WOLDIA SPORT CLUB FANS

WOLDIA SPORT CLUB FANS WSC

01/02/2021

ጤና ይስጥልኝ!!
30/10/2019

ጤና ይስጥልኝ!!

01/12/2018

ጤና ይስልኝ ወልድያ
እንዴት ናችሁ የወልድያ ስፖርት ክለብ የስፖርት ቤተሰቦች!
አጫጭር መረጃወችን ለመወርወር ብቅ ብለናል!!
=================================
ወልድያ ስፖርት ክለብ በዚህ አመት በከፍተኛ ሊግ ውድድሩር የሚሳተፍ ሲሆን ነገ እሁድ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከአቃቂ ቃሊቲ ጋር በ9:00 ሰአት ከሜዳው ውጭ ያደርጋል!!
ወልድያ ከጥቅምት 2 ጀምሮ ዝግጅቱን በወልዲያ ከተማ ሲያደርግ ቆይቶ ከ ህዳር 1 ቀን ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ በማቅናት በርከት ያሉ የወዳጅነት ጨዋታወችን በማድረግ ዝግጅቱን ሲያካሂድ ቆይቷል!!
ወልድያ ስፖርት ክለብ
#ከውሃ ስራ
#ከጉለሌ
#ከመድን
#ከመከላከያ
#ከየካ
#ከቅዱስ ጊዮርጊስ
#ከአራዳ ክ/ከ
ቡድኖች የወዳጅነት ጨዋታዎችን አድርጓል
*****************************
ወልድያ ስፖርት ክለብ ላይ በዚህ አመት ያሉ ለውጦች
*በአዲስ አሰልጣኝ እና ኮቺንግ ስታፍ አባላት ተጠናክሮ ቀርቧል
*የዛሬ አመት ክለቡ ጋር የነበሩ ተጨዋቾችን 80% ቱን በአዲስ ተጨዋቾች ቀይሯል
*በዚህ አመት አንድም የውጭ ሃገር ተጨዋች አላካተተም
*ሶስት ተጨዋቾች አሳድጓል
*የክለቡ ከ50% በላይ ተጨዋቾች የአካባቢው ልጆች ናቸው
*ክለቡ የተጨዋች መኖሪያ ካንፑን ወደ ስታዲየሙ ቀይሯል!!
************************************
የወልድያ ስፖርት ክለብ ተጨዋቾች ዝርዝር!!
1. አንተነህ አሳየ
2. ተስፋሚካኤል በዛብህ
3. ነጋ በላይ
4. ሙሉቀን አከለ
5. ዳንኤል ዝናቡ
6. ሞገስ ዝናቤ
7. ፍሬው ብርሃን
8. ዮናስ ወንዳጥር (ቻይና)
9. ሐብታሙ ሲሳይ (ቃሪያው)
10. ሃይሌ ጌታሁን
11. እንድሪስ ሰይድ
12. ተስፋየ ነጋሽ
13. ከፍያለው ሃይሉ
14. ሰለሞን ወ/ጻድቅ
15. ቢኒያም ጌታቸው
16. አብይ ቡልቲ
17. አብርሃም ተስፋ
18. አለማየሁ ፍስሐ
19. በልስቲ ቀረብህ
20. ሲሳይ ሚደቅሳ
21.ይግረማቸው ተስፋየ
22. ተስሉች ሳይመን
23. በረከት አፈወርቅ
24. ሃብታሙ ንጉሴ
25. ብርሃን አንለይ ናቸው!!
********************
የወልድያ ስፖርት ክለብ የኮቺንግ ስታፍ አባላት
አረጋይ ወንድሙ = ዋና አሰልጣኝ
ያዕቆብ አብርሃ = ም/አሰልጣኝ
በኃይሉ ሰፊው = የግብጠባቂ አሰልጣኝ
ዳዊት አለሙ = ቡድን መሪ
ሰለሞን ሰጠ = ፊዚዮቴራፒስት
ዮናስ አለሙ = ኪት ማናጀር
**********************
ገረመው ካሳ = የክለቡ ስራ አስኪያጅ
አህመድኑር ደስታ = የክለቡ ፕሬዝዳንት
***************************
ወልድያ ስፖርት ክለብ ነገ እሁድ ህዳር 23 ቀን በ9:00 ሰዓት የመጀመሪያ ጨዋታውን ከ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ጋር ከሜዳው ውጭ ይጫወታል!!
#መልካም የውድድር ዘመን!!
#ድል ለወልድያ ስፖርት ክለብ!!!

