽንኦት መሰክሯል።
ከሰሞኑ የስፖርት የቦክስ ውድድሮች ጭምር ሃይማኖታዊ መልክ ተሰጥቷቸው መታየቱ ይታወሳል።
እኛም የቀቤና ህዝብ ሕዝብንና ሃይማኖትን ለተለያዩ አላማዎች ማዋሃድ እና ስፖርትን ወደ ሌላ መረን የለቀቀ አቅጣጫ መውሰድ የባህልም ሆነ የሞራል ውድቀት መሆኑን እናምናለን። ይቅርታ መጠየቅ መልካም ቢሆንም፣ የሀገርን ሰላም እና የጋራ እሴቶች የሚፈትኑ እንዲህ ያሉ አካሄዶች ግን ሁልጊዜም ሊወገዙ ይገባል።
ሀይማኖትና ስፖርት የየራሳቸው ቦታ አላቸው፤ ድንበር ማለፍ ግን ፍጹም አይቻልም!