ትኩስ ትኩሱን ለእናንተ ke besho soccer

ትኩስ ትኩሱን ለእናንተ ke besho soccer ይህ page ትኩስ፣አድስ እና የተረጋገጡ መረጃዎችን የምያገኙበት ስሆን እርስዎም አብረውን መስራት ይችላሉ።

መልካም ዜና! 🇦🇪🇯🇴የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና ዮርዳኖስ ለጋዛ ነዋሪዎች የአየር ላይ ሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ጀመሩዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች – ከበርካታ ወራት መቋረጥ በኋላ ለመ...
28/07/2025

መልካም ዜና! 🇦🇪🇯🇴

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና ዮርዳኖስ ለጋዛ ነዋሪዎች የአየር ላይ ሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ጀመሩ

ዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች – ከበርካታ ወራት መቋረጥ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (UAE) እና ዮርዳኖስ በጋራ በመሆን ለተቸገሩት የጋዛ ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታ ከአየር ላይ መጣላቸውን አስታወቁ።

ይህ እርምጃ በተለይ የምግብ አቅርቦት እጅግ አስቸጋሪ በሆነበት በዚህ ወቅት ለጋዛ ህዝብ ትልቅ ተስፋን የፈነጠቀ ሆኗል።

በዚህ የአየር ላይ እርዳታ 25 ቶን የሚመዝን ሰብዓዊ እርዳታ ለጋዛ ህዝብ መድረሱ ተገልጿል። የእርዳታው ይዘት በጦርነቱ ሳቢያ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ወሳኝ የሆኑ የምግብና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው።

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና ዮርዳኖስ ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ የአየር ላይ እርዳታዎችን ሲያደርጉ የነበሩ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ከወራት በኋላ ተቋርጦ የነበረው የእርዳታ አቅርቦት በድጋሚ መጀመሩ እጅግ የሚያስመሰግን ጥረት ነው።

ይህ ጥምር እርምጃ ወሳኝ እርዳታን ለማድረስ እና በጋዛ ያለውን አስከፊ ሰብዓዊ ቀውስ ለማቃለል ወሳኝ እንደሆነ ይታመናል።

ምንም እንኳን ይህ የአየር ላይ እርዳታ ወሳኝ ቢሆንም፣ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች የምድር ላይ እርዳታ አቅርቦት አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ይሰጣሉ።

ቢሆንም፣ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የተደረገው እያንዳንዱ የእርዳታ ጥረት ለጋዛ ህዝብ ሕይወት አድን መሆኑ የማይካድ ነው።

ለጋዛ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን የብዙዎች ምኞት ነው።

ምንጭ: Khaleej Times

🙏🙏🙏

እድለኛዋ 50 ሚሊየን ብሩን አፈሱትየ50 ሚሊዮን ብር እና የ25 ሚሊዮን ብር የሎተሪ አሸናፊዎች  ተገኝተው ሽልማታቸውን በይፋ ተረከቡ ። የቤትና መኪና ሽልማት ከተጨማሪ ገንዘብ ጋር ያሸነፉም...
26/07/2025

እድለኛዋ 50 ሚሊየን ብሩን አፈሱት

የ50 ሚሊዮን ብር እና የ25 ሚሊዮን ብር የሎተሪ አሸናፊዎች ተገኝተው ሽልማታቸውን በይፋ ተረከቡ ።

የቤትና መኪና ሽልማት ከተጨማሪ ገንዘብ ጋር ያሸነፉም እንዲሁ ሽልማታቸውን ተረክበዋል።

ከደብረ-ብርሀን 10ኪሎ ሜትር በምትርቀው ሰሚነሽ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስትያን ለንግስ ሄዳ በቆረጠችው የሚሊየን ትኬት የ50 ሚሊዮን ብር ዕድለኛ ያደረጋት ወጣት የሽቱ ምስጋናው ትባላለች፡፡

ትውልድና ዕድገቷ ጎንደር ከተማ የሆነው ወጣት የሽቱ ምስጋናው በጎንደር ከተማ ውስጥ የሸቀጣ ሸቀጥ ነጋዴ ናት፡፡

የሽቱ ምስጋናው የ50 ሚሊዮን ብር ቼኳን በዛሬው ዕለት ተረክባለች፡፡

ካሳ አለሙ አዲስ አበባ ውስጥ በአንድ ኮንስትራክሽን ድርጅት ውስጥ በወር የ1500 ብር ተቀጥሮ የሚሰራ የጥበቃ ሰራተኛ ነው፡፡

ለበርካታ አመታት ስራ አጥ ሆኖ አሳልፏል። በዚህ ሁሉ መካከል ግን ሎተሪ ከመቁረጥ “ደከመኝ” ብሎ አያውቅም።

በአንድ የተባረከ ቀን አዲስ አበባ በተለምዶ 24 በሚባለው አከባቢ ከአንድ ሎተሪ አድራሽ በ200 ብር የሚሊየን ሎተሪ ሲቆርጥ ዕድል አይኗን ጥላበት ነበር።