=> facebook.com/woldiasportclub

የወልድያ ስፓርት ክለብ ለ2011 የውድድር ዘመን 14አዳድስ ተጫዋቾችን በማስፈረም የፊታችን አርብ ወደ ካምፕ በመግባት ሌሎችን የጎደሉትን ጨምሮ ለውድድር ቅድመ  ዝግጅቱን ይጀምራል  የፈረሙት...
10/10/2018

የወልድያ ስፓርት ክለብ ለ2011 የውድድር ዘመን 14አዳድስ ተጫዋቾችን በማስፈረም
የፊታችን አርብ ወደ ካምፕ በመግባት ሌሎችን የጎደሉትን ጨምሮ ለውድድር ቅድመ ዝግጅቱን ይጀምራል
የፈረሙትን ተጫዋቾችና ሌሎችንም ጨምረን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን

30/09/2018

LOADING............wsc

አኑ የወልዲያ ልጅሰላም እንደምን አላችሁ ዉድ ወልዲያዊያን እንደሚታወቀው ክለባችን ወልዲያ ስፖርት ክለብ በሆዳሞችና እራስ ወዳድ ጅቦች ከሀገራችን ትልቁ መድረክ ዝቅ እንድንል ተደርገናል ለዚህ...
17/07/2018

አኑ የወልዲያ ልጅ
ሰላም እንደምን አላችሁ ዉድ ወልዲያዊያን እንደሚታወቀው ክለባችን ወልዲያ ስፖርት ክለብ በሆዳሞችና እራስ ወዳድ ጅቦች ከሀገራችን ትልቁ መድረክ ዝቅ እንድንል ተደርገናል ለዚህም ሁሉም በቅርቡ ዋጋውን እንደሚያገኝ እርግጠኛ ነኝ ክለባችን ከዚህ መድረክ ይዉረድ እንጂ ክለባችን ትልቅ መስዋዕትነት ከፍሏል እራሱን ሰዉቶ የኢትዮጵያን ህዝብ ከፍ አድርጓል ይሁንና ወደ ዋናው ጉዳይ ስገባ ስለወደፊቱ ምን ታስቧል? ጥያቄዉ ለሁሉም ነዉ!
1. #አመራሩ ፦ በመጀመሪያ ደረጃ አንድን ነገር ለተሻለ ደረጃ ለማድረስ ጠንክሮ መስራት ነዉ ጠንክረህ ለመስራት ደግሞ አላማ ይኖርሃል አላማህን ለማሳካት እውቀት ያስፈልጋል ስራህን ግብ ለማድረስ መሪ ያስፈልጋል ምን ለማለት ነዉ አመራሩ በእዉቀትና በአላማ የተደገፈ ሊሆኑ ይገባል ዝም ብሎ የፖለቲካ የከሰረ ፖለቲካ ለማስፈፀም እየተመረጡ የህዝብ ሳይሆኑ የአንድ ወገን ተልዕኮ አስፈፃሚ የሚሆን ሊሆን አይገባም ለስፖርቱ ተቆርቋሪ ፍላጎት ታማኝ የህዝብ አገልጋይ ሊሆን ይገባል ዝም ብሎ የህዝብን ገንዘብ ለመዝረፍና ከተጨዋቾች ጋር አየተደራደረ የተሰጠውን አደራ የሚያባክን አመራር አያስፈልገንም አሁንም ስፖርቱን ሊያሳድግ የሚችል ከፕሮጀክቶችና በአከባቢው ያሉ የከተማው ቡድኖች ከታችኛው ቢ ወይም የጁ ከነዚህ ጋር አብሮ መስራትና አሁን ለተፈጠረው ክፍተት መሸፈን የሚቻለው በዚህ ስለሆነ አነዚህ ላይ ሊሰራ የሚችል መሆን አለበት በሌላ በኩል በቅርቡ የዉይይት መድረክ ሊዘጋጅ ይገባል ሰለ ወደፊት አላማችሁን ልታሳዉቁን ይገባል፡፡
2. #ደጋፊ፦ ከደጋፊዉ ምን ይጠበቃል የሚለውን በቀጣይ ፅሁፌ እመለከታለሁ ........................ይቀጥላል!

