Ebinat High School ebhs

Ebinat High School ebhs በዚህ የ facebook ገፅ አጠቃላይ ስለ እብናት 2ኛ ደ/ትቤት ወቅታዊ ?

26/01/2023

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በዚህም ተፈታኞች ከዛሬ ሌሊቱ 5 ሰዓት ከ30 ጀምሮ በ በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/

በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም በቴሌግራም https://t.me/eaesbot ማየት የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ተፈታኞች ከተመሳሳይ እና የተዛባ መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት እራሳቸውን እንዲጠብቁም አገልግሎቱ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

2015
22/09/2022

2015

25/04/2022

selected student

18/04/2022

በ2013 የትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎችን አስመልክቶ የተላለፈ አዲስ ውሳኔ!!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የተከበራችሁ ተማሪዎቻችን፣ የተማሪ ወላጆች፣ መምህራን የትምህርት አመራሮች እና አጠቃላይ የትምህርት ማህበረሰብ በሙሉ፡፡

የሁላችንንም ትኩረት ስቦ የቆየው እና በርካታ ትግል ሲደረግበት የነበረው የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ጉዳይ ከዚህ ቀጥሎ በተገለፁት ሁለት ውሳኔዎች የሚፈፀም ይሆናል፡፡

1. ከዚህ በፊት በተላለፈው የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ወደ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች መግባት ከቻሉት የክልላችን ተማሪዎች በተጨማሪ 4339 ተማሪዎቻችን በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ቅበላ እንዲያገኙ ተወስኗል።

2. በ2013 ዓም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ወደ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመግቢያ ነጥብ ያላሟሉ የክልላችን ሁሉም ዞኖች ተማሪዎች በ2014 ዓ.ም በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በመደበኛ ተማሪነት (as regular students) መፈተን እንዲችሉ ተወስኗል።

ይህ ውጤት ሊመጣ የቻለው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተማሪዎችን ውጤት መቀነስ ባወቀ ማግስት መረጃዎችን በማደራጀትና በመተንትን ለተማሪዎች ውጤት ባልተለመደ ሁኔታ ማሽቆልቆል ምክንያት ይሆናሉ ያላቸውን መላምንቶች በማስቀመጥ ሰፊ ትግል ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር በኩልም የውጤት መቁረጫ ነጥብ ተወስኖ እና ያለፉት ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫ ፎርም የሚሞላበት የመጨረሻው ቀን ከተወሰነ በኋላ ከአማራ ክልል በተነሳ ቅሬታ መነሻነት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ቅሬታውን አዳምጦ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው እንዲራዘም ማድረጉ ትልቅ መደማመጥ የተስተዋለበት ነበር፡፡ ይህም ለቀጣይ በመደማመጥ ላይ የተመሰረተ የሀገር ግንባታ ጉዟችን አንድ ማሳያ ነው ብለን እናስባለን።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በተማሪዎች ጉዳይ አንድም ቀን እንደማይዘናጋ፣ የህዝብን ፍላጎትና ክብር እንዲሁም የኢትዬጵያዊ አንድነታችን ባስጠበቀ መልኩ የሚጠበቅብንን ሁሉ ትግል ማድረጋችንን ልናረጋግጥላችሁ እንፈልጋለን።

ከተፈጠረው ችግር አኳያ ውሳኔው ያላረካችሁ አካላት ልትኖሩ እንደምትችሉ ተገማች ቢሆንም ተማሪዎቻችን በመደበኛ ተማሪነት የመፈተን እድሉን በድጋሜ ማግኘታቸውን እንደ ትልቅ መልካም አጋጣሚ አድርጎ በመውሰድ ለቀጣዩ የከፍታ ጉዟችን መዘጋጀቱ ይጠቅማል ብለን እናስባለን።

አሁን ላይ እያጋጠሙን ካሉት ፈተናዎች ይልቅ መጭው ጊዜ ውስብስብ እና እጅግ ከፍተኛ ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ መሆኑን በመገንዘብ በእልህና ቁጭት በመስራት አንድነታችንን እናጠናክር።

በውጣውረዱ ሁሉ ሀይል እና ብርታቱን ያደለን እና የእስካሁኑ መንገዳችን ባለቤት የሆነው ፈጣሪያችን ለዘላለሙ የተመሰገነ ይሁን!!!

Urgent notification
20/03/2022

Urgent notification

17/03/2022

ማስታወቂያ
በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ባስመዘገባችሁት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላችሁ ተማሪዎች ከዚህ ቀደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳችሁ ይታወቃል። ስለሆነም ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን አውቃችሁ የሚከተሉትን መረጃዎች እንድትመለከቱ እንጠይቃለን፡፡

1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ http://Portal.neaea.gov.et ገብታችሁ እንድታስተካክሉ እየገለጽን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላችሁ የምታመለክቱ ተማሪዎች መረጃችሁን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንድትልኩ እያሳሰብን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር

የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
ፌስቡክ https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

13/05/2021
08/04/2021

የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ፡፡

በዚህም የተፈጥሮ ሳይንስ ለወንድ 380 ሲሆን ለሴት ደግሞ 368 መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች ደግሞ ለወንድ 368 እንዲሁም ለሴት 358 መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ዑርቃቶ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም መስማት ለተሳናቸው ለወንድ 350 እንዲሁም ለሴት 345 ሲሆን ለአርብቶ አደሮች አካባቢ ደግሞ 358 መግቢያ ውጤት ሆኗል፡፡

ከዚህ ባለፈም በትግራይ እና መተከል ደግሞ ለወንድ 358 ለሴት ደግሞ 350 መሆኑንም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

ለማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ለወንድ 370 ሲሆን ለሴት ደግሞ 358 ሆኗል፡፡

ለታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ለወንድ 358 እንዲሁም ለሴት 348 ሆኗል፤ መስማት ለተሳናቸው ለወንድ 340 እንዲሁም ለሴት 335 እንዲሆን ተወስኗል፡፡

በትግራይና መተከል ደግሞ ለወንድ 348 እንዲሁም ለሴት 340 ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሙሃመድ አሊ እና መታገስ አየልኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

ለእብናት 2ኛ ደ/ት/ቤት ተማሪዎች የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳችሁ የውጤት ስህተት ላጋጠማችሁ በዚህ ገፅ በመግባት ፎርሙን ይሙሉ፡፡www.neaea.gov.et  ከዛ complaint...
03/04/2021

ለእብናት 2ኛ ደ/ት/ቤት ተማሪዎች የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳችሁ የውጤት ስህተት ላጋጠማችሁ በዚህ ገፅ በመግባት ፎርሙን ይሙሉ፡፡
www.neaea.gov.et ከዛ complaint ከዛ ሙሉ መጠይቁን ይሙሉ E-mail ያስፈልጋልና ከሌላችሁ የጓደኛወትን ይጠቀሙ ቀኑ ውስን በመሆኑ በቶለ register ያድርጉ፡፡

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ ተገለፀ። By NEAEA  /  February 11, 2021 ትምህርት ሚኒስቴር በኦን ላይን ሊሰጥ የነበረውን የ2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወ...

29/03/2021

Address

T'is Abay

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ebinat High School ebhs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category