ግንቦት 29/2017ዓ.ም የሚሊዮን ሎተሪ ዕጣ በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አዳራሽ ሲወጣ ሁለተኛው የ25 ሚለዮን ብር ዕጣ ለሱ ነበር የወጣው።

የ25 ሚሊዮን ብር ዕድለኛ ካሳ አለሙ አባይ።

የሚሊየን ሎተሪ የ2ኛ ዕጣ አሸናፊ ወጣት ካሳ አለሙ ቅዳሜ ሀምሌ 19 ቀን በስካይ ላይት ሆቴል በተካሔደ ስነ ስርዓት የ25 ሚሊዮን ብር ቼኩን ተረክቧል፡፡

ባሸነፍከው የ25 ሚሊየን ብር ዕጣ ምን ለማድረግ ተዘጋጀህ ሲባል ቤትና መኪና የመጀመሪያዎቹ ቀድሚ ሰጥቶ የሚያከናውናቸው እንደሆኑ ገልፆ በቶሎ ስራ እንደሚጀምርም አጫውወቶናል።

በቶምቦላ ሎተሪ የቤትና መኪና አሸናፊዎችም የታወቁ ሲሆን እንዲሁ ሽልማታቸውን ተረክበዋል።

የአንደኛ እጣ አሸናፊው አቶ ነጋልኝ አበራ በጨፌ ዶምሳ የፍርድ ቤት ዳኛ ሲሆኑ የአንደኛውን ዕጣ የቤት ቁልፍ ዕድለኛ ሆነው ሽልማታቸውን ተረክበዋል።

አቶ ነጋልኝ በቶምቦላ ሎተሪ በ1ኛ ዕጣ በአዲስ አበባ አፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት አጠገብ የሚገኘውን ባለ 3መኝታ ቤት ቁልፉን ተረክቧል፡፡ በተጨማሪም በየወሩ 60 ሺህ ብር ለ3 ዓመታት ይከፈለዋል፡፡

የ50 ሚሊዮን ብር ተሸላሚን ጨምሮ በቶምቦላ ሎተሪ የቤት እና የመኪና ዕድል ከተጨማሪ ገንዘብ ጋር ያሸነፉ ሌሎች የሎተሪ አሸናፊዎች በዛሬው ዕለት ማለትም ቅዳሜ 19/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል ‹‹ሚሊየነሮቹ›› የሚል ስያሜ በተሰጠው መርሀ ግብር በይፋ ሽልማታቸውን ተረክበዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዘንድሮው የእንቁጠጣሽ ሎተሪ ከ66 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት በተለያዮ ዕጣዎች አጠቃሎ ለዕድለኞች አቅርቧል፡፡

በአንደኛ ዕጣ ከቀረበው የ20 ሚሊዮን ብር ዕጣ በተጨማሪ በሁለተኛ ዕጣ የ10 ሚሊየን ብር፣ በሶስተኛ ዕጣ ደግሞ የ5 ሚሊዮን ብር ዕጣን አጠቃሎ በጥቅሉ የ66 ሚሊዮን ብር ሽልማት በእንቁጣጣሽ ሎተሪ እድለኞችን ይጠብቃል።

ይህንን የሎተሪ ዕድል በቴሌብር እና በ ethiolottery.et ላይ በመግዛት ባለዕድል ይሁኑ፡፡

ለበለጠ መረጃ በ +251977717272
+251950189808 እና
+251950199808 ይደውሉ!
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት!

"ኢትዬጲያ የምን ግዜም ቤቴ ናት"jessica Roseየዩጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት jessica Rose ለኢትዮጵያ ያላቸውን ፍቅር በተለያዩ መንገዶች ከሚገልፁከሚያንፀባርቁ የአገራት መሪዎች አን...
26/07/2025

"ኢትዬጲያ የምን ግዜም ቤቴ ናት"

jessica Rose
የዩጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት jessica Rose ለኢትዮጵያ ያላቸውን ፍቅር በተለያዩ መንገዶች ከሚገልፁከሚያንፀባርቁ የአገራት መሪዎች አንዷ ናቸው።

ም/ፕሬዝዳንቷ በ2ተኛው የተ.መ.ድ የምግብ ስርዓት ጉባኤ ላይ ለመካፈል ዛሬ አዲስአበባ ሲገቡ የኢትዮጵያን የአገር ባሕል ልብስ ለብሰው በምጣት ለኢትዮጵያ ያላቸውን ክብርና ፍቅር አሳይተዋል።

በወላይቶ ሶዶ ኦቶና ሆስፒታል የተከሰተው እሳት አደጋ የሆስፕታሉን ዋና ህንፃ ከጥቅም ውጭ አድርጎታል‼️እሳቱን መቆጣጠር ቢቻልም ሆስፕታሉ ላይ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል!የሆስፕታሉ ድንገተኛ ...
26/07/2025

በወላይቶ ሶዶ ኦቶና ሆስፒታል የተከሰተው እሳት አደጋ የሆስፕታሉን ዋና ህንፃ ከጥቅም ውጭ አድርጎታል‼️

እሳቱን መቆጣጠር ቢቻልም ሆስፕታሉ ላይ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል!