የ30ኛ ሳምንት የወልድያ ስፖርት ክለብ ጨዋታ አሁንም ከሜዳው ውጭ ወላይታ ዲቻ ጋር ይጫወታል!!ወልድያ ስፖርት ክለብ በመርሃግብሩ መሰረት የ30ኛ ሳምንት ጨዋታውን ወልድያ ላይ እንደሚያካሂድ ...
11/07/2018

የ30ኛ ሳምንት የወልድያ ስፖርት ክለብ ጨዋታ አሁንም ከሜዳው ውጭ ወላይታ ዲቻ ጋር ይጫወታል!!
ወልድያ ስፖርት ክለብ በመርሃግብሩ መሰረት የ30ኛ ሳምንት ጨዋታውን ወልድያ ላይ እንደሚያካሂድ ፕሮግራም የወጣ ኮቺንግ ስታፉ ተጨዋቾችን ወደ ወልድያ ለመውሰድ ቢሞክርም እና ወደ ከተማቸው እንዲሄዱ ለማግባባት ያወያየ ቢሆንም ከ 4 ተጨዋቾች ውጭ ወደ ወልድያ አንሄድም በማለታቸው እና አለመሄዳቸውንም በፊርማ ማረጋገጣቸውን ተከትሎ ጨዋታው ሰበታ ስታዲየም ይካሄዳል!!
ክለቡ ጨዋታው በሜዳው እንዲካሄድ እንደሚፈልግ በመጥቀስ ከ4 ቸጨዋቾች በስተቀር ሌሎቹ ተጨዋቾች ወልድያ ሂደው እንደማይጫወቱ የፈረሙበትን ቃለ ጉባኤ በማያያዝ ለፌደሬሽን ደብዳቤ ጽፎም አሳውቋል!!
ተጨዋቾቹ ወደ ወልድያ ካልተመለሱ እና በሚመለሱት 4 ቸጨዋቾች ብቻ ጨዋታውን ማካሄድ ስለማይቻል ውጤቱ ፎርፌ ቢሰጥ ሌሎች የወልድያን ውጤት የሚጠብቁ ክለቦች ስላሉ ውጤቱ ሌሎች ክለብ ላይ ተጽእኖ ሊያሳርፍ ስለሚችል በወልድያም ይህን ተከትሎ ሌላ ቅጣትም ሊያስቀጣው ይችላል ቅጣቱም እስከ 500,000 ብር ቅጣት እና አንድ ደረጃ ወደታችኛው ሊግ ወርዶ እንዲጫወት የሚደርስ ቅጣት ሊያስቀጣው የችላል!!
ፌጀሬሽኑ በነዚህ ምክንያት የተነሳ ይህንን ጨዋታ ሰበታ ላይ ከሌሎች ወሳኝ ጨዋታወች ጋር በተመሳሳይ ሰአት እንዲካሄድ ወስኗል!!
የወልድያና የ ወላይታ ዲቻም ጨዋታ ቅዳሜ በ9:00 ሰአት ሰበታ እንደሚካሄድ መወሰኑን እየገለጽን ዝርዝር ሁኔታውን የምናሳውቅ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን!!

ይሄ የምንመለከተው ልጅ ሀይሉ ጓንጉል ይባላል በወልድያ ከተማ የገነት ፍሬ ስፓርትቡድን የታዳጊወች አሰልጣኝ ነው፡፡ስለሱ ብዙ አልናገርም ምክኒያቱም ሁሉ ነገሩመልካም ሰው ነው በአጭሩዛሬ አንድ...
19/06/2018

ይሄ የምንመለከተው ልጅ ሀይሉ ጓንጉል ይባላል በወልድያ ከተማ የገነት ፍሬ ስፓርት
ቡድን የታዳጊወች አሰልጣኝ ነው፡፡ስለሱ ብዙ አልናገርም ምክኒያቱም ሁሉ ነገሩ
መልካም ሰው ነው በአጭሩ
ዛሬ አንድ ደስ የሚል ሀሳብ ስለነገረኝ እኔም ሀሳቡን ወድጀው ፓሰትኩት
ሀሳቡ በወልድያና አካባቢው ያሉት ወጣቶች ለማሰባሰብ በፍቅር አንድ ለመሆን
ችግሮቻችንን ለመፍታት ለመነጋገር በወልድያ በአራቱም አቅጣጫ አንድ አንድ የስፓርት
ቡድን አቋቁመን ውድድር እናዘጋጅና በደንብ እንፋቀር እንገናኝ አንድ እንሁን ፍቅርን
መሰባሰብን ከሚኒስተራችን እንማር የሚል ሀሳብ ነው፡፡፡እስኪ በዚህ ላይ ሀሳብ
አስተያየት እንስጥበትና እንደት በምን ሁኔታ የሚለውን ቀጣይ እናወራለን ፡፡፡፡

ጨዋታው ጀመረአርባምንጭ 0-0 ወልዲያfacebook.com/woldiasportclub
28/05/2018

ጨዋታው ጀመረ
አርባምንጭ 0-0 ወልዲያ
facebook.com/woldiasportclub

ትላንት እለት ግንቦት 07/2010 ዓ.ም የወልድያ ስፖርት ክለብ ቤተሰቦች ቤተሰባዊ ግንኙነቱን የበለጠ ለማጠናከር ባዘጋጁት የራት ፐሮግራምበመጀመሪያ ወደ ክለቡ የተቀላቀሉትን አሰልጣኝ ዘላለም...
16/05/2018

ትላንት እለት ግንቦት 07/2010 ዓ.ም የወልድያ ስፖርት ክለብ ቤተሰቦች ቤተሰባዊ ግንኙነቱን የበለጠ ለማጠናከር ባዘጋጁት የራት ፐሮግራም
በመጀመሪያ ወደ ክለቡ የተቀላቀሉትን አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው (ሞሪኒሆ) (የክለቡን ዋና አሰልጣኝ)
አቶ ያዕቆብ አብርሀም (የክለቡን ም/አሰልጣኝ)
አቶ አሰፋ ብርሀን (የክለቡን ቡድን መሪ) መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው እየተመኙ
ካስተላለፏቸው መልዕክቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
1. የዚህ ክለብ ባለቤት ህዝብ ነው፡፡ ይህ መልካም ህዝብ ክለቡ በፕሪሚየር ሊጉ ቆይቶ መዝናናት፣ ከተማዋን ማስጠራት፣ስቴድየሙ ባዶ እንዳይሆንበት እና የሚወደዉን ክለብ ሁሌም ማየት ይፈልጋል፡፡ ለዚህም ማንኛውንም ሰናይ ተግባር ከመፈፀም ወደኋላ አይልም፡፡
2. ተጫዋቾቻችን ከተለያየ አካባቢ ልትመጡ ትችላልችሁ፣ የተለያየ ሀይማኖት የተለያየ አመለካከት ሊኖራችሁ ይችላል፡፡ ሁላችንም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የምንተጋዉ ለክለባቺን እንደመሆኑ ድንገት ተገቢ ያልሆነ ተግባር የሚፈፅም ግለሰብ ቢኖር እንኳን ሁሌም ከጎናችሁ መሆናችነን እና እናንተም እምነት የሰጣችሁ እና የሚወዳችሁን ህዝብ እንዳትረሱት መግለጽ እንፈልጋለን፡፡
3. በቀሪ 8 ጨዋታዎቻችን ላይ ድንገት ስሜታዊ ሊያደርጉን የሚፈልጉ ግለሰቦች፣ሁኔታዎችን እና ዉሳኔዎችን ወዘተ በመቻቻል እና ክለባችንን የመታደጉን ተልእኮ ባለመርሳት ፣ አላማችንን ብቻ ማሳካት እንዳለብን ፣ ለክለባች ተጫዋቾች እና ኮቺንግ ስታፍ እንዲሁም ለክለባችን ደጋፊዎች መግለፅ እንፈልጋልን፡፡
Like . . . https://facebook.com/woldiasportclub

Address

Woldia

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when WOLDIA SPORT CLUB FANS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share