የሆስፕታሉ ድንገተኛ ክፍል ፣ ዋናው ህንፃ እና በውስጡ ያሉ አብዛኛው የህክምና መሳሪያዎች እና የላብራቶሪ እቃዎች ፣ የህሙማን ኬዝ መዝገቦች ወድመዋል!

እስካሁን ድረስ በታካሚዎች ፣ በአስታማሚዎች እና በህክምና ባለሞያዎች ህይወት ላይ ስለደረሰው አደጋ መረጃ አልደረሰንም!

በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ካለ መረጃውን እንድታደርሱ እንጠይቃለን!

ሆስፕታሉ ለደቡባዊ ኢትዮጵያ ከሚሰጠው አገልግሎት አንፃር የጤና ሚኒስተር ፣ የክልሉ መንግስት እና የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲት ተረባርበው አገልግሎት ማስጀመር አለባቸው!

የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየሠራን የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤን ለማስተናገድ ተዘጋጅተናል - የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎትኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በጀመረ...
26/07/2025

የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየሠራን የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤን ለማስተናገድ ተዘጋጅተናል - የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በጀመረቻቸዉ ጥረቶች በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል፤ ለላቀ ስኬትም ጥረቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ በዚህ ወሳኝ ወቅት ኢትዮጵያ ከጣልያን መንግሥት እና ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በመቀናጀት 2ኛዉን የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡

ይህም በኹለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ግንኙነቶች ውስጥ ኢትዮጵያ እየተጫወተች ያለዉን ሚና የሚጎላ፣ በሥርዐተ ምግብ ዙሪያ የጀመረቻቸዉን ስኬታማ ተግባራት የሚያበረታታ ነው፡፡

ከዐራት ዓመታት በፊት በመጀመሪያዉ የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤ ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎች ኢትዮጵያ በምታስተናግደዉ መድረክ ይገመገማል፤ ቀጣይ አቅጣጫዎችም ይቀመጣሉ፡፡

ኢትዮጵያ በምታስተናግደዉ ጉባኤ ርኃብን ስለማስወገድ እና ምግብ ዋስትና፣ ስለአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶች ምክክር ይደረጋል፤ ቀጣይ መወሰድ የሚገባቸዉ ርምጃዎችም ይመላከታሉ፡፡

ኢትዮጵያ ጉባኤዉን የምታስተናግደዉ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን በማስመዝገብ የማንሰራራት ጉዞን በጀመረችበት ወቅት ነው፡፡

ለጉባኤዉ በተሞክሮነት የምታካፍላቸዉ በርካታ ስኬቶችም አሏት፡፡

በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በአረንጓዴ ዐሻራ ስኬታማ ድሎችን አስመዝግባለች፡፡ በአየር ንብረት ለውጥ ረገድም ባለፉት በጣት የሚቆጠሩ ዓመታት ከ40 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ለዓለም አብነት ናት፡፡

ጉባኤዉ በሚካሄድበት በዚህ ክረምትም 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል እየተጋች ነው፡፡

የሚተከሉት ችግኞች የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ከማስቻላቸውም በላይ የምግብ ዋስትናን እና ሥርዐተ ምግብን ለማሻሻል ሚና ያላቸው ናቸው፡፡

የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤን እንድታስተናግድ ለኢትዮጵያ ዕድል መሰጠቱም ይህንን ጅምር ዕውቅና የሚሰጥ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ባለብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ እየገነባች እና ኹለንተናዊ ስኬት እያስመዘገበች ባለችበት በዚህ ወቅት ከሐምሌ 20-22/2017 ዓ.ም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ሥርዐት ጉባኤን በአዲስ አበባ ታስተናግዳለች፡፡

በጉባኤዉ የአገር መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ ሳይንቲስቶች፣ የምግብ አምራቾች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ የሴቶች ድርጅቶች፣ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች ይሳተፋሉ።

ኢትዮጵያም የመዲናዋን ገጽታ በእጅጉ ለውጣ እንግዶችን በላቀ ዝግጅት ለመቀበል ተሰናድታለች፡፡

በርካታ ስኬቶቿንም በልምድነት ለማካፈል ተዘጋጅታለች፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ለዘመናት ያስቀጠሉትን ለኹለትዮሽና ባለብዝኃ ወገን ግንኙነት ትኩረት የመስጠት ልምድ ተጠቅመዉ ጉባኤዉን በላቀ ስኬት ለማስተናገድ በቂ ቅድመ ዝግጅት አድርገዋል፡፡

የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Address

Soddo

Telephone

+251931647463

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ትኩስ ትኩሱን ለእናንተ ke besho soccer posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ትኩስ ትኩሱን ለእናንተ ke besho soccer:

Shortcuts

Share